በፈተና የመደሰት ሚስጥር
#በፈተና_የመደሰት_ሚስጥር
||•×××××××××××××××××ו||
"ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት" ያዕቆብ 1፡2-3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
1ኛ. በዓለም እስካለን መከራ እንዳለ ማወቅ፡፡
××××××××××××××××××××××××××××××
“በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ" ዮሐንስ 16፥33
❖የሰው ልጅ በምድር የሚኖርበት ዘመን ሁሉ በፈተና የተሞላ ነው፡፡ ማነኛውም ሰው በምድር እስካለ ድረስ በልዩ ልዩ ፈተና ይፈተናል፡፡ ለሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ፈተና አለው፡፡ ፈተናው የሚለየው በመጠኑና በይዘቱ እንጅ ለሁሉም ሰው ፈተና ይኖራል፡፡ ክር በመርፌ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ሁሉ ሰውም በሕይወት ዘመኑ በፈተና ውስጥ ያልፋል፡፡ ከፈተና ነፃ የሆነና ሁለ በደስታ የሚኖር ማንም የለም፡፡ ለእንድ ሰው ሁሉም ነገር ይኖራል ማለት ፈተና የለም ማለት አይደለም፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ለሁሉም አንደ አቅሙ መጠን ፈተና ወይም መከራ አለው፡፡ ኢየሱስ ስለእኔ መከራን ተቀበለ አይደል ታዲያ ለምን የኢየሱስን እየተከተልኩ ፈተና ይበዛል? የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል“ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤” ፊልጵስዩስ 1፥29፡፡
2ኛ. መከራ በሕይወታችን ስደርስ አለመደነቅ፡፡
××××××××××××××××××××××××××××××
"ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፡፡" 1ኛ ጴጥሮስ 4፡12
❖አብዛኛው ጊዜ መከራ በእኛ ሕይወት ላይ ስደርስ እንፈራለን፣ እንደነግጣለን፣ ተስፋ እንቆርጣለን ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ስንፍና ንግግር እንናገራለን ፡፡ ብዙዎቻችን ፈተና ወይም መከራ ስመጣ አድስ ነገር እንደመጣ አድርገን ብዙ ነገር እንላለን፡፡ ምነው በእኔ ብቻ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር አያይም እና ወ.ዘ.ተ፡፡ ነገር ግን ሁለም ብሆን ማወቅ ያለብን በማንም ላይ ያልተከሰተ አድስ ፈተና በአንድ ሰው ብቻ ላይ አይከሰትም፡፡ ለባለቤቱ አድስ መስለው ብታይም ነገር ግን መከራው አድስ አይደለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከወሰደው መከራ ይልቅ ምንም አድስ መከራ የለም፡፡ እርሱ መከራችን በሙሉ ወስዷል፡፡ እኛን በፈተና ውስጥ እያየ ዝም የሚል አምልካ አይደለም እርሱ የሚራራ አባት ነው፡፡ “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።” ዕብራውያን 4፥15፡፡ በሰዎች ላይ ያልደረሰ ልዩ ፈተና እንደመጣ አድርገው ማሰብ ትክክል አይደለም፡፡ ፈተና በሰው ሕይወት ላይ የሚመጣው ደግሞ እንደ አቅሙ ነው እንጅ ሰው ከሚችለው ወይም ከአቅም በላይ አይደለም፡፡ “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13፡፡
3ኛ. መከራ ለጥቅማችን እንደሆነ መረዳት፡፡
××××××××××××××××××××××××××××
“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” ሮሜ 8፥28
❖ሰው በተፈጥሮ መከራን አይወድም፡፡ ከዚህ የተነሳ ብዙዎቻችን መከራን እንደ ክፉ ደግሞ እኛን ለማጥፋት እንደመጣ አድረገን እንወስዳለን፡፡ በዚህ ለመከራ ያለው አመለካከት እጅጉን የተበላሸ ነው፡፡ መከራን ወይም ፈተናን እንደ መልካም አጋጣሚ ወይም ለእኛ ጥቅም እንደመጣ አድ ረገን እንወስዳለን፡፡ በዚህ ለመከራ ያለው አመለካከት እጅጉን የተበላሸ ነው፡፡ መከራን ወይም ፈተናን እንደ መልካም አጋጣሚ ወይም ለእኛ ጥቅም እንደመጣ አድርገን መውሰድ በፍፁም አይሆንም፡፡ በእርግጥ መከራ ወይም ፈተና ሁሉ መልካም አይደለም፡፡ መከራ ወይም ፈተና መልካም የሚሆነው እግዚአብሔርን ለሚወዱትና እንደ ሃሳቡ ለተጠሩት ብቻ ነው፡፡ የፈተናን መልካምነት ወይም ክፉነት የሚወሰነው በአመጣጡ ወይም መከራው በሚከሰትበት በምንጩ ነው፡፡ የመከራና ፈተና በሰው ሕይወት ስከሰት በሁለት መልክ ነው፡፡
➊በራስ ምኞት ምክንያት፦ ይህ ከእግዚአብሔር ሃሳብና ዓላማ ወጭ ሰዎች በራሳቸው እጅ የሚያመጡት ከኋላም ብዙ ችግርን የሚያስከትል ከባድ ፈተና ነው፡፡ ፈተና ነው፡፡ “ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።” ያዕቆብ 1፥14
