ዘወትር በሕይወታችን እሳት ይንደድ


#ዘወትር_ከሕይወታችን_እሳት_አይጥፋ
☞እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ የሚቃጠለው የመሥዋዕቱ ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ ባለው እንጨት ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስኪጸባ ድረስ ይሆናል፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፡፡ ካህኑም የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ በሥጋው ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል። ልብሱንም ያወልቃል፥ ሌላም ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ተሸክሞ ከሰፈሩ ንጹሕ ስፍራ ወደ ሆነ ወደ ውጭ ያወጣዋል። እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል። ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም። ዘሌዋውያን 6፡8-13
✍ከዚህ ክፍል በደንብ ማየት የሚንችለው አንድ ነገር አለ፡፡ በዚህ ቦታ ብቻ ትኩረት ተሰቶ ሦስት ጊዜ ያህል ተደጋግመው ተገልጿል፡፡ ይህም  እግዚአብሔር ለሕዝብ ደጋግመው አፅንኦት ሰቶ የተናገረው ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ጉዳይ ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነደድ አይጥፋ የሚል ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሕዝብ የሚፈልገው ነገር ብኖር አንዱ ከመሠዊያ እሳት እንዳይጠፋ ነው፡፡
✍ይህን ያህል እግዚአብሔር አፅንኦት ሰተው የተናገረበት ትልቁ ምክንያት
➊ እርሱ ራሱ እሳት ስለሆነ ሕዝቡም ማኝነቱን አውቋት እንድያመልኩት፡፡
“አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።”  ዘዳግም 4፥24
“አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።”  ዕብራውያን 12፥29
➋ ከእርሱ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለሆነ ሕዝቡ ትዕዛዙን እንድጠብቅ፡፡
“ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም።” ዘሌዋውያን 6፥13
➌ እርሱ ቅዱስ አምልካ ስለሆነ መሰዊያው ሁለ ንፁና ቅዱስ እንድሆን ስለምፈልግ
17 ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። ለምን ካላችሁ?? ምክንያቱም ²³ ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ዘሌዋውያን 21፡17፣ 23
✍እግዚአብሔር ራሱ እሳት ስለሆነ ከሰው ሕይወት እሳት እንድጠፋ አይፈልግም፡፡ ከአንድ ሰው ሕይወት እሳት ከጠፋ መሠዊያው ይረክሳል፣ ክብሩን ያጣል፡፡ በመሠዊያው እሳት ከሌለ ብዙ ነገር ይቀመጥና መሠዊያውን ያበላሻል፡፡
✍እሳት፦is a manifestation of God himself (እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ማለት ነው) በለላ በኩል ደግሞ God’s Presence (የእግዚአብሔር ህልውና ወይም መገኘቱን ያሳያል)፡፡
