ማን ነገረህ?

▦የተወደዳችሁ፣ የተመረጣችሁና የተከበራችሁ ውድ ወገኖቼ፤
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና
ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ዛሬም እንደተለመደው አንድ መልዕክት ይዤላችሁ
ቀርቤያለሁና እንድታነቡት እጋብዛለሁ።
ውድ ወገኖቼ፤ እስከዛሬ በእናንተ ሕይወት ላይ ብዙ ነገር
ተወርቶና ተነግሮ ወይም ተብሎ እናንተ ደግሞ ስምታችሁ
ይሆናል። ለአብነትም ያህል ፈሪ ነህ፣ ደካማ፣ አትችልም፣
አትጠቅምም፣ አይሆንም፣ አይሳካም፣ አትሄድም፣ አትወጣም፣
አትደርስም፣ አትወርስም፣ እንድህ አትሆንም ወይም ደግሞ
እንድህ አይደለህም እና ወዘተ የተባሉ አንጀት ብጥስና ቀስም
ስብር የሚያደርጉ መጥፎና አሉታዊ (#Negative) ንግግሮችን
ወይም ቃላቶችን በሕይወታችሁ ተነግሮና ተወርቶ እናንተም
በበኩላችሁ ሰምታችሁ ይሆናል።
ከዚህም የተነሳ ብዙዎቻችሁ ምናልባት አልቅሳችሁ፣
አዝናችሁ ወይም ደግሞ ተስፋም ቆርጣችሁ፣ በእግዚአብሔር
ላይ ያለውን እምነትንም አጥታችሁ፣ የተባለውንና የተነገረውን
ንግግሮችንና ቃላቶችን እንዳለ ተቀብላችሁ ዛሬ ላይ በማይሆንና
እናንተንም በማይመጥን ቦታ ላይ ትኖሩ ይሆናል።
እሽ ይሁን ግድ የለም። ግን ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ነገር
ልጠይቃችሁ። በእናንተ ሕይወት ምን እንደተነገረ ወይም ምን
እንደተወራ ወይም ደግሞ ምን እንደተባለ አሁን በደንብ አስቡት።
በእናንተ ሕይወት ላይ ምን ያህል መጥፎና አሉታዊ ንግግሮችና
ቃላቶች እንደተነገሩ፤ አንደተወሩና እንደተባሉ እናንተ ራሳችሁ
በደንብ ታውቁታላችሁ። አሁን ጥያቄ ምን ተነገረ፣ ምን ተባለ
ወይም ደግሞ ምን ተወራ የሚለውን አይደለም። አሁን ጥያቄው
የሚሆነው ይህን ሁሉ ማን ነገረህ፣ ማን አወራ ወይም ደግሞ
ማን አለ የሚለው ነው።
▦ ምናልባት በእናንተ ሕይወት ላይ ፈሪ ነህ፣ ደካማ ነህ፣
አትችልም፣ አትጠቅምም፣ አይሆንም፣ አይሳካም፣ አትሄድም፣
አትወጣም፣ አትደርስም፣ አትወርስም፣ እንድህ አትሆንም ወይም
ደግሞ እንድህ አይደለህም እና ወዘተ የተባሉ ነገሮች ተነግሮና
ተወርቶ ከሆነ ኢስት ይህን መልሱ።
➤ቦቅቧቃ፣ ፈሪና ደካማ እንደሆንክ ማን ነገረህ?
➤እንደማትችል፣ እንደማትጠቅምና ሰው እንደማትሆን ማን
ነገረህ?
➤እንደማይቀና፣ እንደማይሆንና እንደማይሳካ ማን ነገረህ?
