#ለኢየሱስ_ሞት_ተገቢውን_ዋጋ_እንስጥ
❖የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ውድ የጓደኞቼ እንኳን
ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። እናንተና እግዚአብሔር በሚተዋወቁበት በየትኛውም ዓይነት ጉዳይ ላይ #ፋስካ_ይሁን እያልኩ አንድ አጭር መልዕክት ላካፍላችሁ።
❖ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ እንስጥ እላለሁ። ይህ በዓል ለእኛ በተለይም ለአማኞች ከበዓል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለውና ዘወትር መታሰብ ያለበት በዓል ነው። ይህ በዓል ለእኛ ለአማኞች ምን ማለት እንደሆነ መናገር እንኳን አያስፈልግም።
የዚህን በዓል ምንነት እኔ መናገር ከሚችለው በላይ በደንብ ታውቁታላችሁ።
❖አሁን ለማንሳት የፈለኩት ዋናው ጉዳይ የዚህን በዓል ምንነት ማወቅ አለማወቅ አይደለም። ዛሬ ሁላችሁንም ለመጠየቅ ያሰብኩት ጥያቄ ለመሆኑ በዓሉን ከማክበርና ከማወቅ ያለፈ ስንቶቻችን ለዚህ በዓል ተገቢውን ዋጋ ሰተን እናውቃለን?
ተገቢውን ዋጋ መስጠት ስባል ምን ማለት ነው?
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
◉በመሰረቱ ለእኛ የተከፈለው ዋጋ በምንም የሚከፈል
አይደለም። ምንም እንኳን ለእኛ የተከፈለውን ዋጋ መክፈል ባንችልም ነገር ግን ለተከፈለው ዋጋ ተገቢውን ዋጋ መሰጠት እንችላለን። ኢየሱስ ክርስቶስም ከእኛ የሚፈልገው ይህንን ነው።
ይህን በትክክል ማድረግ ከቻለን ዋጋውን እንደ መክፈል ይቆጠራል።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መስጠት ስባል በበዓሉ ወቅት በዓሉን ማሰብ፣ በዓሉን ማክበር፣ ምናልባት የሕማማት ሳምንትን በፆምና በፀሎት ማሳለፍ ወይም ደግሞ የተለያዩ በጎ ነገሮችን ማድረግና በበዓሉ መደሰት ማለት አይደለም።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት በንግግር፣ በሃሳብ ወይም ደግሞ በምኞት የሚገለጽ ነገር አይደለም።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት በእለተ እለት ኑሮአችንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በተግባር የሚገለጽ ድርጊት ነው።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት፦
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ መኖር ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው
ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል
ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24
ኢየሱስ ሞታችንን ሞተው ቅዱሳንንና ጻድቃን ካደረገ በኃላ
በኃጢአት መኖር፣ ለኃጢአት ሳንሞት ለጽድቅ ሳንኖር በዓሉን
ማክበር ማለት ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ
አለመስጠት ነው።
በድጋሚ ለኃጢአት አለመግዛት ወይም በባርነት ቀንበር
አለመያዝ ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ
ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ
እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።” ሮሜ 6፥6
በኃጢአታችንና በበደላችን ምክንያት ሙታን የነበረውን
የእኛን ማንነትን በመስቀል ሞተው ከኃጢአታችንና ከበደላችን
ንጹሃን ካደረገ በኃላ ድጋሚ በኃጢአት መገዛት ወይም ድጋሚ
በባርነት ቀንበር መያዝ ወይም የኃጢአት ባሪያ መሆን ለኢየሱስ
ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት ነው።
ሥጋችንን ከክፉ መሻቱና ከክፉ ምኞቱ ጋር መስቀል ማለት
ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ
ጋር ሰቀሉ።” ገላትያ 5፥24
ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን፣ ትንሣኤውን
በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር ከተባብረን በኃላ
የሥጋችንንና የምኞታችንን ፍቃድ እየፈፀመን በሥጋ መመላለስ
የሥጋችንንና የፍቃዳችንን መሻትና ምኞትን አለመስቀል ለኢየሱስ
ክርስቶስ መስቀል ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት ነው።
ፊተኛ ኑሮአችን አለማሰብና አሮጌውን ሰውነታችን ማስወገድ
ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት
የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ ኤፌሶን 4፥22
በክርስቶስ ሞት አድስ ሰው ከሆንን በኃላ በድጋሚ አሮጌውን
ሰውነታችን ይዘን መቀጠልና ትላንት ትተን የመጣነውን የፊተኛው
ኑሮአችን ማሰብ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ
አለመስጠት ነው።
በላይ ያለውን መሻትና ማሰብ ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ
በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፤ በላይ
ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ
3፥1-2
በላይ ያለውን አለመሻትና አለማሰብ ከዚህ ይልቅ ግን
በምድር ያለውን መሻት ወይም ደግሞ በምድር ያለውን ማሰብ
ለኢየሱስ ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት ነው።
በምድር ያሉትን ብልቶቻችን መግደል ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም
ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ
የሆነ መጎምጀት ነው፤” ቆላስይስ 3፥5
በምድር ያሉትን ብልቶቻችን በሕይወታችን ተሸክመን
ባልሞተ፣ ባልተቀደሰና ሕያው ባልሆነ ሰውነታችን ይህን በዓል
ማክበር ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት
ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ መሞትን በሥጋችን ተሸክመን መዞር
ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ
የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። 2ኛ ቆሮ
4፥10
የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ማለትም ስቃዩን፣ መከራውን፣
ስደቱን፣ መራቡን፣ መጠማቱን፣ ፍቅሩን፣ ትዕግሥቱን፣ ወዘተን
በሕይወታችን እያሳየን ክርስቶስን በሚመስል ሕይወት መመላለስ
ማለት ነው።
❖የእውነት የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በእኛ ሕይወት ተገቢውን
ዋጋ አግኝቷል? ወገኖች ራሳችንን መጠየቅ አለብን።
❖ ይህ ጉዳይ ማለትም የኢየሱስ የመስቀሉ ሞት በእኛ ሕይወት
ላይ ተገቢውን ቦታ ካለገኘበጣም ከባድ ችግር
ውስጥ መሆናችን መታወቅ አለበት።
❖ከላይ በኩል የተጠቀሱት በእኛ ሕይወት ከሌሉ የኢየሱስ
ክርስቶስን ሞት ማወቅና በዓሉን ማክበር ምንም ፈይዳ
የለውም።
❖ዛሬ ሁላችን ቆም ብለን ራሳችን እንይ።
➥◈◈◈◈◈◈ ጌታ ይርዳን
ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። እናንተና እግዚአብሔር በሚተዋወቁበት በየትኛውም ዓይነት ጉዳይ ላይ #ፋስካ_ይሁን እያልኩ አንድ አጭር መልዕክት ላካፍላችሁ።
❖ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ እንስጥ እላለሁ። ይህ በዓል ለእኛ በተለይም ለአማኞች ከበዓል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለውና ዘወትር መታሰብ ያለበት በዓል ነው። ይህ በዓል ለእኛ ለአማኞች ምን ማለት እንደሆነ መናገር እንኳን አያስፈልግም።
የዚህን በዓል ምንነት እኔ መናገር ከሚችለው በላይ በደንብ ታውቁታላችሁ።
❖አሁን ለማንሳት የፈለኩት ዋናው ጉዳይ የዚህን በዓል ምንነት ማወቅ አለማወቅ አይደለም። ዛሬ ሁላችሁንም ለመጠየቅ ያሰብኩት ጥያቄ ለመሆኑ በዓሉን ከማክበርና ከማወቅ ያለፈ ስንቶቻችን ለዚህ በዓል ተገቢውን ዋጋ ሰተን እናውቃለን?
ተገቢውን ዋጋ መስጠት ስባል ምን ማለት ነው?