ለምሳሌ ዳዉትን፣ ሳምሶንን፣ ይሁዳን እና ብዙዎችን ማየት ይቻላል፡፡
➋በእምነት ምክንያት፦ እርሱም እግዚአብሔርን ለሚወዱትና እንደ ሃሳቡ ለተጠሩት እንደ የእግዚአብሔር ሃሳብና ዓላማ በሰዎች ላይ የሚከሰት ከኋላ ብዙ በጎ ነገርን የያዘ ፈተና ነው፡፡ በአብዛኛው ጊዜ ይህ ፈተና ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚመጣ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ማንንም በክፉ አይፈትንም እርሱ መልካም አምላክ ነው፡፡ “ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።” ያዕቆብ 1፥13፡፡ የእግዚአብሔር የሚፈትነው ሰዎቹን ሳይሆን የሰዎቹን እምነት ነው፡፡ ለምሳሌ አብራምን፣ ዮሴፍን፣ ኢዮብን፣እና ብዙዎችን ማየት እንችላለን፡፡
4ኛ. መታገስ
××××××××××
❖ከላይ በኩል ያየናቸው ሦስት ነጥቦች ልዩ ልዩ ፈተናን እንደ ሙሉ ደስታ ለመቁጠር የሚጠቅሙ ወሳኝ ነገሮች ናቸው፡፡ እነርሱ ምንም ወሳኝ ነገሮች ብሆኑም ነገር ግን ለብቻቸው አይጠቀሙም፡፡ በሕይወታችን ላይ የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መካራና ፈተናን እንደ ሙሉ ደስታ ለመቁጠር ትዕግሥት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
✍የጌታ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑትና በልዩ ልዩ መከራ ውስጥ ላሉት ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች በፈተና ውስጥ መደሰት እንዳለባቸው ይናገራል፡፡ ይህን ደስታን ማግኘት የሚትችሉት ደግሞ በትዕግስት እንደሆነም ያስቀምጣል፡፡ "ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት" ያዕቆብ 1፡2-3፡፡ ሐዋርያ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮ 8፥2 ላይ ስለቆሮንቶስ ሰዎች ስመሰክር “በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤” ይላል፡፡ በሌላ ቦታም ሐዋርያ ጰውሎስ አክለውም በ1ኛ ጴጥሮስ 4፡12-13 ላይ" ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።" በብዙ ቦታ የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው በመከራ ውስጥ እንድንደሰት ነው፡፡
4.1.ትዕግስት ከየት ይገኛል፡፡
×××××××××××××××××××××
✍ከእምነት መፈተን ፦ የእምነት መፈተን በትዕግስትን እንደሚያድርግ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል፡፡ በያዕቆብ 1፡2-3 ላይ "ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ" ፡፡ በለላ በኩል ደግሞ ሐዋርያ ጳውሎስ በ1ኛ ጴጥሮስ 1፥6-7 “በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።" ይላል፡፡ ከዚህ ቃል በትክክል ማወቅ የሚችለው የእምነታችን መፈተን መንፈሳዊ ፍሬ እንድናፈራ ያደርጋል፡፡ እርሱም ትዕግስት ነው፡፡
✍የእግዚአብሔር ቃል በምሳሌ 27፥21 ላይ “ብር በከውር ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል።” እንደሚል የሰው እምነትም በፈተና ወይም በመከራ ይፈተናል፡፡ የወርቅ ጥራት (quality) በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የእምነት አቋምም በፈተና ይፈተናል፡፡ ወርቅ በእሳት ወስጥ አልፎ የለበጠ ጠንካራ ወርቅ እንደሚሆን ሁሉ እምነትም በፈተና ውስጥ አልፎ ትዕግስት ያስገኛል፡፡
4.2.ትዕግስት በመከራ ውስጥ እንድንደሰት እንዴት ያደርጋል?
×××××××××××××××××××××××××××××××××××××××××
✍በብዙ መከራ የፈተነ እምነት ትዕግስትን ያስገኛል፡፡ ትዕግስት ደግሞ ደስታን ያስገኛል፡፡ ምክንያቱም፦
➊ ትዕግስት ሰውን ፍጹማንና ምሉዓን እንዲሆን ያደርጋል፡፡
"ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።" ያዕቆብ 1፡4
➋ትዕግስት በእግዚአብሔር ላይ ተስፋን እንድናደርግ ያደርጋል፡፡
“ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤” ሮሜ 5፥3-4
➌ትዕግስት መታዘዙን ያስተምራል፡፡
“ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤” ዕብራውያን 5፥8፡፡

Comments
Post a Comment