#አገልጋዮች_ውጤታማና_ፍሬአማ_አገልግሎት_ለማገልገል_በቅድሚያ_ማወቅ_ያለባቸው_ሦስት_ወሳኝ_ነጥቦች

_____-------ኤፌ 3፡7-9--------_________
❶ኛ. አገልጋዩ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ማወቅ አለበት።
  =============================
◉አንድ አገልጋይ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ማወቅ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጥ ጉዳዩ ነው። አንድ አገልጋይ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ካላወቀ ማገልገል ለብቻው ምንም ትርጉም የለውም።
◉ይህ ጉዳይ አግልግሎትና አገልጋይን ለይቶ ከማወቅ ጋር  የተያያዘ ነው። እጅግ በጣም ብዙ አገልጋዮች በአገልጋይና በአገልግሎት መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነትን ለይቶ እንኳን አያውቁም። በስሜ አገልጋይ ናቸው ነገር ግን አገልጋይ ማለት ምን ማለት ነው? አገልጋይ ማነው? አገልግሎት ምንድነው ተብሎ ብጠየቅ ተገቢውን ምላሽ መመለስ አይችሉም።

⭐በመሠረቱ አገልጋይ ማለት በጌታው ፊት የሚያገለግል ፤ በጌታው ፊት የሚመላለስ፤ በጌታው ፊት  የሚቆም ቅን ሎሌ ፡ አሽከር ፡ ባሪያ ፡ ገረድ ( ኢዮ ፯፡፪ )።

⭐አገልጋይ ማለት የስም ጉዳይ ሳይሆን  የመጠራትና የመለየት ጉዳይ  ነው።
 ✅ “ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።”— ሮሜ 1፥1-2

◉ዛሬ በእኛ ዘመን ከበፊቱ እጅግ በጣም በተሻለ ሁኔታ ብዙ ዓይነት አገልጋዮች አሉት። ይሁን እንጅ ያሉትን አገልጋዮች በሙሉ አገልጋይ ናቸው ብለን ለመናገር አያስደፍርም። ምክንያቱም ለብዙዎች አገልጋይ የሚመስል አገልግሎት አላቸው እንጅ አገልጋይን የሚመስል የአገልጋይ ሕይወት የላቸውም።
◉ይህ እንደዚህ የሆነበት ትልቁ ምክንያት አብዛኞቹ አገልጋዮች አገልግሎታቸውን ከመጀመር በፍት መቅደም የሚገባውን
ወሳኝ ነገርን አላስቀደሙም። ከአገልግሎት በፊት መቅደም ያለበት ወሳኝ ነገር ብኖር አገልጋይ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን ማወቅ ነው። ምክንያቱም በክርስትና ዓለም ላይ ከምንም በላይ የሚቀድመው አገልግሎት ሳይሆን የአገልጋይ ሕይወት ወይም ደግሞ አገልጋይ መሆን ማለትም አገልጋይ ሆኖ መገኘት ነው።