_______________________________________________________________________
በአንድ ክርስቲያን ሕይወት ወስጥ የአሳቱ እየጠፋ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች፦
_______________________________________________________________________
1) ለመንፈሳዊ ነገሮች ፍላጎት ማጣት/ Loss of spiritual appetite
✍እንድ ሰው በphysically ስታመም ወይም በበሽታ ስጠቃ ቀድሞ የነበረው የምግብ ፍላጎት በጣም ይወርዳል ወይም ይቀንሳል፡፡ እጅግ በጣም የሚገርመው ያው ሰው  በጠንኝነት ጊዜ ለመብላት በጣም የሚወደው ምግብ ጭምር በታመመ ጊዜ መብላት አይፈልግም እንድሁም በጣም ይጠላል፤ ለላው ቀርቶ የምግቡ ሽታው ጭምር ያስጠላል፡፡ ሰውዬው ምግቡን ለመብላት ይፈልጋል ነገር ግን አይችልም ፡፡ እንዳይበላ የሚያደርገው ደግሞ ምግቡ ወይም ሰውዬው ተቀይሮ ሳይሆን በውስጡ የገባውና ያለው በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ እስካልተወገደ ድረስ ምግቡን በደንብ መመገብ አይችልም፣ መመገብ ብችልም እንኳን ያለ ፍላጎት ላለመሞት ዝንብሎ ይበላል እንጅ ደስታ የለውም፡፡
✍ልክ እንደዚህ ሁሉ አንድ ክርስቲያን spiritually ስታመም ወይም በመንፈሳዊ በሽታ ስጠቃ ከላይ እንዳየነው ተመሳሳይ ዓይነት ችግር ይፈጠራል፡፡ በዋነኝነት ይህ ችግር ስፈጠረ፦ ሐይወታችን በመንፈሳዊ ምግብ ለመመገብ ያለውን ፍላጎት ያጣል፣ መንፈሳዊ Appetite ይዘጋል፡፡ አንድ ሰው ጠናማ ሆነው ለመኖር የተመጣጠነ ምግብ እንደሚያስፈልግ ሁሉ አንድም አማኝ በመንፈሳዊ ሕይወት ጠናማ ሆነው ለመኖር የተመጣጠነ ምግብ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ከእግዚአብሔር ቃል፣ ከፀሎት፣ ከአምልኮ፣ ወ.ዘ.ተ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው አንድ ምግብ ዓይነት ለምሳሌ ሁሉ Carbohydrate ብቻ ከተመገበ ይህ ሰው ብዙ ዓይነት ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ የተመጣጠነ ምግብ ማለትም  ከfat፣ ከprotin፣ ከvitamin፣ ከcarbhydrate አነስ በዛ ካላገነ በጣም መጥፎ ነው፡፡ በብዙ ዓይነት በሽታ ይጠቃል፡፡ ልክ እንደዚህ አንድ አማኝ የተመጣጠነ ነገር ካለገነ በብዙ ዓይነት በመንፈሳዊ በሽታ ይጠቃል፡፡ አንድ ዘማሪ ሁል ጊዜ መዘመር  ብቻ የሚወድ ነገር ግን ፀሎትን የሚጠላ ከሆነ፤ በእግዚአብሔርን ቃል ጊዜ እንቅልፍና ድካም የሚመጣ ከሆነ ምንም መገለጥ ሳይስፈልግ ይህ ሰው ጠናማ አይደለም የሆነ ክፍሉ ታሟል ማለት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቃል፣ ለፀሎት ፣ ለአምልኮ ያለው ፍላጎት እየቀነሰና እየወረደ ከሄድ እሳቱም አብሮ እየቀነሰ  እየጠፋ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ በቶሎ ተክሞ በሽታውን ማስወገድ አለበት፡፡
2) የመንፈሳዊ ተሳትፎ/እንቅስቃሰ ማጣት / Loss of spiritual participation
