ብልቶቻችን ለእግዚአብሔር እናቅርብ
-#ብልቶቻችን_ለእግዚአብሔር_የጽድቅ_የቅድስና ===☞#መሳሪያ_አድረገን_እናቅርብ☜===
============================
“ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።” ሮሜ 6፥13
✍ይህ ክፍል ምን እንደምናገር አንዳንድ ነገሮችን እንመለከታለን፡፡ እንዚህ የሚናያቸው ነገሮች በዚህ ትምህርት ላይ ጉል ምና ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ እንዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ማየት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ይህ ክፍል የሚከተሉትን ነጥቦችን ይናገራል፡፡
1) ይህ ክፍል ሁለት ዓይነት ተቀራኒ መንግሥታት እንዳሉ ይናገራል፡፡
1. እግዚአብሔርና ሰይጣን ወይም
2. ጽድቅና ዓመፃ ወይም ኃጢአት
2) ይህ ክፍል በሁለት ተቀራኒ መንግሥታት መካከል ጦርነት እንዳለ ይናገራል፡፡
በዚህ ክፍል "ጦር" የሚለው ቃል በቀጥታ ጦርነትን ያመላክታል፡፡ እንዚህ ሁለት ተቀራኒ መንግሥታት እስካሉ ድረስ መቼም ጦርነት እንደማይጠፋ በደንብ እንውቃለን፡፡ ጦርነት ደግሞ ያለው ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ሕዝቡና በሰይጣን ድያብሎስ መካከልም ነው፡፡ በዚህች ምድር እስካለን ድረስ ይህ ውጊያ ወይም ጦርነት እንዳለና የሚቀጥል መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል በኤፌሶን 6፥12 ላይ ይናገራል፡፡ "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” ይላል፡፡
3) ይህ ክፍል ለዚህ ጦርነት የሚቀርብ መሳሪያ እንዳለ ይናገራል፡፡
ጦርነትን መቼም ብሆን በባዶ እጅ የሚዋጋ ማንም ሰው፣ ቡዱን ወይም ሀገር የለም፡፡ ጦርነት ያለ ጦር መሳሪያ ወይም ያለ ጦር ዕቃ ፈፅሞ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው ወይም አንድ ቡዱን ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፍት በቅ የሆነ የጦር መሳርያ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ልክ እንደዚህ ለመንፈሳዊ ጦርነትም መሳሪያ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ክፍል እንምናየው ከሆነ ደግሞ ለጦርነት የሚቀርብ መሳሪያ እንዳለ ክፍሉ ይናገራል፡፡
4) ይህ ክፍል ለዚህ ጦርነት የሚቀርቡ መሳሪያዎች ምን እንደሆኑ በግልፅ ያስቀምጣል፡፡
✍እንዚህ መሳሪያዎች ብልቶቻችን እንደሆኑ የእግዚአብሔር ቃሉ "ብልቶቻችሁ" እያለ በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ ክፍል "ብልቶቻችሁን" የሚለው ቃል የተለያዩ የሰውነት የአካል ክፍሎችን በሙሉ ያመለክታል፡፡
በዚህ ክፍል ላይ ሁሉት ተቀራኒ የሆኑ ቃላቶችን እናገኛለን፡፡ እንዚህ ቃላቶች አቅርቡና አታቅርቡ የሚሉ ናቸው፡፡ እነዚህን እንደሚከተለው አንድ በአንድ እናያለን፡፡
☞☞☞ማቅረብ እና ከለማቅረብ☜☜☜
[===============]
1) አቅርቡ☞ማቅርብ
አቅርቡ የሚል ቃል በግልፅ የሚናገረው የሆነ የሚቀርብ ነገር እንዳለ ነው፡፡
1.1. ማቅርብ ያለብን ወይም የሚቀርብ ነገር ምንድ ነው?
