የዛሬ ዮናስ ማነው?
★የሰው ልጅ ለሚዘራው ለየትኛውም ዓይነት ዘር በስተመጨረሻ የሚታጨድ የራሱ የሆነ ፍሬ እንዳለው ሁሉ ሰው ለሚሠራው ለየትኛውም ዓይነት ሥራም (ክፉ ይሁን ደግ) የሚተርፍ ወይም የሚደርስ የራሱ የሆነ ውጤት ወይም ዋጋ አለው።
★እዚህ ጋ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ድርጊቱ ወይም ሥራው የአንድ ግለሰብ ብሆንም የሥራው ውጤቱ ወይም ዋጋው የሚተርፈው ግን ለብዙዎች ነው። በአንድ ሰው ሥራ ምክንያት የሚመጣ የትኛውም ዓይነት መልካም ይሁን ክፉ ነገር የሚተርፈው ለአንድ ግለሰብ ወይም ለባለቤቱ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ጭምር ነው።
▦የእግዚአብሔር ቃል በዘጸአት 20፡5-6 ላይ ይህን እውነት ይይናገራል። "በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።"
★በሌላ ቦታ ደግሞ ለኃጢአተኞች የመጣ ቁጣ ለጻድቃንም እንደምተርፍ የእግዚአብሔርም ቃል ይናገራል። አው ለኃጢአተኞች የመጣ ቁጣ ለጻድቃንም ይተርፋል። ይህን ከእግዚአብሔር ቃል ማየት እንችላለን። ለምሳሌ፦
●አሁን በምድራችን በተከሰተው በከሮና ቫይረስ ምክንያት እስካሁን ብቻ ባለን መረጃ ማለትም እስከ 08/08/12 ድረስ ከ2,088,240 በላይ ሰው በበሽታ ተይዟል። በዚህ በሽታ የሞተው የሰው ብዛት ደግሞ ከ134,720 በላይ ነው። እነዚህ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ናቸው? በፍጹም አይደሉም። ይህ ሌሎች ሰዎች የዘሩት የዘር ውጤት ነው።
●በመሪ በኢያሱ ዘመን በአካን ምክንያት ታላቅ የኢስራኤል ስራዊት በትንሿ በጋይም ሰዎች ተመቱ። ኢያሱ 7፥5
✅እንደ ሕግ ከሆነ ኃጢአት የሰራው መሞትም ያለበት አካን ነበረ ነገር ግን የተመቱትና የሞቱት ሠላሳ ስድስት ንጹሃን ሰራዊቶች ናቸው።
●በንጉሥ ዳዊት ዘመን በእርሱ ምክንያት በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን ብቻ ሰባ ሺህ ሰዎች ከእስራኤልም ወደቁ። 1 ዜና 21፥14
✅በዳዊት ምክንያት የመጣ የእግዚአብሔር ቁጣ (ቸነፈር) በአንድ ቀን ብቻ ሰባ ሺህ ሰዎችን ገደለ። እግዚአብሔርን የበደለው ኃጢአትን የሠራው ዳዊት ነገር ግን የሞተው ንጹሕ የሆነው ሕዝብ። ለምን? ሰባ ሺህ ንጹሕ ሕዝቡን ከመግደል ይልቅ ኃጢአተኛውን አንዱን ዳዊት መግደል አይሻልም? አው በሰው አመለካከት እጅግ በጣም ይሻላል። ነገር ግን ዳዊት የዘራው የዘሩ ውጤት ነው የበቀለው።
●በነቢዩ በዮናስ ዘመን በእርሱ ምክንያት በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስንና ማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች ሰዎችም እጅግ ተጨነቁ። ዮናስ 1፥4
✅በዮናስ ድርጊት እግዚአብሔር በዮናስ ላይ ተቆጣ፥ በመርከቡ ላይ ታላቅ ማዕበልና ነፋስን አመጣ፥ መርከቧ ልትሰበር ቀርበች። እግዚአብሔርን የበደለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ባለመታዘዝ በራሱ ፍቃድ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ዋጋ ከፍሎ ወደ መርከብ የገባው ዮናስ ነው። ነገር ግን በመርከቧ ላይ ማዕበሉና ነፋሱ የተነሳው ለሁሉም ነው። ዛሬ እኛም ለምናደርገው ለእያንዳንዱ ነገር የራሱ የሆነ ውጤት አለውና እያንዳንዱ ነገርን ስናደርግ በጥንቃቄና ኃላፍነት በሞላበት ሁኔታ የነገን ትውልድንና ሀገርን በማሰብ እንድናደርግ ቃሉ ያስተምረናል።
