የብርሃንና የጨው ማንነትን መግለጥ
13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። 14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። 15 መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። 16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5:13-16
->ይህ ክፍል የተራራው ስብከት በመባል የሚታወቅና በማቴዎስ ወንገል ውስጥ ከሚገኙት አምስት ታላላቅ ትምርቶች አንዱና የመጀመርያ ነው።
->ኢየሱስ ይህን አገልግሎት ያካሄደው በገሊላ ከተማ ሆነው ነው
->ጌታ ኢየሱስ ይህ ትምህርት ስያስተምር ሁሉት ነገር በምሳሌ አንስቷል። ጨውና ብርሃን።
1. ጨውን ለምድር።
1.1. ምድር ስባል ደግሞ
በምድር ላይ ያለው ፍጥረታት ሰውም ጭምር ስትሆን
1.2. በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ነገር ግን በሕይወታቸው ጣዕም ያጡ ሕይወት መራራ የሆነባቸው ናት።
2. ብርሃንን ለዓለም።
2.1. ዓለም ስባል ደግሞ አሁን በእኛ ዘመኔ ያለች በክፋትና በተንኮል የተሞላች ዓለም ስትሆን
2.2. ያልዳኑ ጌታ ኢየሱስን ያልተቀበሉ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች ወይም አሕዛብ ናት።
@=>ጌታ ኢየሱስ ለሎችን ብዙ ዓይነት ምሳሌ መጠቀም እየቻለ ለምንድ ነው ጨውና ብርሃን መጠቀም የፈለገው? @ምክንያቱም ሰው ያለ ጨውና ያለ ብርሃን መኖር አይችልም። ሰው በሕይወት ለመኖር ከእግ/ር በታች ጨውና ብርሃን ያስፈልጋሉ።
->እንደዚህ ሁሉ እኛም ለዚህች ምድርና ዓለም እናስፈልጋለን ምክንያቱም “የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።”ሮሜ 8፥19
~~~==>ሰው ያለጨውና ያለብርሃን መኖር እንደማይችል ቀጥለን እናያለን<==~~~~
1. ጨው/Salt፦Salt is a flavoring added to food to enhance and improve its flavor(ምግብን ለማጣፈጥ የምጨመረ ጣዕም ወይም መአዛ ነው)
©ሰው ያለምግብ መኖር አይችልም። ሰው በሕይወት ለመኖር የግድ የተመጣጠነ ምግብ ያሰፈልጋል። ምግብ ደግሞ ያለጨው ምግብ አይባልም ምክንያቱም ምግብ ያለጨው ጣዕም የለውም።ለምሳሌ ዶሮ ወጥ። ጨው ክብሩ ለምግብ ጣእም መስጠቱ ነው።
©ለምግብ ማጣፈጫ ሰዎች የሚጠቀሙበት የተለመደው ማዕድን ጨው ፣ በሥነ-ቅመማ ስሙ «ሶዲዮም ክሎ ራይድ» (NaCl)የተሰኘው ነው። ለጤንነት ይበልጥ ተፋላጊ የሆነውና ሃኪሞች በሚያሳስቡት መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀው ፣ አዮዲን (አዮዳይን)የተሰኘው ሌላ ማዕድን የተቀላቀለበት ነው። ለአንስሳትና ሰዎች ህልውና እጅግ ጠቃሚ መሆኑ የሚነገርለት ጨው ነው። ምግብን አጣፍቶ ለሰውነት ለአጥንትም ሆነ ለደም የሚጠቅም መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምግብ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያደርግ ነው።
2. ብርሃን/Light፦Light improves darkness, allows us to see with our eyes what could not be seen.