በዚህ ቦታ በግልፅ እንደምናየው ከሆነ አቅርቡ የተባሉት ሁለት ዓይነት ነገሮች ናቸው፡፡
በመጀመሪያ ራሳችን ነው፡፡
ከምንም በላይ በቅድሚያ ማቅርብ ያለብን የራሳችን ሕይወት፣ ማኝነት ወይም በጠቅላላ ሁለንተናችን በሙሉ ነው፡፡ ለማንም ይሁን ቀድመን ራሳችን ካቀርበን በኃላ የቀራውን ማቅርብ ብዙም አይከብድም ምክንያቱም እጅግ አስቸጋሪው ነገር ራሳችን መሠጠት ወይም ማቅርብ ስለሆነ፡፡ አንድ ሰው ለላው ራሳን እንደመስጠት ያህል ከባዱ ነገር የለም ምክንያቱም ራሱን ማቅርብ ወይም ራሱን መሰጠት የፍቅር ሁሉ ጥግ ነው፡፡ “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።” ዮሐንስ 15፥13
በመቀጠል ብልቶቻችን ነው፡፡
ከራሳችን በመቀጠል ማቅርብ ወይም መሰጠት ያለብን ብልቶቻችን ማለትም የሰውነት አካል ክፍሎችን ወይም ሰውነታችን ወይም ስጋችን በመሉ ነው፡፡ ራሱን የሰጠ ሰው በምንም ሁኔታ ብልቶቹን መከልከል አይችልም፡፡ ውስጡን የሰጠ ውጭውም ደግሞ መሰጠቱን አይቀርም፡፡
1.2. ማቅርብ ያለብን ለማን ነው ወይም ለማን እናቅርብ?
ከላይ እንዳየነው የሚናቀርበው ነገር ራሳችንንና ብልቶቻችን እንደሆኑ አይተናል፡፡ ታድያ እንዚህ ነገሮች ለማን ይቀርባሉ? የሚቀበለውስ መነው? የእግዚአብሔር ቃል እንደምናገረው ከሆነ የሚቀርብ ነገር (የእኛ +የእኛ አካል) ለሁለት ወገን እንደሆነ ቃሉ በግልፅ ያሰቀምጣል፡፡ ከላይ በመግቢያው እንዳየነው እንዚህ ሁለት ወገኖች ሁለት ተቀራኒ መንግሥታት ናቸው፡፡ እንዚህ መንግሥታት እግዚአብሔርና ሰይጣን ናቸው፡፡ ስለዚህ የሚናቀርበው ለእንዚህ መንግሥታት ነው ደግሞ ተቀባዩም እነርሱ (እግዚአብሔር ወይም ሰይጣን) ናቸው፡፡ ስለዚህ
1ኛ) ራሳቻን ጠቅላላ ለእግዚአብሔር እናቅርብ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
በዚህ ክፍል ስናይ "ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ" የሚል ቃል ይገኛል፡፡ ይህ ክፍል በቀጥታ የምናገረው በሮሜ 12:1 ያለውን ቃል ነው፡፡ " እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።” ሮሜ 12፥1
ስለዚህ በመጀመሪያ ከምንም በላይ ማቅረብ ያለብን ራሳችን ወይም ማኝነታችን ነው፡፡
2ኛ) ብልቶቻችንን ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሣሪያ አድርገን እናቅርብ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
አሁን በዚህ ክፍል "ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።” የሚል ቃል ይገኛል፡፡ ይህን ቃል ደግሞ በ1ቆሮንቶስ 6:15፤ 19-20 ካለው ቃል ጋር ማየት እንችላለን፡፡ ቃሉ እንድ ይላል " 15 ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም።.....19-20 ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 6:15፤ 19-20" ደግሞ በለላ ሠፈራ “ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ።” ሮሜ 6፥19
አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውንና ብልቶቻቸውን ለእግዚአብሔር ማቅርብ ያልቻሉ ሰነፎች ሁል ጊዜ የሚያነሱት የቃል ክፍል አለ፡፡ በ1ኛ ሳሙኤል 16፥7 “እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው”፡፡ ነገር ግን ይህ ቃል ክፍል በፍጹም ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚሄድ አይደለም፡፡ ለሰዎች ይቅርና ለሰይጣንም ጭምር ጥቅስ አንዳለ ማወቅ አለብን፡፡ እንዚህ ዓይነት ሰዎች ግን ያላዎቁት አንድ ነገር አለ፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፡13 እና 15 መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤... 15 ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም።" ያለውን ቃል የዘነጉት ይመስላል፡፡ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል በማቴዎስ 22፥21 “የቄሣር ነው አሉት። በዚያን ጊዜ፦ እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው።” ይህ ክፍል በግልፅ የሚናገረው እኛ በክርስቶስ የዳነን በደሙ የተገዛን የእግዚአብሔር ብቻ መሆናችን ይናገራል፡፡ በምንም ሁኔታ ሥጋችን ፣ ሰውነታችን ወይም ብልቶቻችን ለሰይጣን ማቅርብ የለብንም፡፡ እኛም የራሳችን የሆነ ሁሉም ነገር የጌታና የጌታ ብቻ ነው፡፡ ለእኛ በእኛ ሕይወት ላይ ምንም ዓይነት ስልጣን የለም፡፡