✍እሳት ባለበት ቦታ ሁሉ ላይ ሙቀት አለ እንቅስቃሰ አለ፡፡ እሳት በተፈጥሮ የማቃጠል ባህር ስላለው አለመንቀሳቀስ አይቻልም ምክንያቱም በውስጡ የገባው እሳት አያስቀምጥም፡፡ አንድ ሰው በአምልኮ፣ በፀሎት፣ ወይም በbible study ጊዜ ወስጡ ካልተቀጣጠለ፣ ካልሞቀ፣ ከቀዘቀዘና ከበረደ ፣ ምንም ዓይነት እንቅስቃሰ/ ስሜት ከጠፋ ለላ ምንም ነገር ሳይሆን እሳቱን ደፈኗል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቶሎ ከመሠዊያው አመዱን አስወግዶ አድሱን አሳት መለኮስ አለበት፡፡
3) የመንፈሳዊ ኃይል/አቅም ማጠት/Loss of spiritual energy
✍መቼም ብሆን፣ ምንም ብሆን ለእሳት ኃይል አለው ምንም እንኳን ትንሽ ብሆንም፡፡  እሳት በውስጡ ያለው አማኝም እንደዛው ኃይለኛ ነው፡፡ በተቀራኒ ደግሞ እሳት የለላው ወይም እሳቱን ያጠፋ አማኝ ደካማ ነው፡፡ ያመልካል፣ ይፀልያል፣ ይዘምራል ነገር ግን አቅም የለውም ምክንያቱም ምንም ኃይል/ እሳት የለውም፡፡ አቅም በውስጡ ካለመኖሩ የተነሳ ሁል ጊዜ ድካም፣ ስንፍናና ስልችት አለ፡፡ ዛሬ በእኛ ሕይወት እያንፀባረቀ ያለው ድካም፣ ስንፍናና ስልችት ከየትም የመጣ ሳይሆን ከኃይል ወይም እሳት ከማጣት የመጣ ነው፡፡ ፀሎትና አምልኮ የሚያስጠላ ነገር ግን ወሬና ቀልድ የሚያምር ከሆነ በውስጣችን የሞላው ኃይል የለላ ኃይል ነው፡፡ ራሳችን እንፈትሽ ይህ ምልዕክት የእሳቱ መጥፋት ምልክት ነው፡፡
_____________________________________________________________________
በአንድ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ እሳቱ እንድጠፋ የሚያደርጉ ምክንያቶች፦
_____________________________________________________________________
1) ትክክለኛ የሆነ የነዳጃ አቅራቦት/የሚያቀጣጥል ነገር ማጣት ነው፡፡
✿ይህ መብራት እያበራ እንድቀጥል ውኃ ያስፈልጋል፡፡ ውኃ ከለለ መብራት የለም፡፡
✿ኩራዝ እያበራ እንድቀጥል ናፍጣ/gas  ያስፈልጋል፡፡ ናፍጣ ከለለ ብርሃን የለም፡፡
✿ተንቀሳቃሽ ሁሉ እንቀሳቀስ ነዳጅ ያስፈልጋል፡፡ ነዳጅ ከለለ የትም መጓዝ አይችልም፡፡
✿እሳትም እየነደደ እንድቀጥል እንጨት ያስፈልጋል፡፡ እንጨት ከለለ እሳት የለም፡፡
✿የመንፈሳዊ እሳትም እንድነድ መንፈሳዊ ነዳጅ፣ መንፈሳዊ እንጨት ያስፈልጋል፡፡
✍እሳት ባለማቋረጥ ሁል ጊዜ እንድነድ ከተፈለገ፦ 1. እሳት 2. እንጨት 3. እሳቱን የሚያቀጣጥል ሰው ያስፈልጋል፡፡ እሳቱ ቀጣይነት እንድኖር እሳትን የሚያነድ በቅ የሆነ ነዳጅ ያስፈልጋል ወይም ደግሞ ጥሩ የሆነ እንጨት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ በክብርት ላይ እሳት አለ ነገር ግን ይህ እሳት በራሱ አይነድም ለላ ነገር ያስፈልጋል፡፡ እሳት እሳት ሆነው የሚጠቀምው እንጨት/ ነዳጅ ወይም ለላ የሚያቀጣጥል ነገር መኖር አለበት፡፡
✍ልክ እንደዚህ መንፈሳዊ እሳትም እንድነድና ተቀጣጥለው እንድቀጥል መንፈሳዊ ነዳጅ/ እንጨት አስፈላጊ ነው፡፡ እንዚህ መንፈሳዊ ነዳጅ ወይም እንጨት የሚባሉት መንፈሳዊ ምግቦች ናቸው፡፡ ለምሳሌ Bible . እንድ እጾዋት/plant ለማደግ በቅ የሆነ ንጥረ ነገርና ውኃ እንደምያስፈልግ ሁሉ አንድ ክርስቲያንም ሁሉ ጊዜ መንፈሳዊ ምግብን ማለትም ሁለ ቃሉን ማንበብን ማዘወተር አለበት፡፡ ሁለ ቃል ስያነብ በውስጡ እሳቱ ይቀጣጠላል፡፡ ይህ የገባው የእግዚአብሔር ቃል እንደ ነዳጅ ያገለግላል፡፡