➤እንደማትወጣ፣ እንደማትሄድ፣ እንደማትደርስና እንደማትወርስ
ማን ነገረህ?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ አንዳንድ እውነታዎችን
እንመለከታለን።
●አንደኛው እውነት፦በእናንተ ላይ የተነገረው ምዋርት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
ከላይ ያየናቸው ማለትም ፈሪ ነህ፣ ደካማ ነህ፣ አትችልም፣
አትጠቅምም፣ አይሆንም፣ አይሳካም፣ አትሄድም፣ አትወጣም፣
አትደርስም፣ አትወርስም፣ እንድህ አትሆንም ወይም ደግሞ
እንድህ አይደለህም እና ወዘተ የተባሉ ቃላቶች በሙሉ
በሕይወታችሁ፣ በኑሮአችሁና በቤታችሁ ላይ የተነገረ ምዋርት
ነው። ምዋርት ደግሞ በእናንተ ሕይወት ላይ እንደማይሰራ
የእግዚአብሔር ቃል በዘኍልቁ 23፥23 ላይ “በያዕቆብ ላይ
አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤” በማለት
ይናገራል።
ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ማወቅ ያለባችሁ ወሳኝ ነገር
ብኖር ይህን እውነት ማመን ነው። ስለዚህ ከማዘን፣ ከመፍራትና
ተስፋን ከመቁረጥ በፍት ምዋርት በእናንተ ላይ እንደማይሰራ
ማወቅ አለባችሁ።
●ሁለተኛው እውነት፦ ምዋርተኞችሁ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
ምናልባት ይህ እውነት ብዙም ላይጥማችሁና ላይገባችሁ
ይችላል። ነገር ግን እውነታው ይህ ነው። በእናንተ ላይ
የሚትምዋረቱ ሌላ ማንም ሳይሆን እናንተው ራሳችሁ ናቸው።
ይህን እውነት ከእግዚአብሔር ቃል ላሳያችሁ። ወደ ዘፍጥረት
3፡9-11 ላይ ሄደን የእግዚአብሔር ቃልን ስንመለከት
"እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ፦ ወዴት ነህ? አለው።
እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ
ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም። እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ
ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ
በላህን?"
ኢስት ተመልከቱት፦
ሰው ነው የተናገረው እንዳንል ለብቻቸው ነበሩ እንጂ
ከሁለታቸው በስተቀር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም።
እግዚአብሔር ነው እንዳንል እግዚአብሔር ራሱ "ዕራቁትህን
እንደ ሆንህ ማን ነገረህ?" እያለ እየጠየቀ ነው። ስለዚህ እሱም
አይደለም።
አያችሁ ወገኖቼ አባታችን አብርሃም ዕራቁትነቱን የተናገረው
እሱ ራሱ ነው እንጂ ሌላ ማንም አይደለም። እርሱም "በገነት
ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ" አለ።
ስለዚህ ወገኖቼ እመኑኝ
በእናንተ ሕይወት ይህን ምዋርት የተናገረው ሌላ ሰው
አይደለም። ሰው በሰው ላይ አይምዋረትም እያልኩ አይደለም።
ይህን እንዳለም አውቃለሁ። ምንም እንኳን ሰው በእናንተ
ሕይወት ላይ ምንም ያህል ብያምዋርት ወይም ብናገር ሰው
ያለው በእናንተ ላይ አይሆንም።
እናንተ የሚትሆኑት ሰው ወይም ምዋርተኛ እንዳለው ሳይሆን
እናንተ የሚትሆኑት ቃሉ እንዳለ ነው። በዓለም ላይ ትልቁ
ምዋርት ማለት ሰው በሰው ላይ የሚያምዋርተው ምዋርት
ሳይሆን ሰው በራሱ ላይ የሚያምዋርተው ምዋርት ነው። ይህ
ምዋርት ከሁሉም የከፋና እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ምዋርት
ነው።
በእናንተ ሕይወት ይህን የተናገረው እግዚአብሔርም
አይደለም። ይህን እግዚአብሔር አምላክ አልተናገረም ደግሞም
እርሱ በፍጹም እንደዚህ አይናገርም። እርሱ ፈሪን ጎበዝ ነህ፣
ደካማውን ብርቱ ነህ፣ የማይችለውን ትችላለህ፣ መሄድ፡
መውጣት፡ መውረስ አልችልም የሚለውን መሄድ፡ መውጣት፡
መውረስ ትችላለህ አይዞ እኔ አለው አትፍራ በርታ ይላል እንጂ
