መንፈሳዊ እርጅና
#መንፈሳዊ_እርጅና
◆◆◆◆◆◆◆
📌መንፈሳዊ እርጅና፦በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚከሰት እርጅና ዓይነት ስሆን የክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ሕይወትን በኃይልና ሁኔታ የሚያጠቃ፣ አልፎም መንፈሳዊ ሕይወትን እስከመግደል የሚደርስ አደገኛ ነገር ነው።
📌መንፈሳዊ እርጅና፦የክርስቲያን መንፈሳዊ ሁለንተናን የሚቆጣጠር፣ መንፈሳዊ አቅምን የሚያሳጣ ሰውን ተራ ክርስቲያን የሚያደርግ አደገኛ የሰይጣን #System ነው።
#መንፈሳዊ_እርጅናና_ተፈጥሮአዊ_እርጅና
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
📌መንፈሳዊ እርጅናን ከተፈጥሮአዊ እርጅና ጋር የሚያመሳስላቸውም የሚያለያያቸውም ብዙ ነገሮች እሉት። ለምሳሌ
📌ሁለቱም እርጅናዎች ከጤና ችግር ጋር ተያይዞ ይመጣሉ።
♦ለሰው ልጅ ከምንም በላይ ጤንነት እጅግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነገር ነው። ሰው በሕይወት ለመኖር ከየትኛውም ነገር በላይ ጤንነት ያስፈልጋል። ሰው ጤናማ ካልሆነ በሽተኛ ይሆናል። በሽተኛ ከሆነ ደግሞ ጊዜውን ያልጠበቀ እርጅና ይመጣል። ጊዜውን ያልጠበቀ እርጅና ተከትሎ ደግሞ ጊዜውን ያልጠበቀ ሞት ይመጣል። ለሁለቱም እርጅናዎች ላይ ጤንነት ጉልህ ምናን ይጫወታል።
✔#ጤንነት ስባል ከበሽታና ከህመም ስሜት ብቻ ነፃ መሆን አይደለም፡፡ ጤና የተሟላ #አካላዊ፣ #ስሜታዊ፣ #መንፈሳዊ እና #ማኀበራዊ ደህንነት ነው፡፡ መጀመሪያ ይሄ ግንዛቤ ውስጣችን ሊኖር ይገባል፡፡ አንድ ሰው አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጤንነቱ በሙሉ ተሟልቶ ሲገኝ ነው ሙሉ ጤነኛ ነው ልንል የምንችለው፡፡ እነዚህ ሁሉ ባልተሟሉበት ሁኔታ ውስጥ አንድ ሰው ህመም ስለማይሰማው ብቻ ጤነኛ ነው ሊባል ግን አይችልም፡፡ ሙሉ የሆነ የአካል፣ የስነልቦናዊ እንዲሁም የማኀበረሰባዊ ደኀንነት ነው::” ይለዋል፤ ይህም ሲባል የበሽታ አለመኖር ብቻ ጤነኝነትን አይገልፅም ማለት ነው፡፡
♦#ጤንነት ስባል #ከምግብ፣ #ከውኃና #ከስፖርት ጋር የተያያዘ ነገር ነው። ሙሉ የሆነ የአካል፣ የስነልቦናዊ እንዲሁም የማኀበረሰባዊ ጤንነት ለማግኘት ጤናማ የሆነ አመጋገብ ማለትም የተመጣጠነ ምግብ፣ ጤናማ የሆነ ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ጤናማና ንጹሕ የሆነ ውኃ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ጤናማ የሆነ ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ጤናማና ንጹሕ ያልሆነ ውኃ ለበሽታ ያጋልጣል። ይህ ጉዳይ ደግሞ መንፈሳዊ እርጅና እጅግ በጣም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። መንፈሳዊ እርጅና እንደ ተፈጥሯዊ እርጅና ከአመጋገብ ጋር (#እግዚአብሔር_ቃል)፣ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ (#መንፈሳዊ_ልምምድ) ከውኃ (#መንፈስ_ቅዱስና_ፀሎት) ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።