2) በቅ የሆነ የመንፈሳዊ አየር ማጣት
✍ለእሳት ጥሩ የሆነ እንጨት ወይም ነዳጅ ብቻ በቅ አይደለም፡፡ ለእሳት በቅ አየር ያስፈልጋል፡፡ ሰው ያለ አየር መኖር እንደማይችል ሁሉ እሳትም ያለ አየር አይነድም፡፡ ሰው ያለ አየር እንደምሞት ሁሉ፣ እሳትም ያለ አየር ይጠፋል፡፡ ይህ መንፈሳዊ አየር ደግሞ ፀሎት ነው፡፡ ለመንፈሳዊ እሳት ፀሎት Oxygen ነው፡፡ ከእሳት Co2ና CO ይወጣል/ ይለቃል፡፡ ይህ እሳት O2/ አየር ከጠፋ ይታፈንና ይጠፋል፡፡ ልክ እንደዚህ መንፈሳዊ እሳትም የፀሎት አየር ይፈልጋል፡፡ ይህ ፀሎት ከጠፋ ሕይወታችን በብዙ ነገር ይታፈንና እሳቱን ያጠፋል፡፡
3) የመንፈሳዊ ልምምድ ማጣት/Lack of sufficient exercise
✍ሰው በአሁኑ ጊዜ የራሱን Physical  ጠኝነት ለመጠበቅ ዘወትር የአካል እንቅስቃሰ ወይም  ስፖርታዊ ሥራዎችን ያደርጋሉ፡፡ ይህ ስፖርታዊ እንቅስቃሰ ወጤት እንድያመጣ ከተፈለገ ግን ሁልጊዜ ይህን ተግባር መፈፀም አለበት፡፡ ዘወትር ልምምዶችን እንድያደርግ ይመከራል፡፡ ልክ እንደዚህም አንድም አማኝ መንፈሳዊ ጠኝነቱን ጠብቆ እሳቱ ሳይጠፋ ለመኖር ዘወትር እሳቱን ማቀጣጠል አለበት፡፡ እሳቱን የማቀጣጠል ሥራ የሁልጊዜ ልምምድ መሆን አለበት፡፡ ቃሉን የማንበብ ፣ የመፀለይ፣ የማምለክ ፣ ወ.ዘ.ተ የእለት እለት ተግባር ማድረግ አለበት፡፡ “ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው።”2ጢሞ 1፥6
________________________________________________________
አንድ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ እሳቱ እንዳይጠፋና የሚያደርጉ ነገሮች፦
________________________________________________________
➊ አመዱን ማራገፍና ማስወገድ
✍በመሰዊያው ላይ እሳትም፣ እንጨትም እያለ ግን እሳት እንዳይነድና  እንድጠፋ ከሚያደርገው ነገር ዋነኛው አመድ ነው፡፡ አመድ አየበረከተ በመጣ ቁጡር እሳቱን የመሸፈንና እንደጠፋ የማድረግ አቅም ይኖራል፡፡ ስለዚህ እሳትን ለማንደድ በመጀመሪያ ከመሰዊያው አመድ መወገድ ይኖርበታል፡፡ አንድት ሴት እሳቱን ከማንደድ በፍት ሁል ጊዜ አንድ ተመሳሳይ ነገር ታደርጋለች፡፡ እርሱም ከሰለማንደጃ ወስዳ በውስጡ ያለውን አመድን ታራግፍና አመዱን ታስወግዳለች፡፡ ከዚህ ቦኃላ አድስ ከሰለ ጨምራ አሳት ተለኩሳለች፡፡ እሳቱ መንደድ ከጀመረም ቦኃላም  አመዱን የማራገፍ ሥራ ትቀጥላለች፡፡ ከእንጨት ሁለት ነገርን ይወጣል፡፡
✍እንጨቱን እንደ እግዚአብሔር ቃል፣ እንደ ፀሎትና እንደ አምልኮ እንውሰድ፡፡ ሰው ሁል ጊዜ ቃሉን ስያነብ፣ ስፀልይና ስያመልክ በዛ ሰው ሕይወት ውስጥ ሁሉት የሚሆን ነገር አለ፡፡
1. እሳት፦ ይህ እጅግ በጣም አስፈላጊና በሰው ሕይወት ውስጥ መኖር የሚገባ ነገር ስሆን
2. አመድ፦ ይህ ደግሞ አላስፈላጊና ከሰው ሕይወት  መወገድ የሚገባ ነው፡፡
✍ሁለ እንጨት በነደደ ቁጡር አመድ ይፈጠራል፡፡ ይህ አመድ ዘወትር በየዕለቱ ከሕይወታችን መራገፈ ይኖርበታል፡፡  የእግዚአብሔር ቃል፣ ፀሎትና አምልኮ ዘወትር በውስጣችን ስነድ እንደ አመገድ ከውስጣችን የሚወገድ ነገር አለ፡፡ ይህ አመድ መወገድ ብቻ ሳይሆን በአከባብ ጭምር መኖር የለበትም ከሠፈር ውጭ ተወስደው መጣል አለበት፡፡
ከሕይወታችን መወገድ ያለበት አመድ ምንድ ናቸው?
