ውስጡ የጌታ ከሆነ ውጭው የማነው?
♦የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
♦መጽሐፍ ቅዱሳችን በምናይበት ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ብዙ ዓይነት ሐሰት አስተማሪዎች እንደሚነሱ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። ለአብነት ያህል በ2ኛ ጴጥሮስ 2፡1 ላይ "ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ" ይላል።
♦ሐሰት አስተማሪዎች እስካሉ ድረስ ደግሞ ሐሰት አስተምህሮዎች መኖሩ አይቀሬ ነው። መቼስ ሐሰት አስተማሪዎች የሚነሱት እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማስተማር ሳይሆን ውሸተኛውን የአባታቸውን የሰይጣን ትምህርት ለማስተማር ነው።
♦አሁን ጊዜው የዘመን መጨረሻ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ዓይነት ሐሰት አስተምህሮዎች በምድራችን ላይ ተነስቷል። አሁን ላይ ከተነሱት ከሐሰት አስተምህሮዎች አንዱ "አንድ ሰው አንድ ጊዜ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኋላ ኃጢአትን ብሰራ እንኳን በምንም ሁኔታ ደህንነቱን ሊያጣና ሊፈረድበት አይችልም። በገዛ ሥጋው ላይ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋ ጋር ጉዳይ የለውም። ሥጋ በዚህ ምድር የሚቀር አፈር ስለሆነ ሰው በሥጋው ላይ የፈለገውን ቢያደርግም ነገር ግን ነፍሱ ከዳነች ምንም ችግር የለም ምክንያቱም የውስጡ የጌታ ነው ውጪ የአፈር ነው " የሚል ነው።
♦ይህ ትምህርት ዓይነት በተለይም ለወጣቱ ትውልድ እጅግ በጣም የሚመች አስደሳችና ምርጥ ትምህርት ነው። ስጀመር ይህ ሐሰት አስተምህሮ ከመምጣቱም በፍት በ1ኛ ሳሙኤል 16፥7 ላይ “ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” የሚለውን ቃል ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአውዱ ውጭ ለራሳቸው እንደሚመች አድርጎ እየተተረጎሙ ለድክመታቸው መሸፈኛ እያደረጉ ያሉ ወጣቶች ይህን አስደናቂው ውሸትን አግኝቶ እንዴት አይደሰቱም?
♦በአጠቃላይ ሰዎች በተለይም በአካሄዳቸው ትክክል ያይደሉ፣ የራሳቸውን ፍቃድና የሥጋቸውን ምኞት ለመፈጸም የሚፈልጉ፣ በሰውነታቸው እግዚአብሔርን የማያከብሩ፣ ብልቶቻቸውን ለእግዚአብሔር የጽድቅ ጦር ዕቃ ሳይሆን ለሰይጣን የአመፃ ጦር ዕቃ አድርጎ እያቀረቡ ያሉና ሰውነታቸው የእግዚአብሔር ቤተመቅደስና የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ እንደሆነ የማያስተውል፣ የማያውቁ ነገር ግን ይህን እውነት መቀበል የማይፈልጉ ሰዎች ይህን አስተምህሮን ለመቀበል ወደኃላ አይሉም።
♦ይህን የሐሰት አስተምህሮን የሚያራምዱ ሐሰት አስተማሪዎች የእግዚአብሔርን ቃልን ያጣምማሉ። ለራሳቸው ዓላማ ማለትም ትውልድን ለማጥመድ ትውልድ የሚፈልገውን አሳብ ይዞ ይመጣሉ። በስተመጨረሻ ዓላማቸው ግን ትውልድን መግደል፣ ከእግዚአብሔር መንግሥት ማስቀረትና ወደ ገሃነም መጣል ነው። “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” ዮሐንስ 10፥10
●ከዚህ በመቀጠል ትክክለኛውና እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል አስተምህሮን እናያለን።
♦ሐሰት አስተማሪዎች እንደሚሉት እውነትም ሥጋ የአፈር እንጂ የጌታ አይደለም ማለትም ውስጡ የጌታ እንደሆነ ወጭው የጌታ አይደለም? በፍጹም። ይህ አስተምህሮ ትክክለኛና እውነተኛ ያልሆነ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው። በእርግጥ ሁሉም ሰው የተገኘው ከአፈር ነው ይሁን እንጂ ሥጋችን የአፈር ሳይሆን የጌታ ነው።
♦ኤፌሶን 2፡1-17 ሄደን የእግዚአብሔር ቃልን በምናይበት ጊዜ ይህ በመጀመሪያ ከአፈር የተገኘው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰው በኃጢአቱና በበደሉ ምክንያት ሞተው ነበረ (ኤፌሶን 2፡1)። እኛ
✅እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሳይሆን እንደ ሰይጣን ፍቃድ እየተመላለሰን (ኤፌሶን 2፡2)
✅በእግዚአብሔር አሳብና ምኞት ሳይሆን የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት እየኖረን (ኤፌሶን 2፡3)
✅በሥጋ በእጅ በተባለው መገረዝ እንኳን ያልተገረዘን በሥጋ አሕዛብ የነበርን (ኤፌሶን 2፥11)
✅ከእስራኤልም መንግሥት ርቀን ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች የሆነን (ኤፌሶን 2፡12)
✅በዚህም ዓለም ተስፋን አጥተን ከእግዚአብሔርም ተለይተን ያለ ክርስቶስ የነበርን (ኤፌሶን 2፡12) ሰዎች ነበርን።
♦ነገር ግን በምሕረቱና በፍቅሩ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር በኃጢአታችንና በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ
✅ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት እንደሰጠና በጸጋ እንዳዳነ (ኤፌሶን 2፡4)
✅በፊት ከእግዚአብሔር ተለይተን ርቀን የነበርን በክርስቶስ ደም በኩል ወደራሱ እንዳቀረበ (ኤፌሶን 2፡13)
✅ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልተን ሠላም አተን ለነበርን ሠላምን እንደሰጠ፣ ምስራችን እንደሰበከ፣ የጥልን ግድግዳ በሥጋው እንዳፈረሰና ሁለቱን አዋህዶ አንደ እንዳደረገው (ኤፌሶን 2፡14-17) የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል።