@ያለብርሃን የሰው ልጅ በፍፁም መኖር እንደማይቻል በሦስት አቅጣጫ እናያለን።
1.የዓለም ሁሉ ብርሃን የሆነው እውነተኛ ብርሃን አየሱስ/Jesus፦ለሰው ይህ ብርሃን ከሌለ ያ ሰው ሰው አይባልም ምክንያቱም በቁም የሞቴ ነው። በጨለማ በጠላት እጅ አለ።፡ /ዮሐ 8÷12/
2.የፀሀይ ብርሃን/Sun Light፦ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ለመኖር የፀሀይ ሃይል ያስፈልጋል። ይህ አስፈላጊ የሆነ ሃይል የሚገነው ከፀሀይ ብቻ ነው because The Primary Source Of Eneregy For All Living Thing Is Sun Light Which Is Called Solar Eneregy ነው።
3.Aritfical የሆነው ብርሃን means Electric Power፦አሁን በዝህ 21 ክፍሌ ዘመን፣ Technology እጅግ በጣም አስፈላግና ወሳይኝ በሆነበት ጊዜ መብራት ምን ያህል አስፈላግ እንደሆነ ከማንም የሚደበቅ አይደለም። እያንዳንዱ የሰው እንቅስቃሰ ከመብራት ጋር የተቆራነ ነው። ይህ መብራት የሰው እስትንፋስ ማለት ይቻላል። ይህን ለማወቅ ብዙም ሳንሄድ የግንቦት ወርን ማየት በራሱ በቅ ነው።
ጥያቄ፦ ሰው ያለጨውና ያለብርሃን መኖር እንደት ይችላል?
እሽ መኖር ካልቻለ ያለእኛስ ይህች ምድርና ዓለም መኖር ትችላለች?
መልስ፦=>ይህን ክፍል በደንብ እናውቃለን ነገር ግን ከማወቅ ያለፈ ስንቶቻችን ይህን ያህል አስፈላጊ መሆናችን እናውቃለን ደግሞ ስንትቻችን ይህ እናምናለን?
When(መቼ) we act as like salt and light በሌላ በኩል ደግሞ how many christain belive or trust they are salt of the earth and the light of the world. I Think እጅግ በጣም ትንሽ ናቸው። ያውቃሉ የሚሉትም ጭምር በተግባር ላይ zero ናቸው።
ያለጨውና ያለብርሃን ሕይወት መኖር እንደማትችል ሁላ ያለእኛ ይህች ምድርና ዓለም መኖር አትችልም። ለዚህች ምድርና ዓለም እኛ እጅግ በጣም እናስፈልጋለን። አሁን ሰዎች ላሉበት ችግር፣አሁን ምድራችን ላለችበት ሁኔታ እኛ አሁን ዓለማችን ላለችበት ምጥ መብትሄ የምንሆን እኛ ነኝ። ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ችግር መድሃንት መሆነ የሚንችለው ጨውና ብርሃን መሆናችን ማወቅ ብቻ ሳይሆን የጨዉና የብርሃን ሕይወት መኖር ወይም የእነርሱን ተግባር(function) Act ማድርግ ከምንም በላይ ትልቅ ቦታ ይዛል።
በነገራችን ላይ ጨውና ብርሃን መሆን ለእኛ ምርጫ አይደለም ግደታ ነው።(Being salt and light is not optional. Jesus did not say you can be salt and light or you have the potential to be salt and light. But He said that you are the salt of the earth and the light of the world.
->ጨውና ብርሃን መሆን አልፈልግም እንኳን ብትል በፍፁም አትችልም ምክንያቱም በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም(A town or A city that is set on an hill cannot be hidden) ማለትም እናንተ ከተማ ናቸው ለዛውም በትልቅ ተራራ ላይ ያለ ከተማ ናቸው ምክንያቱም በጣም የሚያፀባርቅ መብራት ከሩቅ ይታያል። ደግሞ አንድ አባባል አለ"ጨው ለራስ ስትል ጣፍጥ" አለበለዚያ ወደ ውጭ ተጥለ ትረገጣል።
=====>ኢየሱስ ለምን ይህን ያህል ለጨውና ለብርሃን ቦታ ሰጠ<======
1.------=====>ጨው<=====-----.1
®ጨው ካሉት ተፈላጊ ባሕርያትና ጥቅሞች አንጻር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መንገድ መጠቀሱ ምንም አያስደንቅም።