➊ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሥጋ ሥራዎች የተባሉት በመሉ
✍ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ንደት፥ መራርነት፥ ክፋት፥ ውሸት፥ ስድብ፥ ወ.ዘ.ተ ገላ 5:19-21፣ ኤፌ 4:25-32፣ ቆላ 3፡8፣ 1ጼጥ 2፡1
➋ አሮጌውን ሰው፡፡ ኤፌ 4፡22
➌ ድካም፥ ስንፍናና ስልቸት
➍ የልማድና የማስመሰል ሕይወት
✍እንደዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር እሳት በውስጣችን እንዳይቀጣጥልና እንዳይነድ የሚያደርጉ አመዶች ናቸው፡፡ ሁላችን እንደምናወቀው እሳት ጠፍተው አመድ ብቻ ስኖር ውሾችንና ድመቶች የሚተኑበት ሰፍራ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እሳቱ ስቀጣጠልና ስነድ ማንም መቀመጥ አይችልም ምክንያቱም እሳቱ ያቀጥላል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ከሁላችንም ሕይወት ይህ አመድ መራገፉና መወገድ ወደ ውጭ መጣል አለበት፡፡ ይህን ተግባር የሚያደርገው ለላ ሳይሆን እርሱ ራሱ ባለበቱ ነው፡፡

 ➋ዘወትር እግዚአብሔርን Worship/ ማምለክ
✍አሳ በውኃ ወስጥ ለመኖር እንደተፈጠር ሁሉ ሰውም የተፈጠረበት ዋና ዓላም እግዚአብሔርን ለማምለክ እንደሆነ አማኝ ማወቅ አለበት፡፡ “እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፦ ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።” ዘጸ 8፥1
✍ይህ እግዚአብሔርን ለማምለክ የተፈጠረ ሰው በእውነትና በመንፈስ “እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።” ዮሐ 4፥24 እግዚአብሔርን ስያመልክ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በውስጡ ይቀጣጠላል፡፡ የእግዚአብሔር መገኘትና ሕልውና ይሰሟል፡፡ በዚህ ጊዜ እሳቱ መነደድ ይጅምራል፡፡ ይህን ተግባር ሁለ ስያደርግ እሳቱ ፖግ ብለው ይነድዳል፡፡
➌ ዘወትር መፀለይ
✍ፀሎት ለአንድ አማኝ ውደታ ሳይሆን ግዳታ ነው ምክንያቱም ከኢየሱስ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው፡፡ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” ማር 14፥38
✍ከላይ እንዳየነው ፀሎት በውስጣችን ያለው እሳት እንድነድ የሚያደርግ አየር ነው፡፡ እሳትን የሚያቀጣጥሉ ሰዎች ምድጅ ላይ እንጨትና እሳትን ከጨመሩ በኃላ አየር ያስገባሉ ወይም ይሰጣል፣ ልክ እንደዛው በውስጣችን ያለውን አሳት እንድነድ የሚያደርግ ፀሎት ነው፡፡ ፀሎት በጣም ኃል አለው፡፡ አንድ ሰው ስፀልይ ኃይል ያገናል፡፡
➍ የእግዚአብሔር ቃልን መመገብ / Meditate on God's Word.