መጥፎና አስቀያሚ ነገር አይናገርም። እርሱ እግዚአብሔር
ነውና።
ስለዚህ በሁለተኛ ደረጃ ማወቅ ያለባችሁ እውነት በእናንተ
ሕይወት ወይም በእናንተ ኑሮ ላይ ክፉን ነገር የተናገራችሁት
እናንተው ራሳችሁ ናችሁ። ይህን በቶሎ አቁሙት።
●ሦስተኛው እውነት፦ምዋርተኛ የሆናችሁት በምክንያት ነው።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
አሁን ሁላችሁም ባታምኑም እንኳን ምዋርተኞች ናችሁ።
ነገር ግን ምዋርተኞች እናንተው ራሳችሁ እንድትሆኑ ያደረገ
የራሳችሁ የሆነ ምክንያት አላችሁ።
አባታችም አብርሃም እንኳን ብሆን የራሱን ዕራቁትነቱን ራሱ
የተናገረው ወዶ ወይም ደግሞ ለመናገርም ፈልጎ አልነበረም።
አባታችን አብርሃም የራሱን ዕራቁትነቱን ራሱ የተናገረው
በእግዚአብሔር በፍት ኃጢአት ስለሰራ፣ የእግዚአብሔርን አትብላ
ያለውን ዘፍ ስለበላ የእግዚአብሔርን ፍት ማየት ስለፈራ ነው።
ይህን እውነት በዘፍጥረት 3፡8-12 ላይ እናገኛለን።
"እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ
ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም
ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ፦ ወዴት ነህ? አለው።
እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ
ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም፤ እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ
ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ
በላህን? አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት
እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ" አለ።
በሌላ በኩል ደግሞ ኢዮብን በኢዮብ ምዕራፍ ሦስት ላይ
ስንመለከት ኢዮብም በራሱ ላይ ከባድ ነገርን ተናግሯል። ለዚህ
ደግሞ ምክንያት የሆነው በእርሱ ላይ የተፈራረቀው ከባድ የሆነ
ፈተናና በሽታ ነው። ኢዮብ የተናገረው ንግግር ስንመለከት እጅግ
በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ ያህል ጥቅቶችን እንይ።
ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን
ረገመ።… ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም፦ ወንድ ልጅ
ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት። ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር
ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት። …በማኅፀን ሳለሁ
ስለ ምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን
አልጠፋሁም? አለ። ኢዮብ 3፡1-11
ውድ ወገኞቼ እናንተም ልክ እንደ አብርሃምና እንደ ኢዮብ
እናንተው ራሳችሁ ምዋርተኛ የሆናችሁት ወዳችሁ ወይም ደግሞ
ፈልጋችሁ አይደለም። ከላይ ያየናቸውን ብዙ ዓይነት አሉታዊ
( # Negative) ንግግሮችን በራሳችሁ ላይ እንድትናገሩና
እንድታወሩት ያደረገ የራሳችሁ የሆነ ምክንያት አላችሁ።
የአባታችን የአብርሃም ምክንያት ኃጢአት ነው። የኢዮብ
ደግሞ አስቸጋሪ የሆነ ፈተናና በሽታ ነው። የእነርሱ ምክንያት
ይህ ከሆነ ምናልባት በተመሳሳይ ሁኔታ የእናንተም ምክንያት
ተመሳሳይ ልሆን ይችላል። መቼም ብሆን ሰው ያለ በቂ ምክንያት
እንደዚህ ዓይነት መጥፎና ክፉ ንግግሮችን በራሱ ላይ
አይናገርም።
ወገኖቼ አሁን አንድ ነገርን ላሳስባችሁ እወዳለሁ። እናንተ
እንደዚህ እንድትሆኑ ያደረገ፣ እንደህ ዓይነት መጥፎና ክፉ
ቃላቶችሁን በራሳችሁት ላይ እንድትናገሩት ያደረገ ምክንያት
ምንድነው?
