እግዚአብሔር ለምድራችን ዕረፍት ይሰጣል
◉በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረም፥ በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ነበረ። እግዚአብሔር በመከራው ሁሉ ያስጨንቃቸው ነበርና። 2 ዜና 15፡4-5
◉ይህ ዛሬ የእኛ ዘመን ነው። ከዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ምድራችን🌎🌐 ያሳርፋል። እግዚአብሔር ለምድራችን 🌎🌐 ዕረፍትን ይሰጣል። ይህ ዕረፍት ስሆን ለሚወጣው ለሚገባው ሰላም ይሆናል፣ ከሰዎች መሀል ድንጋጤ ይወገዳል። ይህ ብቻ አይደለም፦ዓለማችን ከመከራና ከጭንቀት ታርፋለች።
◉ነገር ግን ይህ ሁሉ ዝንብሎ አይመጣም። ይህን ዕረፍት ወደ ምድራችን ለማምጣት ማድረግ ያለብን ነገሮች አሉ። ➽የእግዚአብሔርን ቃልን ስንመለከት በራሳቸው ዘመን ለራሳቸው ምድር የዕረፍት ምክንያት የሆኑ ሰዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ፦
▦➀በኢያሱ መጽሐፍ በምዕራፍ በ11፤14 ላይ ኢያሱና በካሌብ፦
➖➤በእነርሱ ዘመን በእነርሱ ምክንያት ምድርቷ ከውጊያ አረፈች።
▦➁በመሳፍንት መጽሐፍ በምዕራፍ በ3፤5፣8 ላይ ጎቶንያል፣ ድቦራና ጌዴዎን፦
➖➤በእነርሱ ዘመን በእነርሱ ምክንያት ምድርቷ ለአርባ ዓመት ዐረፈች።
▦➂በመሳፍንት መጽሐፍ በምዕራፍ በ3 ላይ ናዖድ፦
➖➤በእርሱ ዘመን በእርሱ ምክንያት ምድርቷ ሰማንያ ዓመት ዐረፈች።
▦➃በ2 ዜና 14፥1 ደግሞ አብያ፦
➖➤በእርሱ ዘመን በእርሱ ምክንያት ምድርቷ አሥር ዓመት ያህል ዐረፈች።
◉እኛ ወጣቶች ለዚህች (በመከራ፣ በጭንቀት፣ በጥፋት ላለች) ምድር የዕረፍት ምክንያት መሆን አለብን። ዛሬ ለዚህች ምድር እናስፈልጋታለን። ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን አራት ነጥቦችን ማድረግ አለብን።
🔵1ኛ.ከሕይወታችን ከመካከላችን እግዚአብሔር የማይወደውን አጸያፊ ነገርን እናስወግድ።
□ “ከይሁዳና ከቢንያምም አገር ሁሉ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ከያዛቸው ከተሞች ጸያፉን ነገር አስወገደ" — 2 ዜና 15፥8
➤ምንድነው እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት የማይወደው? ያንን በቶሎ ማስወገድ አለብን።
🔵2ኛ.የእግዚአብሔርን መሠዊያን እናድስ።
□"በእግዚአብሔርም ቤት ፊት የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አደሰ።” — 2 ዜና 15፥8
➤የእግዚአብሔር መሠዊያ አገልግሎት አይደለም። የእግዚአብሔር መሠዊያ ሕያውና ቅዱስ የሆነው የእኛ ሰውነት ነዉ።
□“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።”— ሮሜ 12፥1
➤እንዴት ነው? የእኛ መሠዊያ ምን ያህል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል?መሠዊያ ምን ያህል ሕያውና ቅዱስ ነው? ይህን መሠዊያ በፍጥነት ማደስ አለብን።
🔵3ኛ.እንሰብሰብ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እናድርግ።
□"አሳም በነገሠ በአሥራ አምስተኛው ዓመት በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎች ለእግዚአብሔር ሠዉ።" 2 ዜና 15፡10-11
➤ እንሰብሰብ (እንጸልይ) ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እናቅርብ።
□ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። ዘጸአት 23፥25
🔵4ኛ.በፍጹም ልባችን፣ በፍጹም ነፍሳችንና በፍጹም ሕልናችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ ፍቱን እንፈልግ።
□“በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ፤” — 2 ዜና 15፥12
➤በፍጹም ወደ እግዚአብሔር መመለስና እርሱን መፈለግ አለብን።
□"እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ወቀርቦም ሳለ ጥሩት፤ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።" ኢሳይያስ 55፡6-7
🔵በአጠቃላይ፦
✅ከሕይወታችን አፀያፊ ነገርን እናስወግድ
✅ሕያውና ቅዱስ በሆነው ማንነት ለእግዚአብሔር የሚገባውን መሠዋት እናቅርብ
✅ወደ እግዚአብሔር እንፀልይ
✅ከሙሉ ማንነታችን እግዚአብሔርን እንፈልግ

Comments
Post a Comment