✔#በሽታ ስባል ደግሞ የማንኛውንም ግለሰብ #የአካል፣ #የስነልቦናዊ እና #የማኀበረሰባዊ ደኀንነትን የሚያቃውስ ሁኔታ ማለት ነው፡፡ ይህ በሽታ በመንፈሳዊ ቋንቋ ኃጢአት ነው። በሽታ ስበዛ ስጋዊ ሞትን እንደሚያስከትል ሁሉ ኃጢአት አድጎ መንፈሳዊ ሞት ያስከትላል።
♦በሁለቱም እርጅና ላይ እነዚህ ሁለት ነገሮች ማለትም ጤንነትና በሽታ የራሳቸው የሆነ አውንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ያሳድራሉ። ጤንነት በተለይም መንፈሳዊ እርጅናን በከፍተኛ ሁኔታ የሚከላከል ስሆን በሽታ ደግሞ መንፈሳዊ እርጅናን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያፋጥን፤ ከዛም ወደ ሞት የሚያደርስ ነገር ነው።
📌ሁለቱም እርጅናዎች ሁሉንም ይይዛሉ።
♦ተፈጥሯዊ እርጅና ፍጥረታትን በሙሉ የሚይዝ ስሆን መንፈሳዊ እርጅና ደግሞ የሰው ዘርን የሆነውን በሙሉ የሚይዝ በተለይም ክርስቲያኖችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠቃ እርጅና ነው። ሰው የራሱን መንፈሳዊ ጤንነት ካልጠበቀና ካልተጠነቀቀ በስተቀር መጋቢ፣ ወንጌላዊ፣ ነቢይ፣ ሐዋሪያት፣ ነጭ፣ ጥቁር እና ወዘተ መሆን ከመንፈሳዊ እርጅና አያስመልጥም። ነገር ግን ተፈጥሯዊ እርጅና ለማንም የማይቀር #ተፈጥሯዊ ስሆን #መንፈሳዊ_እርጅና_ግን_ሰይጣናዊ_ነው። ማለትም ማንም እንዲሁ መያዝ አይችልም ሰውየው ካልፈቀደ በስተቀር።
📌ሁለቱም እርጅናዎች በጊዜ ህደት ይመጣሉ።
♦ተፈጥሯዊ እርጅና በአንድ ጊዜ ሰውን አይዝም። ይልቁንም በጊዜ ህደት ቀስ እያለ ይመጣል። መንፈሳዊ እርጅናም እንደ ተፈጥሯዊ እርጅና በጊዜ ህዴት የሚመጣ እንጂ በአንድ ጊዜ መተው ክርስቲያኖች የሚያጠቃ ነገር አይደለም። መንፈሳዊ እርጅናም እንዲሁ ቀስ በቀስ እያለ የሚጀመር፣ ከዛም በህደት የሚቀጥል፤ በስተመጨረሻ መላ ሰውነትንና ሁለተናን የሚቆጣጠር አደገኛ የሰይጣን አሰራር ነው።
📌ሁለቱም እርጅናዎች ከእድሜ አንፃር አንዱ ከሌላው ይለያያሉ።
♦ተፈጥሯዊ እርጅና በጊዜ ህደት እድሜን ተከትሎ የሚመጣ ስሆን መንፈሳዊ እርጅና ደግሞ እድሜን ተከትሎ የማይመጣ በሁሉም እድሜ ክልል የሚኖሩ ክርስቲያኖች የሚያጠቃ ክፉ ነገር ነው። በተፈጥሯዊ እርጅና ላይ እድሜ ትልቅ ምና ይጫወታል። በተቃራኒው ደግሞ በመንፈሳዊ እርጅና ላይ ጉዳይ የለውም። በእድሜ ሕጻን ወይም ወጣት መሆን ከመንፈሳዊ እርጅና አያድንም። ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን በእድሜ ሕጻን ወይም ወጣት ሆኖ በመንፈሳዊ ዓለም ደግሞ በጣም ያረጀ ክርስቲያን ልሆን ይችላል። በተቃራኒ ደግሞ በስጋ እጅግ በጣም ያረጀ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ዓለም ደግሞ በመንፈሳዊ እርጅና ያልተጠቃ በጣም ወጣት ልሆን ይችላል።
___ #በመንፈሳዊ_እርጅና_ምልክቶች_____
××××××××××××××××××××××