ስለዚህ በሦስተኛ ደረጃ ማወቅ ያለባችሁ ሌላ እውነት
እንደዚህ እንድትናገሩ ያደረገውን ምክንያት ነው።
ምክንያታችሁ ምንድነው? ኃጢአት ይሁን? ወይስ ፈተና
ይሁን? ወይስ መከራ ይሁን? ወይስ ችግር ይሁን ወይስ
የትኛውም ዓይነት ሁኔታ ይሁን? ምን ይሁን? አሁን
ምክንያቶችሁን ለማወቅ ሞክሩት።
●አራተኛው እውነት፦ከምክንያታችሁ የሚበልጥ ሌላ ምክንያት
አለ።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
◉ውድ ወገኖቼ ከላይ በኩል ያየናቸውን ብዙ ዓይነት አስቀያሚ
ቃላቶችሁን የተናገራችሁት በምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት
የተነሳ ብዙ ነገርን እናንተ ራሳችሁ በእናንተው ላይ
ተናግራችኋል። ከዚህም የተነሳ ብዙ ዓይነት ችግር ውስጥ
ገብታችኋል።
◉እናንተ በራሳችሁ ላይ ክፉ ነገርን እንድትናገሩ ካደረገውና
እናንተም ደግሞ ከምትዘረዝሩት ከየትኛውም ዓይነት ምክንያት
በላይ የሆነና የሚበልጥ ሌላ ምክንያት አለ።
ይህን ምክንያት በደንብ ካወቃችሁና ከተረዳችሁ ሌላ ማንነት
ይዛችሁ እንደገና በምክንያቶቻችሁ ሁሉ ላይ መገለጥ
ትጀምራላችሁ። ይህን ምክንያት ስታውቁ ሌላው ምክንያት ሁሉ
እያለ እንዳልነበረ ይሆናል።
ይህም ምክንያት ምንድነው ካላችሁ ይህ ምክንያት
እግዚአብሔር ነው። ይህ ምክንያት ጌታችን ኢየሱስ
ነው።ከእነዚህ ምክንያት በላይ ሆኖ የሚያስጨንቃችሁና
የሚያስፈራችሁ ሌላ ምንም ምክንያት አይኖርም።
ይህን ታላቅ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ እናያለን።
አባታችን አብርሃም እኮ ከመጀመሪያውም ጀምሮ ዕራቁቱ
ነበረ። ነገር ግን ስለዕራቁነቱ እንድም ቀን ብሆን አስቦት
ፈርተውም አያውቅም። “አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን
ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።” ዘፍጥረት 2፥25
በእርግጥም አብርሃም ዕራቁቱ ነው። ነገር ግን በዕራቁትነት
ምክንያት ፈርተው አያውቅም። አብርሃም የማይፈራው ስሌለበሰ
ወይም ደግሞ ዕራቁት ስላልነበረ አይደለም። አብርሃም ምንም
ልብስ አልለበሰም ስጀመረ ልብስ አልነበረም።
አብርሃም የማይፈራበት ትልቁ ምክንያት አብርሃም የለበሰው
ተራ ልብስ ሳይሆን አብርሃም የለበሰው የእግዚአብሔርና
የእግዚአብሔርን ክብር በመሆኑ ነው።
አብርሃም ዕራቁቱን እንደሆነ ያወቀውና በዕራቁትነት ምክንያት
የፈራው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ በመተላለፍና ኃጢአት በመሰራቱ
ምክንያት የእግዚአብሔር ክብርና ሞገስ ከላዩ ከተነሳ በኃላ
ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ
ሰው ከፈሪ ነው። ነገር ግን ሰው የማይፈራው ፥የሚያስፈራ
ነገር ስለሌለ ሳይሆን ከሚያስፈራው ከየትኛውም ዓይነት ነገር