#አሁን_በምድራችን_ላይ_የተነሳው_ለታላቅ_ማዕበልና_ንፋስ_ምነድነው?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
★አሁን ሁላችን እንደምናውቀው በምድራችን ላይ ይህ ነው የማይባል ብዙ ዓይነት ታላቅ ማዕበልና ንፋስ ተነስቷል። በዚህም ምክንያት ምድራችን እየተናወጠች ነው። አሁን በምድራችን ከተነሳው ማዕበልና ንፋስ መካከል አንዱ ኮሮና ቫይረስ ነው። የአሁን መናወጥ መርከቧን (ምድርቷን) መስበር የሚችል አደገኛ ነገር ነው። ምክንያቱም በመርከቧ ላይ የተነሳው ማዕበልና ንፋስ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ወረርሽኝ ነው። በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት የብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን አልፎአል። ከዚህም ባልተናነሰ መልክ ከኢኮኖሚ የተነሳ የብዙ ሰዎች ሕይወት አደጋ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ችግር በቅርቡ እልባት ካለገኘ ዓላማ ወደ የማትወጣበት አዘቅት ውስጥ ትገባለች። ለነገሩ አሁን እየገባች ነው። ከዚህ አዘቅት ለመውጣት ብዙ ዓመታትን የሚፈጅ ነው። ይህም ከተሳካ ብቻ ነው። ይህ ወረርሽኝ ከዚህ ያለፈ በብዙ አቅጣጫ በዓለም ላይ እጅግ በጣም ከባድ ተፅዕኖውን እያስከተለ ነው።
#አሁን_በምድራችን_ላይ_ለተነሳው_ለታላቅ_ማዕበልና_ንፋስ_ተጠያቂ_ማነው?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
★በእርግጥም በምድራችን ላይ የተነሳው ማዕበልና ንፋስ እጅግ በጣም ኃይለኛ ነው። ይህም ሁኔታ እጅግ በጣም የሚያስፈራ ነው። ነገር ግን አሁን ላይ ከዚህ ማዕበልና ንፋስ በበለጠ ሁኔታ እጅግ በጣም የሚያስፈራው ለዚህ ችግር ኃላፍነቱን የሚወስድ ወይም ተጠያቂ የሚሆን ሰው መጥፋቱ ነው። ይህ ሰው እስካልተገኘ ድረስ ማዕበሉና ንፋሱ ይጨምራል እንጅ በፍጹም አይቀነስም።
●ታዲያ አሁን በዓለማችን እንዲሁ በአገራችን ለተነሳው ማዕበልና ንፋስ ማነው ተጠያቂ?
★የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ እንደምናገር በመርከቧ ላይ ለተነሳው ማዕበልና ንፋስ ዋና ተጠያቂ ነቢዩ ዮናስ ነው። ነገር ግን እጅግ በጣም የሚገርመው ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት የሆነ ነቢዩ ዮናስ በከባድ እንቅልፍ መተኛት ነው። “እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፥ በባሕርም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች። መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።” ዮናስ 1፥4-5
✅ዛሬም በዚህ ጊዜ ከሁሉ በላይ እጅግ በጣም የሚያሳዝነውና የሚያስፈራው ይህ ሁኔታ ነው።
★በማዕበልና በንፋስ ምከንያት መርከቧ ልትሰበር ቀርባለች። ልክ እንደ አሁን ጊዜ ሰዎች ሁሉ ከፍርሃት የተነሳ እያንዳንዱ ወደ አምላካቸው እየጮኹ ነው። ሌላው ደግሞ አሁን በእኛ ጊዜ ወረርሽኙን ለመከላከል ብለን የተለያዩ ነገሮች እንደሚናደርግ ሁሉ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ያኔም ሰዎች መርከቢቱ እንድትቀልልላቸው በማለት ሰዎች የራሳቸው ንበረት እየጣሉ ብዙ ነገር አጡ፣ ብዙዎች ከሰሩ። ልክ እንደ እኛ ማለት ነው።
✅ይህ ሁሉ ስሆን ግን (ከላይ በኩል ያየነው) ለዚህ ችግር ዋና ምክንያት የሆነው ነቢዩ ዮናስ በመርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር። (ዮናስ 1፥4-5)