◉አገልጋይ መሆንና አገልጋይ ሆነው  መገኘት ከየትኛውም  ዓይነት አገልግሎት ይቀድማል። አገልጋይ መሆን ወይም አገልጋይ ሆኖ መገኘት ለአንድ አገልጋይ የሕልውና ጉዳይ ነው። ለአንድ አገልጋይ አገልጋይ መሆን ወይም ሆኖ መገኘት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው። አገልጋይ መሆን አለመሆን የሕይወት ጉዳይ ነው።
◉ራሱ አገልጋይ መሆኑን ያላወቀ አገልጋይ ዘወትር በፊቱ የሚታየው ማገልገል ብቻ እንጅ በአገልግሎቱና በሕይወቱ እግዚአብሔርን ስስማስደሰት ሆነ ስለማክበር የሚያውቀው ጉዳይ የለም። ለዚህ ነገር  ምንም ዴንታ የለውም።
 ✅ለእርሱ ትልቁ ስኬት የሚባለው አገልግሎትን ማካሄድ ነው። ለእርሱ ዋና ዓላማ ማገልገል ብቻ ስለሆነ እንደምንም ብሎ ማገልገል ከቻለ እንደ ትልቅ ስኬት ይቆጥራል። አገልግሎቱን እግዚአብሔር ተቀበለ አልተቀበለም፣ እግዚአብሔር በአገልግሎት ተደሰተ አልተደሰተም ለእርሱ ጉዳይ አይደለም።
◉ሩጫቸው ሁልጊዜ ከንቱ ነው። ለዚህ ነው የብዙ አገልጋዮች ዘመን በከንቱ እያለቀ ያለው። ለዚህ ነው ብዙ አገልጋዮች በማስመሰልና በልማድ ዘመናቸውን እየጨረሱት ያሉት። ከዚህም የተነሳ ብዙዎች አገልጋዮች አገልጋይ ይመስላሉ ነገር ግን አገልጋይ አይደሉም ማለትም በአገልግሎታቸው አገልጋይ ይመስላሉ ነገር ግን በሕይወታቸው አገልጋይ አይመስሉም። ምክንያቱም አገልጋይ መሆን ወይም ሆኖ መገኘትና አገልጋይ መምሰል እጅግ በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
★ዛሬ በዘመናችን ያሉት አገልጋዮች በሙሉ አገልጋይ አይደሉም። ሁሉም አገልጋዮች ጤናማ አገልጋይ ብሆኑ ኖሮ አሁን በምድራችን የሚከሰተው ችግርና መከራ አይከሰትም ነበረ።
✅ሁሉም አገልጋዮች አገልጋይ አለመሆናቸው በምን እናውቃለን?
 1) በሕይወታቸው እናውቃለን ።
===================
✅ሕይወታቸውንና አገልግሎታቸው በፍጹም አይገናኝም።
✅የኖሩትን አያገለግሉም ያገለገሉትን ደግሞ አይኖሩም።
✅አገልጋይ ሆኖ ሳይሆን መስሎ ይታያሉ። ለምሳሌ፦
▣ቅድስናስና የላቸውም ነገር ግን ስለቅድስና ይሰብካሉ፣ ይዘምራሉ፣ ወዘተ።
▣መታዘዝ የላቸውም ነገር ግን ስለመታዘዝ ይሰብካሉ፣ ይዘምራሉ፣ ወዘተ።
▣ትህትና የላቸውም ነገር ግን ስለትህትና ይሰብካሉ፣ ይዘምራሉ፣ ወዘተ።
▣ፍቅር የላቸውም ነገር ግን ስለፍቅር ይሰብካሉ፣ ይዘምራሉ፣ ወዘተ።
2) በእድገታቸው እናውቃለን ።
 =================
✅እንደ አገልግሎት ዘመናቸው ያህል የሚታይ፣ የሚያድግና የሚጨምር ሕይወትና እድገት የላቸውም።
 ✅በየጊዜው እየቀጨጨና እየቀነሰ የሚሄድ እድገት አላቸው።
3). በፍሬያቸው እናውቃለን
 ================
✅በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ፍሬአማ አይደሉም።
✅የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች በሕይወታቸው የላቸውም።
★ራሱ አገልጋይ መሆኑን ያወቀ አገልጋይ በአገልግሎቱ ውጤታማና ፍሬአማ ይሆናል። ይህን ያላወቀ አገልጋይ ግን በአገልግሎቱ ውጤታማና ፍሬአማ ልሆን አይችልም።
◉ሐዋሪያው ጻውሎስ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ያወቀ አገልጋይ ነው።“ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥12
◉እኛም ዛሬ ወደራሳችን ተመልሰን ራሳችን እንይ።  አገልጋዮች ነኝ? ወይስ አይደለንም? ስንቶቻችን ይህን ጥያቄ ራሳችን ጠይቀን እናውቃለን?