ይህ ጨው በጥንት ዘመኔ "ነጩ ወርቅ" የሚል ተቀጥላ ስም አግኝቶ በነበረው። በዚህ ጨው ምክንያት ብዙ ሀገራትና ነገሥታት ተዋግቷል። ለእርሱ ሲባል ሀገራት ጦርነት ተካሂደዋል።
®ጨው በዓለም ህዝብ ታሪክ፣ ለምግብ ማጣፈጫነት የረጅም ዘመናት ታሪክ ከመኖርም ባሻገር ጨው በዓለም ሕዝብ ታርክ በጣም ከፍ ያለ ቦታና ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነገር ነው። አሁንም ድረስ እጅግ ተፈላግ ነገር ነው። ለምሳሌ፦
->እንደ ጥንታዊት ኢትዮጵያ በመሳሰሉት አገሮች፥ የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ እንደ ገንዘብ ሆኖ አገልግሏል።
->በጥንታዊት ቻይና በዋጋ ረገድ ከወርቅ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ነበረው። የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ ጨውን ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው ዕቃ አድርጎ ሲመለከተው ቆይቷል።
->በጥንታዊት ጀረመን ነጭ ወርቅ ተብሎ የሚጠራና ጀረመንን በዓለም ኢኮኖም ከፍ ብላ እንድትቀመጥ ያደረገ ይህ ጨው ነው።
->በጥንታዊት ሮመ መንግሥት ለወታደሮች እንደ ደሞዝ የሚሰጠውም ይህ ጨው ነው
->በጥንታዊት ግርኮች ዘንድ እንደ መለኮታዊ ወይም እንደ እግዚአብር የሚታይም ይህ ጨው ነው
->ዛሬም ቢሆን በብዙ ሀገራት ዘንድ ጨው ቁስል የመሻርና ፀረ ሕዋሳት ባሕርይ እንዳለው የሚነግርለት።
እንዲሁም በምድር ዙሪያ ምግብ ለማጣፈጥና አንዳንድ ዕቃዎችን ሳይበላሹ ለማቆየት የሚያገልግልም ይህ ጨውነው።
~~__---ስለጨው አንድ ትልቅ እውነት አለ---___~~~
1. ይህ ጨው ይህን ያህል እጅግ በጣም አስፈላግ ነገር ብሆንም ግን አሁን ገበያ ላይ ካሉት ጋር ስናይ በዋጋ ትንሽ ነው። ተፈላግነቱን ያህል ዉድ መሆን አልቻለም።
አንድ ነገር አስቡ በጣም ተፈላጊ ናቸው =>ነገር ግን አሁን የእናንተ ተፈላጊነትና የእናንተ ዉድነት ለብዞች አልገባም፣ አልተረዱም። ለላው ይቅርና እናንተ እንኳን አላወቃቹም፣ አልተረዳቹም But You Are Very Expensive Just Like Diamond እና እንደ ወርቅ በጣም ተፈላግ ናቸው።
So We Are Expensive Like Diamond And Favorite Like Gold።
Diamond ከማይድናት ሁሉ እጅግ በጣም ወድ ስሆን ወርቅ ደግሞ እጅግ በጣም ተፈላግ ነው።
2. ይህ ጨው ይህን ያህል እጅግ በጣም አስፈላግ ብሆንም ነገር ግን በብዙ ሰዎች ዘንድ ጥሩ ቦታና እንክብካበ አይሰጥም። እንደ ለሎች በትልቅ ቦታ አይቀመጥም። ብዙ ጊዚ ኩሽና ላይ ይቀመጣል።
=>አሁንም አንድ ነገር አስቡ በጣም ውድና ተፈላጊ ናቸው ነገር ግን ለእናንተ ትልቅ ቦታ ላይሰጣችሁ ይችላል። ዋና ነገር ለምን ትልቅ ቦታ አይሰጥም ከማለት ይልቅ ዝም ብለ የአንተን የጨው ተግባር መወጣት አለብህክ። ያነ ተግባር ራሱ አንተን ከፍ ያደርጋል። ይህ ካልሆነ ኩሽና ላይ እንኳን አትቀመጥም ወደ ውጭ ትጣላሌ ከዛም ትረገጣሌ።
Diamond እጅግ በጣም ዉድ ደግሞ ወርቅ በጣም ተፈላግ ከመሆን በፍት የሚገኘው ከመሬት በታች በአለት ውስጥ። ከዚህ ተነስቶ በሰው አገንትና እጅ ላይ ሆኖ ዓለምን የሚዞረው።
3. ጨው ጣፋጭነቷን ለሁሉም ነው
የጨው ጣፋጭነቷ ወጥ ያለ ነው አትለዋወጥም።
ጨው ጣፋጭነቷን ለሁሉም እኩል ትሰጣለች።
=>ጨው በገባበት ምግብ ሁሉ ራሷን ተፅኖ ታሳድራለች።
ጨው ፍቅር ናት ዘር ጎሳ አትለይም ።
ክርስቶስ ተከታዮቹን ለምን በጨው መሰላቸው? ኢየሱስ በዓለም ውስጥ ላሉት ክርስቲያኖች እናንተ ጨውና ብርሃን ናቸው አለ?
