መንፈሳዊ አገልግሎት
መንፈሳዊ አገልግሎት
“ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።” 2 ዜና 29፥11
ልጆቼ ሆይ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ፦
✅በፊቱ ትቆሙ ዘንድ
✅ታገለግጉት ዘንድ
✅ታጠኑለት ዘንድ
◆መግቢያ
◈መንፈሳዊ አገልግሎት ከመንፈሳዊ ሕይወት አይበልጥም።
◈አገልግሎት በሕይወት ተጨምቀው የሚወጣው ጁስ ነው።
◈በሕይወታችን ኢየሱስ ማሳየት ቀዳሚ አገልግሎት ነው።
◈ከአገልግሎት በፊት ሰውነትን ሕያውና ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ይቀድማል።
አገልግሎት ምንድነው?
◆አገልግሎት፦ ሌሎችን መረዳት ነው።
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መፈጸም ነው።
እግዚአብሔርና ሰዎችን ማስደሰት ነው።
የተጠራንበት ሁለተኛው ዓላማ መፈጸሚያ ነው።
አገልግሎት በትክክል እንዳናገለግል የሚያደርግ ምክንያት ምንድነው?
◆የአገልግሎት እንቅፋትቸልተኛ መሆን
ጸጋውን አለማወቅ
ኃጢአት
የአገልግሎት ስምሪት ማጣት
አገልግሎት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆን ወይም ትዕግሥት አለመሆን
ሩቅ ያለውን ብድራት ቅርብ አድርጎ ማየት
ብድራት መኖሩን ጭምር አለማወቅ
የእግዚአብሔር መሳሪያ ወይም ትጥቅ ምንድነው?
◆የአገልግሎት ትጥቅ፦የመንፈሳዊ ቅዱስ ኃይል
ጸምና ጸሎት
የእግዚአብሔር ቃል
ቅድስና ሕይወት
የአገልግሎት ሸክም
ለአገልግሎት አቅም እንድኖር የሚያደርግ ምንድነው?
◆የአገልግሎት አቅም፦ቅድስና ጸሎት የእግዚአብሔር ቃል
የአገልግሎት ክብር ምንድነው?
◆የአገልግሎት ክብር፦የእግዚአብሔር መገኘት
የአገልግሎት ማእከል ምንድነው?
◆የአገልግሎት ማእከል፦ኢየሱስ ክርስቶስ
የአገልግሎት Scope እስከየት ነው?
◆የአገልግሎት Scope (መጠን ራዕይ)፦እስከ ዓለም ዳርቻ
የአገልግሎት ፈተና ምንድነው?
◆የአገልግሎት ፈተኛ፦ትዕቢት
ልምምድ፦ የእግዚአብሔርንና አገልግሎትን መለማመድ
ምድራዊ ጥቅምን ማሳደድ
ተቃራኒ ፆታ
ያለመዘጋጀት፦ አለማንበብና አለመጸለይ
አድሎ ወይም ማዳላት
ዘር፣ ጎሳ ፣ አከባቢውነት
የአገልጋይ ባሕርይ ምንድነው?
◆የአገልጋይ ባሕርይ፦ኢየሱስን መምሰል
መታዘዝ
መንፈሳዊ ፍሬ
ትህትና ፍቅር
የአገልግሎት ግብ ምንድነው?
◆የአገልግሎት ግብ፦የነፍሳት መዳን
የእግዚአብሔር መንግስትን ማስፋፋት
የእግዚአብሔር ክብርና ሽልማት ማግኘት
◆ማጠቃለያ፦ ግጥም
ቸል አትበሉ አገልግሎት
ነገር ግን እናስቀድም ከሕይወት
ተግተው ማገልገል ሽልማት ያሰጣል
አለማገልገልም ሽልማት ያሳጣል
እናገልግል ይክበር እግዚአብሔር ይዳን ነፍሳት
አትርሱት አገልግሎት አለው ብድራት
Comments
Post a Comment