❷ኛ.አገልጋዩ ራሱ የምን አገልጋይ እንደሆነ ማወቅ አለበት።
==================================
◉በመጀመሪያ ደረጃ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ያወቀ አገልጋይ ቀጥሎ ማድረግ ያለበት የምን አገልጋይ እንደሆነ ማወቅ ነው። ይህ ራሱን አገልግሎት ለይቶ ማወቅ ወይም ደግሞ ለርሱ የተሰጠውን ፀጋ ሥጦታን ለይቶ ከማወቅ ጋር የተያያዘ ነገር ነው።
◉ሁሉም ሰው በአንድ አገልግሎት ዘርፍ አይሰማራም። እንደ ፀጋ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዱ አገልጋይ የራሱ የሆነ የአገልግሎት ዘረፉ አለው። አንድ አገልጋይ የራሱን የአገልግሎት ዘርፉን ካላወቀ በምንም ታአምር ውጤታማና ፍሬአማ ልሆን አይችልም።
► አንድ ተማሪ ተማረ ስለሆነ በሁሉም ትምህርት ዓይነት ውጤታማ አይሆንም። ነገር ግን በአንዱ ወይም በሁለቱ አልፎ ይሄዳል በዛውም እጅግ ውጤታማ ይይሰራል። ለዚህ ነው አንድ ተማሪ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት (ኮሌጅ ወይም ዩንቨርስቲ)  ስገባ አንዱን ትምህርት መርጦ በዛ ትምህርት ዘረፉ ውጤታማ ለመሆን ጠንክሮ የሚሰራው።
◉የራሱን አገልግሎት ዘርፈ ለይቶ ያላወቀ አገልጋይ ለራሱም ለሌሎችሁም ጭምር አደጋ ይሆናል።
►ለምሳሌ ያህል አንድ አገልጋይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው የአገልግሎት ዘርፉ ማለትም ፀጋ  ስጦታው ማስተማር ነው። ነገር ግን አገልጋዩ የራሱን ፀጋ ስጦታ ለይቶ ካለማወቅ የተነሳ የራሱ ያልሆነውን ያልተሰጠውን ነገር ግን የሚመኘውን ለምሳሌ ትንቢትን የራሱ ፀጋ ብሎ ይዟል።
◉ይህ አገልጋይ ራሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም አልፎ ቤተክርስቲያንም እጅግ በጣም ይጎዳል። ይህ አገልጋይ ለብዙ አገልጋዮች መንገድን ይዘጋል። እንዲሁም መዝጋት ባይችልም ሌሎች በራሳቸው መንገድ እንዳይሄዱ እንቅፋት ይሆናል። በስተመጨረሻ ራሱን ሌሎችም ጭምር ይዞ ገደለ ይገባል።
◉ሐዋሪያው ጻውሎስ ራሱን የአገልግሎት ዘርፉን ደንብ አውቆታል።  “እንደ ኃይሉ ሥራ እንደ ተሰጠኝም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ስጦታ መጠን የወንጌል አገልጋይ ሆንሁለት።”— ኤፌሶን 3፥7
◉እኛም ዛሬ የየራሳችን የአገልግሎት #field ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ይኖራል። ይህ የብዙዎች ችግርና ጥያቄ ነው። እርሱም የሚከተለው ጥያቄ ይሆናል።
◇የአገልግሎት ዘርፍ ወይም ጸጋ ስጦታዬ ምን እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
★ መንፈሳዊ ተሰጥዎአችንን ለማግኘት በተለያዩ መንገዶች መለየት ይቻላል።
✅የመንፈሳዊ ስጦታ ሙከራዎች ወይም ዳሰሳዎች፣ በጣም ሳንጠመድ ከተደረጉ ስጦታችን የት እንደሆነ እንድንገነዘብ በሚገባ ሊያሳዩን ይችላሉ።
✅ከሌሎች የሚገኝ ማረጋገጫም መንፈሳዊ ተሰጥዎአችን ምን እንደሆነ ሊያሳየን ይችላል። ጌታን ስናገለግል የሚያዩን ሌሎች ሰዎች ዘወትር መንፈሳዊ ስጦታችንን ሊለዩ ይችላሉ፣ እኛ በሚገባ ያልጨበጥነውን ወይም ያላስተዋልነውን።
✅ጸሎትም ደግሞ በጣም ጠቃሚ ነው።
✅ለምሳሌ በአንድ ፀጋ ስጦታ ላይ ስትሰራ ለዛ ነገር ሸክም መሰማት፣ ዘወትር ለማድረግ መፈለግ መጓጓት፣ የደስታና የሀሰት ስሜት መሰማት ስጦታው የአንተ ለመሆኑ ምልክቶች ናቸው።