1. ጨው ለጣዕም መስጫ ያገለግል። ጨው ምግብን ያጣፍጣል / ኢዮብ 6÷6/
ምግብ ለመበላት ሊጣፍጥ ይገባዋል፡፡ ምግብ የማይጣፍጠው ከሆነ ሰው ለመብላት አይፈልግም፡፡ ምግብን ለማጣፈጥ የሚጠቅመው ዋነኛው ነገር ደግሞ ጨው ነው፡፡ ጨው የምግብ ጣእምን ሰብሰብ የማድረግ አቅም አለው፡፡ ጨው የምግብ ጣእምን ወደ አንድ ደረጃ የማምጣት ችሎታ አለው፡፡
ልክ ከእግዚአብሄር ጋር በክርስቶስ የመስቀል ስራ እንደታረቅን ወደ መንግስተ ሰማያት ያልገባነው በምድር ላይ ወሳኝ ስራ ስላለን ነው፡፡ ስለ ተከታዮቹ ኢየሱስ ሲናገር የምድር ጨው ናችሁ ይላል፡፡
ክርስቲያኖችም በኃጢአት አልጫ የሆነውን ኅብረተሰብ ማጣፈጥ አለባቸው።
መራራ ሆና ጣዕም ትርጉም ላጣች ምድር ጨው መሆን አለብን።
2. ጨው ለመከላከልና ለማቆያ ያገለግላል።
ምግብ ለመበላት ሊጣፍጥ ይገባዋል (ሰው ለመኖር ምድር ምቹ መሆን አለባት)። ነገር ግን ምግቡ ጣፋጭነቱን ይዞ እንዳይቆይ የሚያደርግ ነገር አለ እርሱም ባክተርያና ፓንጋስ ነው። ይህ ባክተርያና ፓንጋስ ምግቡ እንድበሰብስ(decay)እንድሆን ያደርጋል (እኛ የምኖርባት ምድር ለሰው ልጅ ምቹ እንዳትሆን የሚያደርግ ጠላት አለ። ይህ ጠላት ምድር በኃጢአት፣በክፍት፣በተንኮል እንድትበሰብስና እንድትበላሽ ያደርጋል። ለምሳሌ ሰዎች ሥጋ እንዳይበላሽ በፍርጅ ያስቀምጣሉ። ፍርጅ የለላቸው ደግሞ በጨው ቀምመው ቋንጣ ያደረጉት ነበር።
ለምሳሌ ያህል የሙሴ ሕግ በመሠዊያው ላይ ለእግ/ር የሚቀርብ ማንኛውም መሥዋዕት በጨው መጣፈጥ እንዳለበት ያዛል። ( ዘሌዋውያን 2:13 ) እንዲህ ይደረግ የነበረው መሥዋዕት ለቀረቡት ነገሮች ጣዕም ለመጨመር ተብሎ ሳይሆን ጨው ከብክለት ወይም ከብልሽት ነፃ መሆንን ስለሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
በተመሳሳይ ሁኔታ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ይህች ምድር ጣዕሟን ይዛ እንድትቀጥልና ምቹ እንድትሆን ማድረግ አለብን።
መንፈሳዊ ምሳሌነት ያለው ሕይወት በመምራት በክፋት ለተሞላው ማኅበረሰብ መልካም መዓዛ እንጨምራለን። በተጨማሪም እግዚኣብሔር ክፋት እንዳይጨምርና ማኅበረሰቡ የበለጠ ክፉ እንዳይሆን ለመከላከል፥ በውስጡ ያሉትን ክርስቲያኖች እንጠቅማለን (በማስተማር፣በመምከር፣መንገድ በማሳየትና በመግፀፅ።
ራሳችንንም ለሎችንም ከመስበስበስ(decay) ከመሆን መጠበቅና መከላከል አለብን። ለምሳሌ ሥጋዊ ክርስቲያ
በፀሎት መከላከል እንችላለን
3. ጨው ቁስልን ለማድረቅ ያገልግላል።
እኛ ክርስቲያኖችም በኃጢአት፣በችግር፣በመከራ፣በሀዘን የቆሰለውን የተጓዳውን ሰውና ዓለም መፈወስ፣ማዳን፣ዳግም ሕይወት መስጠትና የወደቁትን ማንሳት አለብን። /ኢሳ 1÷5/
4. ጨው በጥንት ዘመን ገንዘብ ሆኖ ያገለግላል ፡፡