◉ ልክ እንደ ነቢዩ ዮናስ አሁን በምድራችን ላይ ለተነሳው ማዕበልና ንፋስ ዋና ተዋናይ የሆኑ አራት አካላቶች አሉት።
★እነዚህ አካላቶች ያንቀላፉ ለዛውም ከባድ እንቅልፍ የተኙ፣ ንሰሐ የማይገቡ፣ ከክፉ መንገዳቸው የማይመለሱ፣ ድምፁን የማይሰሙ፣ ተግሣጽን የማይቀበሉ፣ በእግዚአብሔር የማይታመኑ፣ እግዚአብሔርን የማይፈልጉና የማይጠይቁ፣ ወደ እግዚአብሔር የማይመለሱ፣ ዛሬም አንገታቸውን ደንዳና አድርጎ የሚሄዱ፣ ይህ ሁሉ ነገር በምድራችን ስሆን እንኳን ምንም የማይመስላቸው ሰዎች ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ ለምድራችን ትልቁ ኮሮና እነዚህ ሰዎች ናቸው እንጂ የቫይረሱ ኮሮና አይደለም።
▣እነዚህ አራት አካላቶች እነማናቸው?
#አራት_አካላቶች፦ ት/ሶፎንያስ 3፡4-5
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
❶.አለቆች ናቸው።
===========
▪አለቆች ለዚህ ማዕበልና ንፋስ ዋነኛ ተዋንያን ናቸው።
▪እነዚህ አለቆች ከታች ከቀበሌ እስከ ፈደራል ደረጃ ድረስ በስልጣን ያሉ መሪዎች ናቸው።
▪እነዚህ አለቆች እንደ አንበሳ ከእኔ በላይ ሌላ የለም የሚሉ እግዚአብሔር በሰጠው ወንበር ላይ ተቀምጦ እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ናቸው።
▪እዚህ አለቆች ስስታሞችና ነፍስ ገዳዮች ናቸው።
✅“በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።” ሕዝቅኤል 22፥27
▪እነዚህ አለቆች ሕዝብን የሚበዘብዙ፣ ግፍን የሚሰሩ፣ፍርድን የማያድርጉ ክፉ አለቆች ናቸው።
✅የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” ሕዝቅኤል 45፥9
❷.ፈራጆች ናቸው።
==========
▪ከአለቆች ቀጥሎ ለዚህ ማዕበልና ንፋስ ዋነኛ ተዋንያን ፈራጆች ናቸው።
▪እነዚህ ፈራጆች የፍርድ ቤት ዳኞች፣ ጠበቃዎች፣ የሀገርና የአከባቢው ሽሽማግልዎች ናቸው።
▪እነዚህ ፈራጆች ተኩላ የሆኑ ለገንዘብ ብሎ ፍርድን የሚያጣምሙ ሰዎችንም ጭምር የሚገድሉና የሚያስገድሉ የብዙ ሰዎች እንባ ባለቤት ናቸው።
▪እነዚህ ፈራጆች ውሸታሞች ለገንዘብ ብሎ እውነትን በሐሰት የሚቀይሩ ከእውነት ጋር የተጣሉ ክፉዎች ናቸው።
❸.ነቢያቶች ናቸው።
===========
▪በሦስተኛ ደረጃ ለዚህ ማዕበልና ንፋስ ዋነኛ ተዋንያንን ነቢያቶች ናቸው።
▪እነዚህ ነቢያት ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው። ት/ሶፎ 3፡5
▪እነዚህ ነቢያት ቀበሮዎች፣ ውሸታሞችና ምዋርተኞች ናቸው።
“እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።” ሕዝቅኤል 22፥28
▪እነዚህ ነቢያት ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከገዛ ሥጋቸውንና ከገዛ ስሜታቸው የሚናገሩ አታላዮች ናቸው።
✅የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።” ኤርምያስ 23፡13-16
✅በሰማርያ ነቢያት ላይ ስንፍናን አይቻለሁ፤ በበኣል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤል ያስቱ ነበር።
▪እነዚህ ነቢያት አመንዝራ ነቢያቶች ናቸው።
✅ በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
❹.ካህናቶች ናቸው።
==========
▪በስተመጨረሻ ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂዎች ካህናቶች ናቸው።
