ምርጥ ዕቃ መሆን
●"በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል። ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል። ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤ የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።" 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡20-24
♦ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህን አስደናቂ መልዕክት የፃፈው እውነተኛ ልጁ ለሆነው በእምነት ለወለዳው ለተወደደው ለጢሞቴዎስ እንደሆነ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ላይ እናያለን።
♦ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህን መልዕክት ለልጁ ለጢሞቴዎስ የፃፈው፦
1) ጢሞቴዎስ ከሚጋፈጠው ስደት ባሻገር በእምነቱ እንዲበረታ ለማሳሰብ። በመጨረሻዎቹ ጥቂት ወራት ጳውሎስ ብቸኝነት ተጫጭኖት ነበር። ከጽሑፎቹ እንደምንመለከተው፥ ጳውሎስም እንደኛ ሰው በመሆኑ በአንዳንድ አማኞች ተግባራት ጥልቅ ስሜት ጉዳት ደርሶበት ነበር። ስደትን ከመፍራታቸው የተነሣ ይመስላል ብዙዎቹ የጳውሎስ የግል ጓደኞችና የአገልግሎት ተባባሪዎች ብቻውን ጥለውት ወደየቤቶቻቸው ገቡ። ጳውሎስ ከእስያ አውራጃ ሁሉም ሰው እንደ ተወው ይናገራል። ይህም በኤፌሶን አካባቢ የሚገኝ ስፍራ ሲሆን፥ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜያት ያገለገለበት ቦታ ነበር (2ኛ ጢሞ.1፡15)። አብሮት ያገለግል የነበረው ዴማስ ትቶት ሄደ (2ኛ ጢሞ. 4፡10)። እነዚህ ሰዎች በክርስቶስ ማመናቸውን ይተዉ አይተዉ የታወቀ ነገር የለም። ነገር ግን ጳውሎስ እጅግ በሚፈልጋቸው ጊዜ ትተውት መሸሻቸው በጥልቀት ጎዳው። ነገር ኝ እንደ ሉቃስ ያሉ ጥቂቶች አብረውት እስከ መጨረሻው ቆይተዋል (2ኛ ጢሞ. 4፡11)። የቅርብ ወዳጁ ጢሞቴዎስ እንኳን ከጳውሎስ ጋር ለመተባበር በመፍራቱ ምክንያት እምነቱን ለመደበቅ የሞከረ ይመስላል። ስለሆነም ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ስደትን እንዳይፈራና በእስራቱ ወይም የእስራቱና የሞቱ ምክንያት በሆነው ወንጌል እንዳያፍር ይነግረዋል (2ኛ ጢሞ. 1፡8)።
2) ጳውሎስ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለነበሩት ችግሮች ከሰማ በኋላ፥ ኔሮ ስደቱን እያጠናከረ ሲሄድና የሐሰት ትምህርቶች ሲስፋፉ ብዙ ሰዎች በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዳይተዉ ሰግቷል። በመሆኑም ጳውሎስ ጢሞቴዎስ የወንጌልን እውነት እንዲጠብቅ (2ኛ ጢሞ. 1፡14)፣ ተጨማሪ ስደት የሚያስከትልባቸው ቢሆንም (2ኛ ጢሞ. 1፡8፤ 2፡3) በአስቸጋሪ ጊዜያት ወንጌሉን መመስከራቸውን እንዲቀጥሉ (2ኛ ጢሞ. 4፡2) ለማሳሰብ ይፈልጋል።
3) ጢሞቴዎስ በጥንቃቄ ሊይዘው በሚገባው የእግዚአብሔር ቃል ላይ አገልግሎቱን በመመሥረት በእምነቱ እንዲጸና ለማበረታታት (2ኛጢሞ. 2፡15)።
♦ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚህ ክፍል ማለትም በምዕራፍ ሁለት ከቁ20-24 ልጁን ጢሞቴዎስን ምርጥ ዕቃ ሁን እያለ ምርጥ ዕቃ መሆን እንደምገባ ያሳስባል። በዚህ መሠረት፦
⭐በቁ.20 ላይ ቤትና ዕቃን፣ የዕቃ ዓይነቱንና ዕቃዎች በስንት እንደሚከፈሉ የተወሰኑ ነገሮችን ያስቀምጣል።
✅በዚህ ቦታ ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ አራት ዓይነት የዕቃዎች በቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ይናገራል። እነርሱም፦የእንጨት፣ የሸክላ፣ የወርቅ እና የብር ዕቃዎች ናቸው።
✅እነዚህ ዕቃዎች ደግሞ በሚሰጡት አገልግሎት አንፃር ወደ ሁለት ይከፈላሉ።
1.ለከበረ አገልግሎት የሚውሉ
2.ላልከበረ አገልግሎት ወይም ለውርደት የሚውሉ ናችሁ።
⭐በቁ.21 ላይ ከዕቃዎች መካከል ተለይቶ ምርጥ ዕቃ የሚሆን ምን እንደሚሆን አራት ነገሮችን ያስቀምጣል።
⭐ከቁ.22-24 ደግሞ ከዕቃዎች መካከል ምርጥ ዕቃ ለመሆን የሚፈልግ ማነኛውም ዓይነት ሰው ምን ማድረግ እንደሚገባ አሁንም አራት ነገሮች ይናገራል።