1) #ኃይማኖተኝነት
◆◆◆◆◆◆◆
◆ሀይማኞተኝነት ትልቁ የመንፈሳዊ እርጅና ምልክት ነው፡፡ ይህ ከመቸውም ጊዜ በላይ በዚህ ዘመን ገኖ ጫፍ የወጣ ለሀገርም ለቤተክርስቲያንም ከፍተኛ ችግር የሆነ ጉዳይ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ የክርስትና ደሴት ተብላ የምትታወቅ ሀገር ብትሆንም በደሴቷ ላይ ያለው አብዛኛው አማኝ ጤናማ ክርስቲያን ሳይሆን የተለከፈ ኃይማኖተኛ ነው።
◉ለኃይማኞተኞች ኃይማኞት እንጂ እምነት የላቸውም። በተቃራኒው ደግሞ ለአማኝ እምነት እንጂ ሀይማኖት የለውም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዎች የሰጠው ኃይማኞት ሳይሆን ሕይወት የሆነውን እምነት ነው። እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በእምነት እንጂ በኃይማኖት አያውቅም። እነርሱ (#ኃይማኖተኞች) ከምንም ላይ አብዝተው የሚጨነቁት፣ የሚያስቡትና የሚከራከሩት ስለእምነት (#ስለክርስቶስ) ሳይሆን ስለኃይማኖት (#ስለዶክትርን_ስለሕግ_ስለባህልና_ስለወግ) ነው። ስለኢየሱስ ወይም ስለ እምነት ምንም ዓይነት ደንታ የላቸውም። በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ኃይማኞት እንጂ እምነት አይደለም። በእነርሱ ደምና ስጋ ውስጥ ያለው ወደ ውስጣቸው ሰርጾ የገባው ክርስቶስ ሳይሆን ኃይማኞትን ነው። ከዚህ የተነሳ ኃይማኞትን ስነሳ ደማቸውን ይፈላል። ለኃይማኖታቸው ስባል የማይከፍሉት ዋጋ የለም፤ የራሳቸውን ጭምር አሳልፎ ይሰጣሉ። በተቃራኒው ደግሞ ስለክርስቶስ ስባል እንኳን የራሳቸውን መስጠት ይቅርና አንድም ነገር ማድረግ አይወዱትም።
◉ ይህ ኃይማኞተኝነት የመንፈሳዊ እርጅና ተቋም ነው። ሰዎች ከዚህ ተቋም ተምረው በመውጣት የራሳቸው ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ኃይማኞተኞች ያደርጋሉ። ይህ ኃይማኞት ሰዎችን ማሰሪያ የሰይጣን ገመድ በተጨማሪ ደግሞ ሰዎችን መውገሪያ የሰይጣን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በዚህ በኃይማኖት ገመድ ብዙዎችን ያስራሉ፤ ደግሞም በዚህ በኃይማኖት ደንጋይ ብዙዎችን ይወግራሉ።
#እነዚህ_ኃይማኖተኞች፦
◆◆◆◆◆◆◆◆◆
✔ከኃጢያት ታቅበህ ራስህን ጠብቀህ ብትኖር ውሸቱን ነው ሲያስመስል ነው እየተደበቀ አንድ ሁለት ይላል ይሉሃል። ደግሞ ድንገት ተንሸራተህ የኃጢያት ጭቃ ያዳለጠህ እንደሆነ እንዴት ትወድቃለህ አርአያ ነህ ስንልህ ይሉሃል። አሃ ብለህ ልብ ገዝተህ በእግዚአብሔር ፊት በንስሐ ወድቀህ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎ ወደቀድሞ ህይወትህ ስትመለስ ደግሞ ተዘግቶ የተረሳ የኃጢአት ፋይል እያገላበጡ እግዚአብሔር ምህረት ያደረገውን ጥፋት እየዘረዘሩ አቤት ይሉ ይጀምራሉ። እንደዚህ እያሉ ለራሳቸው ገሃነም ይገባሉ ደግሞ ሌሎችንም ገሃነም ያስገባሉ።
📖“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።” ማቴዎስ 23፥15