▪እነዚህ ካህናቶች ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርጎ የተቀበሉ ሁሉ ናቸው።
▪እነዚህ ካህናቶች መጋቢያን፣ ወንጌላውያን፣ ዘማሪያን እና ሌሎች ናቸው።
▪እነዚህ ካህናቶች መቅደሱን (ሰውነታቸውን) ያረክሱ፣ ሕግን የተላለፉ፣ በእግዚአብሔር በሕግም ላይ ግፍ የሰሩ አመፀኞች ናቸው። ት/ሶፎ 3፡5
✅“ካህናቶችዋም ሕጌን በድለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል፤ ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አልለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም ዓይናቸውንም ከሰንበታቴ ሰወሩ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።” ሕዝቅኤል 22፥26
★ነቢዩን ዮናስን ስንመለከት ምንም እንኳን ያንቀላፋ ብሆንም በመርከቡ አለቃ አማካኝነት ከእንቅልፍ ከተነሳና ዕጣውም በእርሱ ላይ ከወደቀ በኃላ አንድ መልካም ነገርን አደረገ። ለችግሩ ዋናው ምክንያት እርሱ እንደ ሆነ አንድም ነገር ሳይደብቅ ራሱንም ገለፀ። “እርሱም፦ ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው።” ዮናስ 1፥12።
★እንደተባለውም ዮናስን አውጥቶ በውኃ ውስጥ ጣሉት። ከዚህም በኃላ ማዕበልም ንፋሱም ፀጥ አለ። “ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ።” ዮናስ 1፥15
✅ነቢዩ ዮናስ ወዲያውኑም ማዕበሉና ንፋሱን ፀጥ ማድረግ ባይችልም ነገር ግን መርከቧን ከመሰበር አድኗል። እነዚህም ከላይ ያየናቸው አራቱ አካላቶች ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ የጠፋውን የሰውን ነፍሰ ማዳን ባይችሉም፣ እስካሁን ድረስ የጠፋውን ኢኮኖሚን ማምጣት ባይችሉም ነገር ግን ምድርቷን ከስብራት ማዳን ይቻላሉ። ነገር ግን ይህ የሚሆነው ማዕበሉና ንፋሱን ማስቆም ከቻሉ ብቻ ነው።
#ይህን_ማዕበልና_ንፋሱን_ማን_ያስቆማል?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
★አሁን በምድራችን ላይ የተነሳውን ይህን ታላቅ ማዕበልና ንፋስን ማስቆም የሚችል ሰው ማነው? ብባል ይህ ችግር እንዲፈጠር ምክንያት የሆነ ዮናስ ነው። የዛሬ ዮናስ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ትተን በራሳችን ፍቃድ የሄዴን፣ እግዚአብሔርን ከማምለክ የተመለስን፣ ኃጢአትን የሠራን እኔና እናንተ ነኝ።
★አሁን የተነሳውን ማዕበልና ንፋስን ማስቆም ማለትም ይህን ወረርሽኝ ከምድራችን ማንሳት የሚችል ሰው ዮናስ ሆነው ነገር ግን፦
✅ለዚህ ክስተት ኃላፍነቱን የሚወስድ፣ ራሱን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ ይህ የሆነው በእኔ ምክንያት ነው የሚል፣ የሌላውን ጉድፍን ማየትን ትቶ የራሱን ምሶሶ የሚያይ፣ እኔ ነኝ ኃጢአተኛውን ብሎ በእግዚአብሔር ፍት የሚወድቅ በፍጹም ልብ ንሰሐ የሚገባና የሚመለስ ሰው።
✅ይህ ሰው ነው ለምድርቷ እረፍትን ማምጣት ወይም ማሳረፍ የሚችል። እኔ ይህን አደርጋለሁ የሚል፣ ለዚህች ምድር የእረፍት ምክንያት እሆናለሁ የሚል ጀግና ማነው? ይህን ዓለም ለማሳረፍ ማለትም አሁን በዓለም ላይ የተነሳውን ማዕበልና ንፋስን ማስቆም የሚችል አንድ ዮናስ በቂ ነው። ምናልባት ያ ዮናስ አናንተ ልትሆኑ ትችላላችሁ።

እግዚአብሔር ሆይ ዮናስ እኔ ነኝ
ReplyDeleteእባክህ ማረን