❸ኛ.አገልጋዩ ራሱ ለምን የዛ አገልጋይ እንደሆነ ማወቅ አለበት።
==================================
◉አንድ አገልጋይ ራሱን ከማወቅ፣ የራሱን field ከማወቅ አልፎ በሦስተኛ ደረጃ ማወቅ ያለበት ትልቁ ጥያቄ ለምን የዛ አገልጋይ እንደሆነ ወይም ለምን ያ ስጦታ ለእርሱ እንደተሰጠ ነው።
◉ይህ ጉዳይ ዓላማውን ከማወቅ ጋር የተያያዘ ነው። ማነኛውም ዓይነት ሰው በየትኛውም ዘረፍ ይሰማራ ነገር ግን የተሰማራበት ዓላማን ካላወቀ በፍጹም ውጤታማ ልሆን አይችልም።
►አንድ ተማሪ ለምን እንደሚማር ካለወቀ በትምህርቱ ፍሬአማ ልሆን አይችልም።  ልክ እንደዛው አንድም አገልጋይ ለምን እንደሚያገለግል ካለወቀ በአገልግሎቱ ፍሬአማ አይሆንም።
◉ለምሳሌ
 ➥ዘማሪ፦እግዚአብሔር ለምን ዘማሪ እንዳደረገው ወይም የመዝሙርን ስጦታ ለምን እንደተሰጠው ማወቅ አለበት።
➥ነቢይ፦ እግዚአብሔር ለምን ነቢይ እንዳደረገው ወይም የነቢይነት ስጦታን ለምን እንደተሰጠ ጥንቅቆ ማወቅ አለበት።
➥ሌሎችም በዚህ መልክ ራሳቸውን መጠይቅና ለምን ያ ስጦታ ለራሳቸው እንደተሰጣቸው ማወቅ አለባቸው።
 ◉ሐዋሪያው ጻውሎስ ለምን የወንጌል አገልጋይ እንደሆነ አውቆታል። ጻውሎስ እግዚአብሔር ለምን የወንጌል አገልጋይ እንዳደረገው? ለምን ይህን ስጦታ ለእርሱ እንደሰጠው ሁለት ዓላማዎችን ያስቀምጣል።
➀ ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ — ኤፌሶን 3፥8-9
 ➁ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ— ኤፌሶን 3፥8-9
◉በተለያዩ አገልግሎት ዘርፍ ያላችሁ አገልጋዮች ራሳችሁን በደንብ መጠየቅ አለባችሁ።
➥ በእናንተ ሕይወት፣ በእናንተ አገልግሎት የእግዚአብሔር  ዓላማ ምንድነው?
➥ እግዚአብሔር አምላክ  ከብዙዎች መካከል መረጦ የፀጋው ባለቤት ስያደርግ የሰማዩ እቅድ ምንድነው?
➥እናንተ ዛሬ በዘመናችሁ ለአሕዛብ መስበክ ያለባችሁ የክርስቶስ ባለጠግነት ምንድነው?
➥እናንተ ዛሬ በአገልግሎታችሁ ለሰው ሁሉ መግለጥ ያለባችሁ የተሰወረው የእግዚአብሔር ምስጢር ምንድነው?
◉ ዛሬ ይህን ደንብ ማወቅ አለብን።  ዝንብለን አልመጣንም ዝንብለን አልተመረጠንም ስለዚህ ዝንብለን አንኖርም። በእኛ ሕይወት ለእግዚአብሔር ዓለም አለው።ለዓላማው ኖረን እንለፍ።
“ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤”  — ሐዋርያት 13፥36

Comments

Popular posts from this blog

መንፈሳዊ አገልግሎት

3ቱ የክርስቲያን ልብሶች

መንፈሳዊ እርጅና