✔በሰው ህይወት ውስጥ ጣልቃ እየገቡ ያልበላቸውን ሲያኩ የራሳቸውን ሊጥ ረስተው የሰውን ሲያቦኩ የሚገኙ ሞኞች ናቸው። የሰውን ጉድፍህ እንጂ የራሳቸውን ምሶሶ ማየት የማይችሉ እውሮች ናቸው።
📖“በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?” ማቴዎስ 7፥3
⚫ሰው ሲወድቅ በድንጋይ ወግረው የሚገሉ የሰው ደም አፍሳሾች ናቸው። ለወደቀው ሰው ምህረትና ይቅርታ እንዳለ እንኳ የማያውቁ የሞተ ውሻን በመደብደብ የሚረኩ ህሊናቸው የታወረ ሞኞች ናቸው።
📖“ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦ መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ዮሐንስ 8፥3-5
⚫አፍቸው ሰፊ ልባቸው ጠባብ፣ ውጭያቸው የሚያምር ውስጣቸው ጨለማ የሆኑ ክፎዎች ናቸው።
📖“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።…እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።" ማቴዎስ 23፡25፤27
⚫ በኢየሱስ ዘመንም የነበሩ፣ ዛሬም በእኛ ዘመንም የሚኖሩ፣ ነገም ደግሞ የሚኖሩ የማይጠፋ ክፎዎች ናቸው። ክርስቶስን የሰቀለው ሰይጣን አልነበረም ሃይማኖተኞች እንጂ። ሲበላ በላ ብለው ይከሱታል...ሳይበላ ሲቀር ደግሞ ይህ ሰው ምግብ የማይበላው ጋኔል ቢኖርበት ነው ይላሉ..ኃይማኖተኞች ወይ የማይገቡ አሊያም የማያስገቡ ደንቃሮች ናቸው። እነርሱ በጣታቸው ሊነኩ የማይደፍሩትን ተራራ አንተ ገፍተህ እንድታነቅንቅላቸው ያዙሃል።
📖“ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።” ማቴዎስ 23፥4
2) #አባልነት
◆◆◆◆◆
◉የቤተክርስቲያን አባልነት ሌላው ትልቁ የመንፈሳዊ እርጅና ትልቁ ነው። በመንፈሳዊ እርጅና የተጠቁ ሰዎች የክርስቶስ አካል ከመሆን ወደ ቤተክርስቲያን አባል ወደመሆን ይሸጋገራሉ። የክርስቶስ አካል አይደሉም ነገር ግን በጣም #Active የሆኑ የቤተክርስቲያን አባልና የእሁድ ደንበኛ ናቸው።
📖“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ።” ማቴዎስ 23፥23
3) #ሥጋዊነት
◆◆◆◆◆◆
◉ሥጋዊነት ሌላው የመንፈሳዊ እርጅና ምልክት ነው። በመንፈሳዊ እርጅና የተጠቁ ሰዎች በአብዛኛው ሥጋዊያን ናቸው። ከዚህ የተነሳ በመንፈስ ቅዱስ ከመመራት ይልቅ በስጋ፣ በስሜትና በልምድ ይመራሉ። የእነሱ ዋና መሪ መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ዶክትሪን ወይም የቤተክርስቲያን ስረአት ነው። በተጨማሪ በእግዚአብሔር ቃል ከመመራት ይልቅ በሰው ቃል ወደ መመራት፣ የሰውን ቃል ወደ መስማት እና የሰውን ቃል ወደ ማመን ይሸጋገራሉ።
4) #መንፈሳዊ_እድገትን_ማቆም
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