♦ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ሁሉ ያደረገው ለሰው ልጆች ነው። ለሰው ልጆችም ስል ብዙ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። ነገር ግን ይህን መከራና ስቃይን የተቀበለው በመንፈስ ወይም በነፍስ ብቻ ሳይሆን በሥጋው ጭምር ነው። የተገረፈው፣ የተመታው፣ የተራበው፣ የተጠማው፣ የተሰቃየውና ሙከራን የተቀበለው በሙሉ በሥጋው ነው።
♦ኢየሱስም በመጨረሻው ወደ ሰማይ ከማረጉ በፍት በማቴዎስ 26፡26-28 ላይ ( "ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። በተመሳሳይ በ1ኛ ቆሮንቶስ 11፡24-25 ላይም "ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።") ሁልጊዜ ይህን ማሰብ እንደሚገባና ደግሞ ሁለንተናችን ማለትም መንፈሳችን፣ ነፍሳችንና ሥጋችን ጌታችን እሱ እስከመጣ ድረስ ያለ ነቀፋ ፈጽመው በቅድስና መጠበቅ እንዳለበት ይናገራል። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥23
♦በእነዚህ በሁለቱም ክፍሎች (በማቴዎስ 26፡26-28 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡24-25) ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ሥጋና ደም እንደ ተለመደው በምሳሌ ለመናገር ፈልጎ ሳይሆን እንጀራው እውነተኛ ሥጋ ደግሞ ጽዋ እውነተኛ ደም እንደሆነ በዮሐንስ 6፥55 ላይ “ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።” በማለት አስረግጠው ተናግሯል።
♦በዚህ መሠረት አንድ ትልቅ እውነትን ላሳያችሁ። ሰው የሚሰራውን የትኛውም ዓይነት ኃጢአት የሚሰራው በገዛ ሥጋና ደም ላይ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ሥጋና ደም ላይ ነው። ምክንያቱም ሰው በዋጋ ተገዝቷልና ለራሱ አይደለም። “በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም" (1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20)። በእኛ ሕይወት ላይ የእኛ ምንም ነገር የለም። በእኛ ሕይወት ሆነ በእኛ ሥጋ ላይ ለእኛ ምንም ዓይነት ስልጣን የለም። ስልጣን የማንም ሳይሆን የኢየሱስና የኢየሱስ ብቻ ነው። ስለዚህ በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበር አለብን። "ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" (" (1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20)። ውስጣችን የጌታ እንደሆነ ሁሉ ውጭያችም የጌታ ነው።
#በሥጋችን_እግዚአብሔር_ማክበር_ያለብን_ለምንድነው?
××××××××××××××××××××
♦ውስጣችን የጌታ እንደሆነ ሁሉ ውጭያችም የጌታ ነው። ስለዚህ በሥጋችን እግዚአብሔር ማክበር አለብን። ለሞን? ምክንያቱም ሥጋችን፦
➀ኛ. የእግዚአብሔር ቤትና የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ስለሆነ።
★የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16-17
★ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20
★ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 2ኛ ቆሮ 6፥16
➁ኛ. ሥጋችን የክርስቶስ ብልት ስለሆነ።
★ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም። ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና።1ኛ ቆሮንቶስ 6፡15-16
➂ኛ. ብልቶቻችን ለእግዚአብሔር የጽድቅ ጦር ዕቃ አድርገን ማቅረብ ስላለብን።
★እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤ ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ሮሜ 6፡12-13
★ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ። ሮሜ 6፥19
➃ኛ.በዋጋ ስለተገዛን
★በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20
♦ወገኞቼ ዘመን ክፉ ነው። ብዙ አታላዮች አሉና እንጠንቀቅ እንጽና። በመጨረሻ ሐዋሪያው ጻውሎስ ለተወደደው ለልጁ የለገሰውን ምክር ለእናንተ ላካፍላችሁ።
❖ ዘመኑ ምንም ይሁን እናንተ ግን፦
➦መልካሙን የእምነት ገደል ተጋደሉ፣ ከዚህ ዓይነት ሐሰት አስተምህሮ ሽሹ።
✅አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል። መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡11-12
➦ኢየሱስን አጥባቃችሁ ተከተሉ።
✅“አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤” 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥10
➦እንደ ተማራችሁና እንደተረዳችሁት ፀንታችሁ ቁሙ ኑሩ።
✅“አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥14-15
♦በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበር እንድንችል ጌታ ፀጋውን ያብዛልን።

Comments
Post a Comment