♦ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚህ ክፍል ትልቅ ቤት እያለ ለመግለጽ የፈለገው ቤት ምድራዊ ወይም ቁሳዊ ቤት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤት ነው። የእግዚአብሔር ቤት ደግሞ ሕንፃ ሳይሆን ሰው ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልዕክት የእግዚአብሔር ቤት እናንተው ራሳችሁ ናቸው በማለት ሰው የእግዚአብሔር ቤት እንደሆነ ይናገራል። "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።"1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16-17
❖የእግዚአብሔር ቃል በትንቢተ ኢሳይያስ 66፡1-2 ላይ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ" ይላል።
♦ጳውሎስ የሚናገረው ይህ ትልቅ ቤት የእግዚአብሔር ቤት ነው። በዚህ ትልቅ ቤት ውስጥ ደግሞ ምርጥ ዕቃ እንጂ ተራ፣ የማይጠቅም ወይም የተዋረደ ዕቃ አይኖርም። እንኳን በእግዚአብሔር ቤት ይቅርና በአንድ ሀብታም ቤትም ተራ ዕቃ አይኖርም። መቼም የአንድ ሀገር መንግሥት ቤት ላይ ተራ ዕቃ ከሌላ ደግሞ የእግዚአብሔር ቤት ላይ እንዴት ተራ ዕቃ ልኖር ይችላል? ለዚህ ነው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ ምርጥ ዕቃ ሁን እያለ የሚመክረው።
●ለመሆኑ ምርጥ ዕቃ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
♦ምርጥ ዕቃ መሆን ማለት፦
1) ለእግዚአብሔር የልብ ሰው መሆን ማለት ነው። ለምሳሌ እንደ ዳዊት
2) ለእግዚአብሔር ምቹ ሰው ማለት ነው። ለምሳሌ እንደ ሙሴ
3) ለእግዚአብሔር የክሱ ገንዘብ መሆን ማለት ነው። ለምሳሌ እንደ ነቢያት
4) ለእግዚአብሔርም ለሰውም ጠቃሚ ሰው መሆን ማለት ነው። እንደ ዮሴፍ
5) ለብዙዎች መትረፍ ማለት ነው። ለምሳሌ እንደ ኢየሱስ
6) እግዚአብሔርን የሚያደስት ኑሮ መኖር ማለት ነው።
7) የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ማለት ነው።
●ምርጥ ዕቃ የመሆን ጉዳይ እንዴት ነው?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
♦ምርጥ ዕቃ የመሆን ጉዳይ ያን ያህል የሚከብድ ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ስንፈጠር ምርጥ ዕቃ ሆነን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ስለተፈጠረን። እኛ የእግዚአብሔር ምርጦች ነኝ። ትንቢተ ኢሳይያስ 42፥1 “እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ” ይላል።
♦እንደዚህ ማንም አይልም እግዚአብሔር ግን ምርጦቼ እያለ ይጠራል። ሰው በተፈጥሮ ሸክላ ዕቃ ነገር ግን በልጁ በኢየሱስ በኩል ምርጥ አድርጎኛል። ምርጥ አድርጎ በዚህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ የከበረ መዝገብን ያስቀመጠ እግዚአብሔር ነው። ስንቶቻችን ይህን እናውቃለን? እግዚአብሔር ዛሬ ከእኛ የሚፈልገው የስም ምርጥነት ሳይሆን በተግባር የሚገለጽ ምርጥነትን ነው። ሰው ስም ብቻ ይዞ ምርጥ መሆን ካልቻለ ምን ጥቅም አለው።
♦ምርጥ ዕቃ የመሆን ጉዳይ፦
➥የቀለም (ቀይ ጠቁር) የመሆን ጉዳይ አይደለም።
➥የቁመት (ረዥም አጭር) የመሆን ጉዳይ አይደለም።
➥የብልግና (ሀብታም ደሀ) የመሆን ጉዳይ አይደለም።
➥የእውቀት (ማወቅ አለማወቅ) ጉዳይ አይደለም።
➥የእንጨት ወይም የሸክላ ዕቃ የመሆን ጉዳይ አይደለም።
➥የወርቅ ወይም የብር ዕቃ የመሆን ጉዳይ አይደለም።
♦ምርጥ ዕቃ የመሆን ጉዳይ የማንም ሳይሆን የሰውየው ወይም የባለቤቱ ጉዳይ ነው። ምርጥ ዕቃ ለመሆን የግድ የወርቅ ወይም የብር ዕቃ መሆን አይጠበቅበትም። በቃ ምርጥ ዕቃ የመሆን ጉዳይ የማመንና የመነሳት ጉዳይ ነው። አንድ ሰው ራሱ ምርጥ መሆኑን ካመነና ምርጥ ዕቃ ለመሆን ከወሰነና ከተነሳ የእንጨት ወይም የሸክላ ዕቃ ብሆንም ምርጥ ዕቃ መሆን ይችላል። ምክንያቱም በሸክላ ዕቃ ውስጥ የከበረ መዝገብን ያስቀመጠ ሰው ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የወርቅ ወይም የብር ዕቃ መሆን ማለት ምርጥ ዕቃ ማለት አይደለም። የወርቅም የብርም ዕቃ በራሱ ምርጥ ዕቃ መሆኑን ካለመነና አምኖ ካልተነሳ በስተቀር በፍጹም ምርጥ ዕቃ ልሆን አይችልም። እንዲሁም ተራና የማይጠቅም ዕቃ ልሆን ይችላል። አንዳንዶች የሉም ምርጥ ነገር አላቸው ነገር ግን ተራ ዕቃ የሆኑ?