◉መንፈሳዊ እድገትን ማቆም ዋነኛ የመንፈሳዊ እርጅና ምልክት ነው። እዚህ ጋር እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ክርስቲያን በመንፈሳዊ እርጅና ስጠቃ መንፈሳዊ እድገትን በማቆም ብቻ አያበቃም። በመንፈሳዊ እርጅና የተጠቁ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ዕድገት በማቆም ይጀምራሉ፣ ከዛም በመቀነስ ይቀጥላሉ በስተመጨረሻ በማድረቅ ይጨርሳሉ። ከዚህ በኃላ እምነታቸው ወደ ኃይማኞት፤ ኃይማኞታቸው ደግሞ ወደ ጣኦት ይሸጋገራል። በስተመጨረሻ አማኞች ሆኖ በሚያሳዝን ሁኔታ ጣኦት አምላክዮች ይሆናሉ።
5) #ለሌሎች_ሸክም_መሆን
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
◉በተፈጥሮ ያረጁ ሰዎች እንኳን ብናይ በጣም አስቸጋሪ ናቸው። ከዚህም በባሰ ሁኔታ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ያረጁ ክርስቲያኖች ለሀገርም ለቤተክርስቲያንም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሸክም ናቸው። መንፈሳዊ አቅማቸውንና ጉልበታቸውን ስላጡ ሌላውን መሸከም አይችሉም። ይልቁንም እነርሱ ለሌሎች ሸክም ይሆናሉ።
_____°#ከመንፈሳዊ እርጅና_እንዴት_እንውጣ°____
×××××××××××××××××××××
⬛አንዳንዴ ጊዜ የመንፈሳዊ ጉልበት ያልቅና አቅም ያንሰናል፡፡ ማለዳ ብርቱና ሙሉ ሆነን ከሰአት በኋላ ውድቅ እንላለን፡፡ መሄድ እንፈልጋለን ግን ይደክመናል፡፡ ወደፊት መራመድና ነገሮችን መፈፀም ያቅተናል፡፡ የሕይወታችን አቅጣጫና የመኖራችን ትርጉም ይጠፋል። የተስፋ ቃሉን ወደ መርሳት፣ የራሳችንን ወደ መጥላት አልፎም ሞትን ወደ መለመን እንገባለን። ይህ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ እርጅና ስጠቁ የሚመጣ የመንፈሳዊ ቀውስ ነው።
⬛በመንፈሳዊ እርጅና ለተጠየቁትና በእንደዚህ ዓይነት አስቀያሚ ሁኔታ ውስጥ ላሉት ትልቅ ዜና አለ። እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት መካከል እንደ ሰውና ንስር የተለየ አስደናቂ ፍጡር የለም። እነዚህ ሁለት ፍጥረታት ከየትኛውም ዓይነት ፍጥረታት የሚለዩበት አስደናቂ የሆነ ባህሪ አላቸው። ይህም እንደገና የመታደስ ወይም ከመንፈሳዊ እርጅና የመውጣት ድጋሚ በመንፈስ ጎልማሳ የመሆን ፀጋ ነው። ይህ አስደናቂ ፀጋ ማለትም የእንደገና ምዕራፍ ለሌላ ለየትኛውም ዓይነት ፍጥረታት አልተሰጠም። በዓለም ላይ አርጅቶ እንደገና መታደስ የሚችል ከሰውና ከንስር በስተቀር ማንም የለም። ሁለቱንም እርጅና ያጠቃቸውል ነገር ግን ሁለቱም ከእርጀናቸው ድጋሚ መታደስ ይችላሉ።
⬛የንስር አሞራ ሚስጥራዊ ተፈጥሮ ፍጥረታት ሁሉ ይችን ምድር ሲወርሱ የተሰጣቸው አስገራሚና ልዩ ውብ ተፈጥሮ አላቸው፡፡ ከነዚህ የተፈጥሮ ፀጋ ከተሰጣቸው ድንቅ የምድራችን ፍጥረታት መካከል አንዱ የንስር አሞራ ነው፡፡ ንስር ይህን ተፈጥሯዊ ፀጋውን በሚገባ ይጠቀማል። ንስር እጅግ በጣም ብልህ ፍጥረት ነዉ። እርጅና ስያጠቃ፣ ኃይሉ ሲደክመው ኃይሉን ማደስ ሲያስፈልገው በደንብ ያውቅበታል። የእግዚአብሔር ቃል በኢሳይያስ 40፥31 ለንስር ያለውን ማንነትን በዝርዝር ያስቀምጣል። የንስር ማንነት በተፈጥሮ በከፍታ መብረር፣ መሮጥ፣ በየትኛውም ሁኔታ አለመታከት፣ አለመድከም እና የትኛውም መሰናክልን አልፎ መሄድ ነው። “እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