እኛ ክርስቲያኖችም የእግዚአብሔር ገንዘቦች ነኝ።/2ኛ ቆሮ 12÷14/
ስለዚህ የእግዚአብሔር ገንዘቦች መሆናችን አዉቀን ለየእግዚአብሔር ምቹ የክስ ገንዘብ መሆን አለብን።
5. ጨው በብሉይ ኪዳን ዘመን ለመሥዋዕት ይጨመር ነበር /ዘሌ 2÷13/
እኛ ክርስቲያኖችም መሥዋዕት እስከመሆን ድረስ ስለ ክርስቶስ መመስከርና ሕይወታችንም ጭምር ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለብን። /ፊሊጵ 1÷29/
6. ጨው በጠቅላላው ፍቅርን ያመለክታል /ማር 9÷50/፡፡
ፍቅር ለራሱ አይኖርም ለለላው እንጅ።
ጨው አልጫ ቢሆን የሚሰጠው ጥቅም እንደማይኖር ሁሉ ሰውም ያለፍቅር ጥቅም የለውም የተጣለ ነው።
ክርስቲያኖችም በክርስቶስ ሕግ ካልተመሩ ከንቱ ይሆናሉ፡፡
7. ጨው በሌላ መንገድ የቅጣት፣ የፍርድና የመርገም ምልክት ይሆናል፡፡ /ዘፍ 19÷26፣ መሳ 9÷45/፡፡
እውነተኛ ክርሰቲያናዊ ሕይወት የሌላቸው ክርስቲያኖች የመርገምና የቅጣት ምልክቶች ናቸው/ዕብ 6÷4-6/
ስለዚህ እኛ ክርሰቲያኖች እውነተኛውን ገፀ ባሕር መጫወት አለቸው።
~~~÷÷>ታድያ የምድር ጨው ከሆንኩ ከእኛ ምን ይጠበቃል?<÷÷~~~
ጨው የምግብን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው እኛ የምድርን የህይወት ደረጃ ከፍ ማድረግ አለብን።
እኛ እግዚአብሄርን የመፍራት ከፍ ያለ የህይወት ደረጃ ካላሳየን ምድር እግ/ርን መፍራት አትችልም። ስለዚህ እግ/ርን መፍራት በእኛ ሕይወት ማሳየት አለብን።
እግዚአብሄርን የመምሰል ህይወት ምሳሌ ካልሆንን ምድር የእግዚአብሄርን መልክ ማየት አትችልም፡፡ ስለዚህ ምሳሌ ሕይወት እንኑር።
እኛ እግዚአብሄርን ስለማክበር ሞዴል ካልሆንን እግዚአብሄር እንዴት እንደሚከበር ምንም ፍንጭ አይኖረውም፡፡ስለዚህ እኛ ሞዴል ሆነን እንገኝ።
በእግዚአብሄር ፀጋ በራስ የማይቻል ነገር በማድረግ እግዚአብሄር እንዳለ ካልመሰከርን ስለእግዚአብሄር መኖር የሚመሰክር ሰው አይኖርም፡፡
ጨው የምግብንን የተለያየ ጣእም እንደሚሰበስበውና አንድ ወጥ ጣእም እንደሚሰጠው እኛም የምድርን ትኩረት ወደ ሰማይ የምናመለክት መሆን አለብን።
እንዲሁም ከሞት በኋላ ህይወት አንዳለ አድርገን በመኖር ሌሎችንም የምናነቃውና ምድራዊ ህይወት ጊዜያዊ እንደሆነ አድርገን በመኖር ሌሎቹ ለዘላለማዊ ህይወት እንዲዘጋጁ የምናስጠነቅቀው እኛ ነን፡፡
በሰማይ ጌታ እንዳለው ሰው በመኖር ራስን በመግዛትና በዲሲፒን ኑሮ ክርስትና እንደሚቻል ፣ እግዚአብሄርን ማስደሰት እንደሚቻልና ለእግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ መኖር እንደሚቻል ለሌሎች ምሳሌ የምንሆነው መሆን አለብን።
ሰው በእግዚአብሄር አምሳል እንደተፈጠረና ለእግዚአብሄር ክብር እንደተሰራ በህይወታችን የምናመለክተው መሆን አለብን።