የበላይ የሆነ እግዚአብሔር ስለሚኖር ነው።
❖በተቃራኒው ደግሞ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ስጣላ፣ ትዕዛዙን
ስተላለፍና ኃጢአትን ስሰራ ከማንም በላይ ፈሪ ይሆናል።
በሕይወቱም ሁሉ ፈሪነትንና ሽንፈትን እያወጀ ተራ ኑሮ ይኖራል።
ሰው ደካማ ነው። ነገር ግን ሰው ብርቱ የሚሆነው ደካማ
ስላልሆነ ሳይሆን በድካም ሁሉ ኃይልና ብርታት የሚሆን ጌታ
ኢየሱስ ስላለ ነው።
❖በተቃራኒው ደግሞ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ስጣላ፣ ትዕዛዙን
ስተላለፍና ኃጢአትን ስሰራ ከማንም በላይ ደካማ ይሆናል።
በዘመኑ ሁሉ አለመቻሉንና ደካማነቱን እያወራ ይኖራል።
ሰው አይችልም። ነገር ግን ሰው ሁሉም ነገር የምችለው
የመቻል አቅም ስላለ ሳይሆን ሁሉን የምችል ጌታ ኢየሱስ በሰው
ውስጥ ስላለ ነው።
❖በተቃራኒው ደግሞ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ስጣላ፣ ትዕዛዙን
ስተላለፍና ኃጢአትን ስሰራ ከማንም በላይ ራሱን ዝቅ አድርጎ
አንገቱን ደፍቶ በዘመኑ ሁሉ አለመቻሉን እያወራ ይኖራል።
ሰው በራሱ መውጣት፣ መሄድና መውረስ አይችልም። ነገር
ግን ይህን እንድናደርገው የሚያስችል እግዚአብሔር ነው።
❖በተቃራኒው ደግሞ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ስጣላ፣ ትዕዛዙን
ስተላለፍና ኃጢአትን ስሰራ የትም መውጣት፣ መሄድና መውረስ
እንደማይችል አምኖ ተራና የወረደ ሕይወት ይኖራል።
ስለዚህ በአራተኛ ደረጃ እናንተ ከምትዘረዘሩት ከየትኛውም
ዓይነት ምክንያት በላይ ሌላ የበላይ የሆነ ምክንያት መኖሩን
እወቁት።
# ስለዚህ_ምን_እናድርግ ካላችሁ፦
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
➀እናንተው ራሳችሁ ምዋርተኛ አትሁኑ።
★የመዝራትና የማጨድ መርህ ስላለ በእናንተ ሕይወት ላይ
አሉታዊ ነገርን አትናገሩ።
➁ምዋርተኛ እንድትሆኑ ያደረገውን ምክንያታችሁን እወቁት።
❖ እናንተ የራሳችሁ በራሳችሁ ላይ እንድትምዋርቱ ያደረገው
ምንድነው? ያንኑን ምክንያት እወቁት።
➂ለምክንያታችሁ መንስኤን እወቁት።
❖ለምክንያታችሁ መንስኤ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ ማለት
ኃጢአታችሁ ነው? ወይስ ሁኔታ ወይስ መከራና ችግር ወይስ
ፈተና ነው? ይህን ለይታችሁ እወቁት።
➃ከምክንያችሁ በላይ የሆነ እግዚአብሔር እንዳለ እወቁት።
❖ለዚህ አስቀድማችሁ ሁለቱ ነገር አድርጉ
1ኛ.ምክንያታችሁ ኃጢአት ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ።
2ኛ.ምክንያታችሁ ሌላ ከሆነ በእግዚአብሔር ላይ ጣሉት።
➄ወደ ማንነታችሁ ተመለሱ።

Comments

Popular posts from this blog

መንፈሳዊ አገልግሎት

3ቱ የክርስቲያን ልብሶች

መንፈሳዊ እርጅና