⬛ንስር ስያረጅ እነዚህ አስደናቂና ከየትኛውም አዕዋፋት በላይ ያደረገውን ማንነቱን ወደ ማጣት ይደርሳል። ታዲያ በዚህ ጊዜ በከፍታ ከሁኔታ በላይ መብረር ለንስር ችግር ይሆንበታል። ትላንት ዶፍ ዝናብ አያስጨንቀውም ደመናውን ሰንጥቆ ከላይ ሆኖ ያይ የነበረው፣ ትላንት አይኖቹ ከደመና በላይ ሆኖ በርቀት ባህር ውስጥ ያሉትን አሳዎች ያይ የነበረው፣ ትላንት ከደመናና ከሁኔታው በላይ የትኛውም ዓይነት አዕዋፋት በማይደርሱበት ከፍታ ላይ ስበር የነበረው ንስር ከእርጅና የተነሳ የቀድሞውን ማንነቱን መኖር ያቅተዋል። ታድያ ይሄ ንስር የገዛ ላባዎቹ በከፍታ እንዳይበር ተግዳሮት ይሆኑበታል። በዚህ ጊዜ ወደ አለት ንቃቃት ይገባል በዛም ይመሽጋል፤ ያረጁትን ላባዎች በአፉ እየነቃቀለ ያስወግዳቸዋል። ምንም እንኳን ከባድ የሆነ ሕመም ብኖርም፤ ሰውነቱ ብቆስልም። በዚህ ጊዜ ቀድሞ ወደ ሰማይ እየወሰደ አለት ላይ የሚፈጠፍጠው ጠላቱ የሆነው እባብ መድከሙን አይቶ እንደ ቀድሞ አይሆንም። በዚህ ጊዜ የራሱ ጥፍሮቹን አለቱ ላይ እየሳለ ራሱን ይከላከላል። የምሽግ ጊዜው እስኪያበቃ ይታገሳል። ከዚህ በኃላ የቀድሞው ማንነቱን መመለስ ይጀምራል። ጥፍሮቹና ላባዎች ድጋሚ ማቆጥቆጥ ይጀመራሉ። አዲስ ላባ ማቆጥቆጥ ሲጀምር እንደገና በኃይል ተሞልቶ ከቀድሞው ይልቅ በአድስ ኃይልና ጉልበት የቀድሞውን ማንነቱን ይወጣል።
⬛ለእኛ ሁሉም ነገር ያለቀለት፣ ያበቃለት ወይም ደግሞ ያከተመለት መስሎ ልታይ ይችላል። በተጨማሪ ጊዜ ያለፈብን፣ የተበለጥን፣ የሳትን ሊመስለን ይችላል፡፡ ልክ እንደ ኤልያስ "ኤልያስም ፈርቶ ተነሣ፥ ነፍሱንም ሊያድን ሄደ፥ በይሁዳም ወዳለው ወደ ቤርሳቤህ መጥቶ ብላቴናውን በዚያ ተወ። እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል አሁንም፥ አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ ብሎ እንዲሞት ለመነ" (1ኛ ነገሥት 19፡3-4)። ይሁን እንጂ የእንደገና አምላክ የእንደገና ምዕራፍን ይከፍታል። ያበቃ፣ ያለቀና ያከተመ ነገር እንደገና ወደ መኖር ይሸጋገራል። ልክ እንደ አስደናቂው ንስር። ለዚህ ነው የእግዚአብሔር ቃል ክርሰቲያን ከንስር ጋር አያይዞ "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም" (ኢሳያስ 40፡31) የሚለው።
#እንዴት_እንደገና_መታደስ_እንችላለን።
×××××××××××××××××××××
⬛ክርስቲያን ከመንፈሳዊ እርጅና መውጣት፣ እንደገና መታደስና እንደገና ኃይሉ መልበስ ይችላል። ማንኛውም ዓይነት በመንፈሳዊ እርጅና የተጠቃ ክርስቲያን የንስሩ ዓይነት የመታደስ ፍላጎትና መሻት ካለው በሚገባ መታደስና ወደ ቀድሞ ማንነት ልመለስ ይችላል። በእርግጥ ሁኔታ ቀላል አይደለም። በጣም ብዙ ዋጋ ያስከፍላል። ብሆንም ግን ለእኛ ጥቅም ነው።