✍የእግዚአብሔር ቃል በማቴዎስ 6፥2 “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።” እንደምለው ሁለ አንድ ሰው ራሱን ሆነ የራሱን አካል ወይም ብልቶችን ለሁለት ወገን ማቅርብ በፍጹም አይሆንም፡፡
☞ሁለት እግር አለ ተብለው ሰው በአንደ ሁለት ዛፍ እንደማይወጣ ሁሉ ፣ አንድ ተጨዋች መጨዋወት በመቻሉ በአንድ ጊዜ ለሁለት በዱን መጨዋወት እንደማይቻል ሁሉ አንድም ሰው ራሱን አካል ወይም ብልቶችሁን በምንም ታምዕር ለሁለት ወገን ማለትም ለእግዚአብሔር እና ለሰይጣን ማቅርብ አይችልም፡፡ ማንም ሰው ብሆን ብልቶችሁን ለእግዚአብሔር የጽድቅ ጦር ዕቃ አድርገው ማቅርብ አለበት፡፡ አፈር ወደ አፈር እስክመለስ ድረስ የትኛውም ሰው በአፈር እግዚአብሔርን ማክበር አለበት ምክንያቱም አፈርን የተጠረ ሰይጣን ሳይሆን እግዚአብሔር ስለሆነ ሥጋችን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ አለብን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በሮሜ 6፥12 “እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤” የሚለው ለዚህ ነው፡፡
✍ከላይ በኩል የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ቦታ እንደምናገረው አቅርቡ አታቅርብ ይላል፡፡ አቅርቡ አታቅርቡ የተባለው ምንድነው ስባል፦
1) ራሳችሁን ወይም ማንኝታችሁን እና
2) ብልቶቻችሁን ወይም ሥጋችሁን ነው፡፡ ለማን ስባል ደግሞ
✍ከሁለቱ ወገኖች መካከል ለአንደኛው ወገን ብቻ ማለትም
ለእግዚአብሔር☞ የጽድቅ ወይም የቅድስና ጦር ዕቃ አድርጋችሁ አቅርቡ ወይም
ለሰይጣን☞ የዓመፃ ወይም የኃጢአት ጦር ዕቃ አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡
ነገር ግን ለሁለቱም ወገን ማቅረብ ፈጽሞ የማይሆንና የማይቻል ነገር ነው፡፡ የጌታ ባርያ ፖስተር ታምራት ኃይለ " ወይ ለክርስቶስ ወይ ለሰይጣን....ሦስት መንገድ የለም" ብለው እንደዘመረው ሦስት መንገድ የለም፡፡ መሀል ተሳፋሪ አንሁን፡፡ ስለዚህ ዛሬ ምርጫው የእኛ ነው፡፡ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ወስኑ፡፡
ማኝነታችን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ያለብን ለምንድ ነው?
[===============================]
ከላይ በብዙ ቦታ የእግዚአብሔር ቃልን እንዳየነው ማኝነታችን ማለትም ራሳችንንና ብልቶቻችን ወይም ሥጋችን የጽድቅ ወይም የቅድስና መሳሪያ አድረገን ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንዳለብን በደንብ አይተናል፡፡ አሁን ደግሞ የምናየው ማኝነታችን ለእግዚአብሔር ለምን እናቀርባለን? ለምን ለሰይጣን አናቀርብም?
1) የእግዚአብሔር ስለሆነን
“እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።” ሕዝቅኤል 18፥4
2) የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስለሆነን
"16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 1 7ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።" 1ቆሮ 3:16-17
3) የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ስለሆነን
"ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?" 1ቆሮንቶስ 6: 19-20
4) በዋጋ ስለተገዛን
" በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም" 1ቆሮንቶስ 6: 19-20
5) ሥጋችን ለጌታ ስለሆነ
“ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤” 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥13
6) በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበረ ስላለብን
"ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።" 1ቆሮንቶስ 6: 19-20
7) ኃጢአት ሳይሆን እግዚአብሔርን ማንገስ ስላለብን
“እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤” ሮሜ 6፥12
ብልቶቻችን ለእግዚአብሔር የጽድቅ፣ ለሰይጣን የዓመፃ መሳሪያ የሚሆነው እንዴት ነው?