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
◉በመሰረቱ ለእኛ የተከፈለው ዋጋ በምንም የሚከፈል
አይደለም። ምንም እንኳን ለእኛ የተከፈለውን ዋጋ መክፈል ባንችልም ነገር ግን ለተከፈለው ዋጋ ተገቢውን ዋጋ መሰጠት እንችላለን። ኢየሱስ ክርስቶስም ከእኛ የሚፈልገው ይህንን ነው።
ይህን በትክክል ማድረግ ከቻለን ዋጋውን እንደ መክፈል ይቆጠራል።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መስጠት ስባል በበዓሉ ወቅት በዓሉን ማሰብ፣ በዓሉን ማክበር፣ ምናልባት የሕማማት ሳምንትን በፆምና በፀሎት ማሳለፍ ወይም ደግሞ የተለያዩ በጎ ነገሮችን ማድረግና በበዓሉ መደሰት ማለት አይደለም።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት በንግግር፣ በሃሳብ ወይም ደግሞ በምኞት የሚገለጽ ነገር አይደለም።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት በእለተ እለት ኑሮአችንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በተግባር የሚገለጽ ድርጊት ነው።
◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት፦
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ መኖር ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው
ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል
ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24
ኢየሱስ ሞታችንን ሞተው ቅዱሳንንና ጻድቃን ካደረገ በኃላ
በኃጢአት መኖር፣ ለኃጢአት ሳንሞት ለጽድቅ ሳንኖር በዓሉን
ማክበር ማለት ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ
አለመስጠት ነው።
በድጋሚ ለኃጢአት አለመግዛት ወይም በባርነት ቀንበር
አለመያዝ ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ
ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ
እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።” ሮሜ 6፥6
በኃጢአታችንና በበደላችን ምክንያት ሙታን የነበረውን
የእኛን ማንነትን በመስቀል ሞተው ከኃጢአታችንና ከበደላችን
ንጹሃን ካደረገ በኃላ ድጋሚ በኃጢአት መገዛት ወይም ድጋሚ
በባርነት ቀንበር መያዝ ወይም የኃጢአት ባሪያ መሆን ለኢየሱስ
ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት ነው።
ሥጋችንን ከክፉ መሻቱና ከክፉ ምኞቱ ጋር መስቀል ማለት
ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ
ጋር ሰቀሉ።” ገላትያ 5፥24
ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን፣ ትንሣኤውን
በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር ከተባብረን በኃላ
የሥጋችንንና የምኞታችንን ፍቃድ እየፈፀመን በሥጋ መመላለስ
የሥጋችንንና የፍቃዳችንን መሻትና ምኞትን አለመስቀል ለኢየሱስ
ክርስቶስ መስቀል ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት ነው።
ፊተኛ ኑሮአችን አለማሰብና አሮጌውን ሰውነታችን ማስወገድ
ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት
የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ ኤፌሶን 4፥22
በክርስቶስ ሞት አድስ ሰው ከሆንን በኃላ በድጋሚ አሮጌውን
ሰውነታችን ይዘን መቀጠልና ትላንት ትተን የመጣነውን የፊተኛው
ኑሮአችን ማሰብ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ
አለመስጠት ነው።
በላይ ያለውን መሻትና ማሰብ ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ
በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፤ በላይ
ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ
3፥1-2
በላይ ያለውን አለመሻትና አለማሰብ ከዚህ ይልቅ ግን
በምድር ያለውን መሻት ወይም ደግሞ በምድር ያለውን ማሰብ
ለኢየሱስ ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት ነው።
በምድር ያሉትን ብልቶቻችን መግደል ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም
ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ
የሆነ መጎምጀት ነው፤” ቆላስይስ 3፥5
በምድር ያሉትን ብልቶቻችን በሕይወታችን ተሸክመን
ባልሞተ፣ ባልተቀደሰና ሕያው ባልሆነ ሰውነታችን ይህን በዓል
ማክበር ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት
ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ መሞትን በሥጋችን ተሸክመን መዞር
ማለት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➥የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ
የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። 2ኛ ቆሮ
4፥10
የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ማለትም ስቃዩን፣ መከራውን፣
ስደቱን፣ መራቡን፣ መጠማቱን፣ ፍቅሩን፣ ትዕግሥቱን፣ ወዘተን
በሕይወታችን እያሳየን ክርስቶስን በሚመስል ሕይወት መመላለስ
ማለት ነው።
❖የእውነት የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በእኛ ሕይወት ተገቢውን
ዋጋ አግኝቷል? ወገኖች ራሳችንን መጠየቅ አለብን።
❖ ይህ ጉዳይ ማለትም የኢየሱስ የመስቀሉ ሞት በእኛ ሕይወት
ላይ ተገቢውን ቦታ ካለገኘ
ውስጥ መሆናችን መታወቅ አለበት።
❖ከላይ በኩል የተጠቀሱት በእኛ ሕይወት ከሌሉ የኢየሱስ
ክርስቶስን ሞት ማወቅና በዓሉን ማክበር ምንም ፈይዳ
የለውም።
❖ዛሬ ሁላችን ቆም ብለን ራሳችን እንይ።
➥◈◈◈◈◈◈ ጌታ ይርዳን

- ለኢየሱስ ሞት ተገቢውን ዋጋ እንስጥ።◈◈◈◈◈◈◈
Comments
Post a Comment