⬛በመንፈሳዊ እርጅና ውስጥ ገብታችሁ ከባድ ችግር ውስጥ ያላችሁ ለእናንተ ሁለት ምርጫ አለ። እንደኛው ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ወይም ደግሞ ጥቂት ጊዜን የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን ዘመን በሕይወት መኖር። ጉዳዩ የሕልውና ጉዳይ ነው። ጉዳዩ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ነው። ስለዚህ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ግዴታ ነው።
◆የመጀመሪያውን ከመረጣችሁ በጊዜ ትሞታላችሁና ታሪካችሁም እዛ ጋር ያበቃል።
◆የሁለተኛውን ከመረጣችሁ ግን እነዚህን ሦስት መስዋዕትነቶችን መክፈል ይኖርባቸዋል።
➀ኛ.በከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት ለብቻችሁ ጎጆን ቀልሱ።
✔ማለትም ወደ አለት ንቃቃት ውስጥ ገብታችሁ በዚያ ተሸሸጉ። ይህም አለት ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ዓይኖቹን ወደሱ ማንሳት።
◉"ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።"መዝሙር 121፡1-2
➁ኛ. ጎጆ ከቀለሳችሁ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የሚሆነው ኃይለኛ የሆነ ፀሎት መፀለይ ነው።
✔ማለትም በክርስቶስ ውስጥ ገብታችሁ ከተሸሸጋችሁ በኃላ ዮናስ በአሳ ሆድ ውስጥ ሆኖ ያደረገውን ነገር ማድረግ። እርሱም ወደ እግዚአብሔር መመለስ፣ ኃይሉን መለመንና የራሳችሁን ለእግዚአብሔር ማስገዛት።
◉"አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።" ኢዮኤል 2፡12-13
➂ኛ. ይህን ካደረጋችሁ በኋላ የእግዚአብሔር በመተማመን በትዕግስት መጠበቅ።
✔በክርስቶስ ውስጥ ገብታችሁ ከፀለያችሁና ከተመለሳችሁ በኃላ የቀድሞው ኃይሉ እስከመለስ ድረስ በትዕግስት መቆየትና ደጁን መጥናት።
◉"ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።"መዝሙር 40፡1-2
⬛ከእኛ የሚጠበቀው አንድ ነገር ነው። እርሱም እግዚአብሄርን በመተማመን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ ማስተዋሉ የማይመረመረውን እግዚአብሄርን በመጠበቀ ብዙ እናተርፋለን እንጂ የምናጣውና የሚጎድልብን አንዳች ነገር የለም፡፡ በራስህ ትደክማለህ ትካክታለህ፡፡ እግዚአብሔር ሲያድስ ግን ሄደህ ሄደህ አትደክምም፡፡ ሮጠህ ሮጠህ አትታክትም፡፡ የእግዚአብሄር እድሳት ከፍ ያደርግሃል ከሁኔታው ሁሉ በላይ ያወጣሃል፡፡ ስለዚህ በምናደርገው ሁሉ እግዘዚአብሄርን በመተማመን እንጠብቅ፡፡ ለእግዚአብሔር እድሳት ስፍራ እንስጥ፡፡ እግዚአብሄርን በመጠባበቅ እንዲያድሰን እንፍቀድለት፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን!!!

It is a nice revelation .I suggest that it should be provided in pdf format for public.Because it is very empressive lesson
ReplyDelete