[=====================================]
✍የእኛ ብልቶቻችን እኛን ውብና ድንቅ አድርገው ለፈጠረው ለእግዚአብሔር የጽድቅ፣ የቅድስና መሳሪያ ወይም ጠላታችን ለሆነው ለሰይጣን፣ ለዓለም ወይም ለሥጋ የኃጢአት ፣ የዓመፃ መሳሪያ ሀነው እንዴት እንደምቀርብ እንመለከታለን፡፡ ለዚህም መነሻ እንድሆን አንዳንድ የሰውነት ክፍሎችን ወይም ብልቶቻችን በዝርዝር አስቀመጠን ማየት በጣም ጥሩ ይመስላል፡፡
1) አንደበት
ስለአንደበት የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ቦታ በጣም ትኩረት በመስጠት ስናገር እናያለን፡፡ ይህን ያህል የእግዚአብሔር ቃል ለምን ትኩረት እንደሰጠ ከያዕቆብ መልዕክት አራት ምክንያቶችን ከእንመለክታለን፡፡ እነዚህ ነጥቦች ያሉት በያዕቆብ 3:1-12
1ኛ. አንደበት ሥጋችን ሁሉ ሊመራ ወይም ሊቆጣጠር የሚችል ልጓም ነው፡፡
“እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።” ያዕቆብ 3፥3
በዚህ ክፍል አንደበት የተመሳሰለው ከፈረሰ ጋር ነው፡፡ ይህም ከኃይል ወይም ከጉልበት አንፃር ነው፡፡ በዓለማችን ትልቁ ጉልበት የፈረስ ጉልበት፡፡ ፈረስ እጅግ ኃይለኛ በጣም ጉልበተኛ ነው፡፡ ነገር ግን የሚገርመው ይህ ኃይለኛ ወይም ጉልበተኛ ፈረስን ሰጥ አድረገው መቆጣጠር የሚችል ትንሽ የሆነች ልጓም ናት፡፡ ፈረስን ያለ ልጓም ማንም ልቆጣጠር አይችልም ምክንያቱም ጉልበቱ በመክና ጉልበትም የላቀ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ኃይለኛ ብሆን ግን በትንሹው ልጓሞ ይቆጣጠራል፡፡ በዚህ ልጓም ሰው እንደፈለገው ያደርጋል፡፡
የእኛ ሥጋም ልክ እንደ ፈረስ እጅግ ኃይለኛ በጣም ጉልበት አለው፡፡ ብዙ ዓይነት ጥፋትን ልያስከትል ይችላል፡፡ ፈረስ በልጓም እንደምቆጣጠር ሁሉ ሥጋችን ልቆጣጠር የሚችል አንደበት ነው፡፡ ሰው አንደበቱን መቆጣጠር ከቻለ ሰውነቱን በትክክል መቆጣጠር ይችላል፡፡
2ኛ. እንደበት ሰውነታችን በአስቸጋሪ ሁኔታ በትክክል ሊመራ የሚችል መሪ ነው፡፡
“እነሆ፥ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ።” ያዕቆብ 3፥4
በዚህ ቦታ ደግሞ አንደበት የተመሳሰለው በመርከብ ጋር ነው፡፡ ይህም ከትልቅነት አንፃር ነው፡፡ መርከብ በጣም ግዙፉና ታላቅ ነው፡፡ አንዳንድ መርከቦች ከአንድ አነስተኛ ከተማ ይበልጣሉ፡፡ ነገር ግን የሚራመዱት አስቸጋሪ በሆነው ዐውሎ ነፋስና ወጀብ ባለበት ውኃ ላይ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን መርከብ ቀጥ አድርገው በትክክለኛው አቅጣጫ እንድጓዝ የሚያደርግ ትንሹው መሪ ናት፡፡
የእኛ ሰውነታችንም ልክ እንደ መርከብ ትልቅ ነው ምክንያቱም በውስጡ ብዙ ዓይነት ስሜቶች አሉ፡፡ ወደ ሕይወትም ወይም ወደ ሞት ወደ ጥፋት ሊመራ ይችላል፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ በጣም አስቸጋሪ የሆነ እኛን ሊያጠፋ የሚችል ዐውሎ ንፋስና ወጀብ አለ፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የመንፈሳዊ አቅጣጫ ሳይስት ሰውነታችንን ሊመራ የሚችል መሪ አንደበት ነው፡፡ ይህ መሪ የራሱን ሥራ ካቆመ መርከቡ ሊጠፋ ይችላል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው መርከቡ ለብቻው ሳይሆን ባለበቱን ጭምር ይዞ ይጠፋል፡፡