እግዚአብሄርን ማክበር የሰው በምድር ላይ የመፈጠር አላማ መሆኑን የምናስታውሰው እኛ ነን፡፡
ምድርን ከሚታይ ነገርና ከስጋዊ ፍላጎት ከፍ ያለን ደረጃ የምንሰጣት እኛ የምድር ጨው ነን፡፡
በምድር ላይ የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ ስለመኖር ለሌሎች የምንመሰክረው እኛ ነን፡፡
በምድር ላይ እግዚአብሄርንና ሰውን በመውደድ እንዴት እንደሚኖር የምንመሰክረው እኛ ነን፡፡
እኛ ነን አለምን ማጣፈጥ የምንችለው፡፡ አለምን ለማጣፈጥ ጣእሙ ያለን እኛ ነን፡፡ እኛ ግን ይህንን ወሳኝ ሃላፊነታችንን ካልተወጣን ማንም ሊሰራልን አይችልም፡፡
እኛ አለምን ካላጣፈጥን እኛን ሊያጣፍጠን የሚችል አለም የለም፡፡ ጨው ደግሞ ካላጣፈጠ ለምንም አይጠቅምም፡፡ ስለዚህ ነው ጨው በአለም ሁሉ መበተን ያለበት፡፡ ጨው በጨው እቃ ውስጥ ቢቀመጥ ምንም አይጠቅምም፡፡ ጨው ግን ተለያየ አይነት ምግብ ውስጥ ቢጨመር ያጣፍጣል፡፡ ክርስትናን ካለራስ ወዳድነት በፍቅር ለሌሎች መልካም ምሳሌ በመሆን ክርስትናን እንዲቀበሉ የምናበረታታው የምድር ጨው በመሆን ነው፡፡
2.-----=====>ብርሃን<=====-----.2
@ብርሃን ጨለማ በሆነው ነገር ላይ ሁሉ ያበራል። ያለብርሃን ዓለም ጨለማ ናት።
ብርሃን አስደናቂ ነገር ነው። አስደናቅ ከሚያደረጉት ነገሮች መካከል፦
ትንሽ ብርሃን ብዙ ጨለማ ትገፋለች። ብርሃን ትንሽ ብትሆንም በጨለማ ላይ ሥልጣን አላት። የክርስቲያኖች ምንም እንኳ በቁጥር ቢያንሱም ወይም ትንሽ ብሆኑም የክርስቶስን ባሕርያት በዓለም ውስጥ ማብራት አለባቸው። በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህን ክርስቶስ የጠቀሳቸውን ባሕርያት የያዙ ክርስቲያኖች ለሁሉም በግልጽ የሚለዩ ይሆናሉ። ምስክርነታችን የሚመጣው ከአፋችን ሳይሆን ከተግባራችን ነው
ብርሃን የጨለማ ተቀራኒ ናት። ብርሃን ከጨለማ ጋር ምንም ዓይነት ግንኝነት የለውም። የሰዎችን ክፋት አብርተን በማሳየት፥ ሕ ይወታቸውንና ማኅበረሰባቸውን በሚለውጥ መንገድ እንዴት ሊኖሩ እንደሚችሉ እናሳያቸዋለን፡ ነገር ግን ሕይወታችን ዓለምን በመምሰል በኃጢአት ከጨለመ፥ ይህ በማሰሮ ውስጥ እንዳለ መብራት ይሆናል። ወይም ደግሞ ስደትን ፈርተን ብርሃናችንን ብንደብቅ፥ እግዚአብሔር ጽድቁን ለማብራት እኛን የተጠቀመበት ዓላማ ከግቡ ሳይደርስ ይቀራል። 2ቆሮ 6:14። ከጨላማ ሥራ ጋር አለመተባበር። ጨለማ ማለት ክፋት፥ ተንኮል፥ ጥላቻ፥ ቂም፥ መለያየትና የመሳሰሉት ናቸው። ዮሃንስ ሲናገር “ወንድሙን የሚጠላ እስካሁን በጨለማ አለ። “ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥” ኤፌሶን 5፥11