✍አንድ አማኝ በውስጡ ያለውን እሳትን ማቀጣጠል ከፈለገ የእግዚአብሔር ቃልን ዘወትር ማንበብ፣ መማር፣ ማጥናት እና በቃሉ ለመኖር መለማመድ አለበት፡፡
➎ ለክርስቶስ passionate ከሆነ /ጥልቅ ስሜት ካላቸው ሰዎች ጋር ሕብረት ማድርግ
✍በተፈጥሮ ብዙ ዓይነት ሰዎች በቤተክርስቲያን አሉ፡፡ አንዳንዶቹ በተፈጥሮ መንፈስ ቀዝቃዛ ናቸው፡፡ እንዳንዶችሁ ደግሞ እጅግ በጣም የሚቀጣጠሉ ናቸው፡፡ የቀሩት ደግሞ ለብ ያሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለአምልኮ፣ ለፀሎት፣ ለወ.ዘ.ተ ነገር ፍላጎት ካላቸውና ከአንተ ጋር እንጨት ሆነው መቀጣጥል ከምችሉና ከምፈልጉ ጋር መሆን በራሱ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ምንም ያህል ኃይል ያለው ብሆንም አንድ እንጨት ለብቻው አይነድም፡፡ አብሮ የሚነድ ለላ እንጨት ያስፈልጋል፡፡ ይህ እንጨት ግን ደረቅ መሆን አለበት ካልሆነ ደግሞ ምንም እንኳን ከደረቅ እንጨት ጋር በመሆን የሚነድ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን ጭስ ብቻ ማብዛት የለበትም፡፡ መንፈሳዊ ነገር ከሚጠላ፣ ለመፀለይና ለማምለክ  ከማይወድና ከማይፈልግ ይልቁን ለወሬ፣ ለቀለድ፣ ለሀመት በርቱ ከሆነ ስው ሕብረት ማድረድ የእርሱን ብቻ ሳይሆን የአንተንም እሳት ጭምር ያጠፋልና ተጠንቀቁ፡፡
➏ ዘወትር አድስ እንጨት መጨመር
✍እሳት እየነደደ መቀጠል አለበት ከተባለ ዘወትር አድስ እንጨት ወደ መሠዊያወ መጨመረ ይኖርበታል፡፡ አንድት እንጀራ የሚታጋግር እናት ልጡ እስከምያልቅ ድረስ እንጨትን ትጨምራለች ምክንያቱም አንድ ጊዜ የተጨመረ እንጨት በቅ አይደለምና፡፡  የመጀመሪያው እያለ ሳያልቅ ለላ እንጨት ትጨምራለች፡፡ የምጣዱ ሙቀት ሳይቀነስ ሳይበዛ እንደ ምጣዱ ባህር እሳቱን ተቆጣጥራ መቀጠል አለባት፡፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ አንድም አማኝ በተገቢው መልክ እሳት እንዳይጠፋ አየነደደ እንድቀጥል ዘወትር እንጨትን ወደ መሠዊያው መጨመር አለበት፡፡ ባለማቋረጥ ፀሎትን፣ አምልኮን፣ የእግዚአብሔር ቃልን ወደ ውስጡ መጨመር አለበት፡፡  አሁን በዘመናችን ብዙ አገልጋዮች አድስ እንጨትን ጨምሮ አሳትን ከማቀጣጠል ይልቅ ድረው በአንድ ወቅት እግዚአብሔር በውስጣቸው በሕይወታቸው ያቀጣጠለውን እሳት ብቻ እያወሩ በትዝታ ወደኋላ ሄዶ ያንንም ጊዜ እየተረኩ ብቻ ለመኖር ይፈልጋሉ፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ግን ዛሬ እሳቱ ጠፍተው አመድ ብቻ ታቅፈው መኖሩን አለማወቃቸው ነው፤ ብያውቁም እንኳን አድስ እንጨት ጨምሮ እሳትን ማንደድ አይፈልጉትም፡፡ በዚህ ምክንያት የዛሬው አመድ ሳይታያቸው የድረው እሳት በትዝታ እያሰቡ ዘመናቸውን ይገፋሉ፡፡ ስለዚህ ዛሬ አመዱ ተወግዶ እሳቱ ዘወትር እንዲቀጣጥል አድስ እንጨት መጨመር አለበት፡፡  የዛሬው ምግብ በዛሬው እንጨት እንደምበስል ሁሉ በዛሬው እሳት ዛሬ በመቀጣጠል ማገልገለ ይኖርብናል፡፡ የዛሬው እሳት ለነገ አገልግሎት ጥሩ ብሆንም ነገር ግን የነገውን ምግብ ለማዘጋጀት ለላ አድስ እንጨት ያስፈልጋል፡፡
እሳት በሕይወታችን ስኖር
➊ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንፈፅማለን፡፡
➋ በእግዚአብሔር መገኘት ወይም ህልውና ውስጥ እንሆናለን፡፡
➌ በንፅህናና በቅድስና መኖር እንጀምራለን፡፡
➍ እሳት ሆነን እንገለጣለን፡፡

Comments

Popular posts from this blog

መንፈሳዊ አገልግሎት

3ቱ የክርስቲያን ልብሶች

መንፈሳዊ እርጅና