3ኛ. እንደበት ሕይወታችን በሙሉ ሊያጠፋ የሚችል እሳት ነው፡፡
“እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል። አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።” ያዕቆብ 3፥5-6
በዚህ ቦታ ደግሞ አንደበት የተመሳሰለው ከእሳት ጋር ነው፡፡ ይህም ከጥፋት አንፃር ነው፡፡ እሳት ምንም ትንሽ ብሆን እንኳን የማጥፋት ፣ የማቃጠል አቅም አለው፡፡
እንዲሁም አንደበትም ከሰውነት ክፍሎች በጣም ትንሽ ብሆንመን ግን ሥጋችን ሁሉ የማሳደፍ፣ የሕይወችን ሩጫ የመግታት፣ ከዛም አልፎ ሕይወታችን ወደ ገሃነም ሊወስድ የሚችል እጅግ ዐመፀና ዓለም ነው፡፡ አንደበት ትንሽ ናት ነገር ግን በሥጋ ሁሉ ላይ ትመካለች፡፡
4ኛ. አንደበት ሊገራ የማይችል አደገኛ የሆነች ብልት ናት፡፡
"የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤ ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።" ያዕቆብ 3:7-8
በዚህ ቦታ አንደበት የተመሳሰለው ከመግራት ጋር ነው፡፡ ይህም
ሰው እግዚአብሔር በሰጠው ሥልጣን መሠረት ፍጥረታትን በሙሉ ይገራል ወይም ይቆጣጠራል ነገር ግን ለሰው ልጅ ሁሉ እጅግ ያስቸገረው ነገር ብኖር የራሱን አንደበት መግራት ወይም መቆጣጠር አለመቻሉ ነው፡፡ ይህች አንደበት የሚገድል መርዝ ያላት ፣በጣም ክፉና ወላዋይ ብልት ናት፡፡ ይህችን መቆጣጠር ማለት ዓለምን መቆጣጠር ማለት ነው፡፡
5ኛ. አንደበት ምንጭ ናት
"10 ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። 11 ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን? 12 ወንድሞቼ ሆይ፥ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣም። ያዕቆብ 3: 10-12
በዚህ ቦታ ደግሞ አንደበት የተመሳሰለው ከምንጭ ጋር ነው፡፡ በትክክል ከተጠቀምንበት ጥሩ ምንጭ ካልሆነ ደግሞ መጥፎ ምንጭን የሚታፈልቅ ናት፡፡
የበረከትም የመረገምም፣ የሕይወትም የሞትም፣ የጣፋጭም የመራራም እና የልምላመም የጥፋትም ምንጭ ናት
አንደበት በውስጡ ምላስን፣ ከንፈርንንና ጥርስን ይዛል፡፡ እነዚህ ለማን እየቀረቡ ነው?
የሰውነት ክፍሎች
ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሳሪያ
ለሰይጣን የዐመፃ መሳሪያ
የቃሉ ክፍል
አፊ/አንደበት
ጻድቅ ፣ እውነተኛ አንደበት
ኃጢአተኛ፣ ተንኮለኛ፣ ሸንጋይ፣ጠማማ፣ ኃጢአተኛ፣ የሰነፎች አፈ
መዘምር ዳዊት
መጸሐፈ ምሳሌ
ምላስ
ጻድቅ፣ ፈዋሽ፣ እውነተኛ፣ ጠብብ ምላስ
ጠማማ፣ ሐሰተኛ፣ ሐመተኛ ምላስ
መጸሐፈ ምሳሌ
ከንፈር
እውነተኛ ብልሃተኛ
ሐሰተኛ ፀመፀኛ
ዳዊትና ምሳሌ
አይን
ትሁት ዓይን
ትዕቢተኛ፣ ሰነፍ ዓይን
መጸሐፈ ምሳሌ
ጆሮ
የሕይወትን ተግሣጽ የሚሰማ፣ ጠቢብ፣ ክፉ ነገርን የማትሰማ ጆሮ
የሕይወትን ተግሣጽ የማይሰማ፣ ጆሮ ጠቢና፣ ሰነፍ፣ ክፉ ነገርን ጆሮ
መጸሐፈ ምሳሌ
እጅ
ደምን የማታፈስ፣ ትጉና ታታር ጉቦን የማትቀበል የማትሰጥ እጅ
ደምን የሚታፈስ፣ ታካችና ሰነፍ፣ጉቦን የሚትቀብል የሚትሰጥ እንጅ
መጸሐፈ ምሳሌ
እግር
ወደ ክፉ የማትሮጥ እግር
ወደ ክፉ የሚትሮጥ አግር

Comments
Post a Comment