ብርሃን ልተፋና ብርሃኑና ልታቆም ትችላለች። ስለሆነም መጠንቀቅና መዘጋጀት አስፈላግ ነው። ማቴ 25:1-12
~~__---ስለብርሃን አንድ ትልቅ እውነት አለ---___~~~
ብርሃን ለሁሉም እኩል ታካፍላለች እንጅ አታደላም።
ብርሃን የእኛ አለመሆኑን አወቀን ለሁሉም እኩል ማካፈል አለብን። ፍቅርን፣መልካምነትን፣etc
ብርሃን ለሁሉም እኩል ትደርሳለች እንጅ አትመርጥም።
ወገን ነው ሳንል ለሁሉም እኩል መድረስ አለብን።
ብርሃን ለሁሉም እኩል ሃይሏን ትሰጣለች እንጅ ለጥቅቶች ብቻ አይደለም።
ፀጋችን ለሁሉም መስጠት አለብን
ብርሃን በሁሉም ቦታ ታበራለች እንጅ ገደብ ወይም ወሰን የላትም።
ቤ/ያን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታ ብርሃናችን መብራት አለበት። በት/ቤት፣በሥራ ቦታ፣etc
ብርሃን ቀለም፣ጎሳ፣ ዘር አታቅም።
ዘራችን አፈር መሆናችን ማወቅ አለብን። በዚህ ጉዳይ ሙሉ ማለት እችላለው ክርስቲያን ውሸተኛ ነው።
ብርሃን ፍቅር ናት፣ብርሃን እናንተ ናት አቅፋ ሙቀት ትሰጣለች
(----====>የክርስቲያኖች ብርሃነት/ብርሃን መሆናቸው<===---)
1. ክርስቶስን ሲከተሉ ነው፡፡ /ዮሐ 12÷35-36/
ተራራ ላይ ያለን ከተማ እንደመሆናችን መጠን ሰዎች ስለምያዩ ክርስቶስን ስንከተለ ብርሃናችን ማብራት አለብን።
በተራራ ላይ የተሰራች ከተማ እንዲሁም በከፍተኛ መቅረዝ ላይ የተሰቀለ መብራት ከሩቅ ይታያና ሊሰወሩት አይችሉም፡፡ ክርስቲያኖችም በመልካም ስራቸው በሁሉ ዘንድ መታየትና መታወቅ ለአምላካቸውም መመስገን ምክንያት ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፦
እርሱ ምህረትን ይወዳል፥ እርሱ ፍቅር ነው። እርሱ ጠላቶች እያለን ወደደን ደግሞም ጠላቶቻችሁን ዉደዱ አለን። ማቴዎስ 5፡45
2. ቃሉን ሲያስተምሩ ነው፡፡ /ፊሊጵ 2÷15/
ከቃሉ ጋር ሕይወታቸውም ብናገር ምክንያቱም
ሰው ከቃሉ በፍት እኛን ስለምያይ
2. ላላመኑት መድኃኒት በመሆን ነው፡፡ /ኢሳ 49÷6 የሐዋ 13÷47/
He is telling his disciples that they are to go out into the world (dark with sin) and show them the way to God, to be a shining light on the path of life. They are to improve and enhance people’s lives through their actions.
“እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።”ማርቆስ 16፥15
18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። 19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28:18-10
Comments
Post a Comment