●ምርጥ ዕቃ ለመሆን ምን እናድርግ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
●ምርጥ ዕቃ የመሆን ጉዳይ የግለሰቡ ጉዳይ ስለሆነ ምርጥ ዕቃ ለመሆን የሚፈልግ ማነኛውም ዓይነት ሰው የሚከተሉት አራት ነገሮችን ማድረግ አለበት።
1. ሰውየው ራሱ ምርጥ ዕቃ መሆኑን ማወቅና ማመን አለበት።
◈“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9
◈“እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤” ቆላስይስ 3፥12
♦ምርጥነት የማንነት ጉዳይ ነው። ሰው ራሱን ማንነት ካላወቀ እንሰሳ ይሆናል። ሰው ምንም ማጣት ይችላል ነገር ግን በምንም ታአምር ማንነቱን ማጣት የለበትም። ይህ ከሁሉም የከፋ ሞት ነው። በመሆኑም አንድ ሰው (ጌታ ያመነ) ይህንን እውነት ካለወቀና ካላመነ በዘመኑ ሁሉ ተራ ዕቃ ሆኖ ተራ ኑሮ እየኖረ በስተመጨረሻ ተራ ሞት ይሞታል።
2. ከክፉ ወጣትነት ወይም ከጎልማሳነት ምኞት መሸሽ አለበት።
◈“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ ”2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22
♦የራሱን ማንነት በደንብ የሚያውቅ ምርጥ ዕቃ ከማንም ጋር ዝንብሎ አይቀላቀልም። ምክንያቱም ምርጥ ዕቃ ነውና ራሱን ተራ ቦታ ላይ አያገኝም። ምሳሌ ዶክተር አብይ መጠጥ ወይም ሽሻ ቤት ላይ ታገኑታላችሁ? በፍጹም አታገኙትም። ለምን ምክንያቱም ራሱን ማንነት ያውቃል።
💠 ስለዚህ ምርጥ ዕቃ ለመሆን የሚፈልግ የማንኛውም ዓይነት ሰው ወይም ወጣት ራሱ ምርጥ መሆኑን ካወቀና ካመነ በኃላ ፈጥኖ ማድረግ ያለበት ከክፉ ከወጣትነት ምኞት መሸሽ ነው። ይህ ክፉ የወጣትነት ምኞት ሰውን ተራና የማይጠቅም ዕቃ የሚያደርግ አደገኛ ነገር ነው። ወጣት ከዚህ መሸሽ ካልቻለ ተራ ዕቃ የመሆን እድል እጅግ በጣም ሰፊ ነው። ለምሳሌ እናቶች በእርግዝና ወቅት ብዙ ነገር ይመኛሉ። ምንም እንኳን ምኞት ብኖራቸውም ለጽንሳቸው በደንብ ይጠነቀቃሉ። ምክንያቱም ያረገዙት ተራ አይደለም ልጅ ነው እንጅ።
3. ከሰነፎችና ካልተማሩ ከሞኞች መራቅ አለበት።
◈" ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤ የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።" 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡23-24
♦አንድ ምርጥ ዕቃ ለመሆን የሚፈልግ ማነኛውም ዓይነት ሰዉ ወይም ወጣት ከክፉ ከወጣትነት ምኞት መሸሽ ብቻ ሳይሆን ከሰነፎችና ካልተማሩ ከሞኞች መራቅ አለበት። እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ማንነት የረሱና ተራ ዕቃ የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰነፎች የሌሎችን ማንነትን ያበላሻሉ። እነዚህ ሰዎች ሌላ ሰው መሆን ይቅርና የገዛ ወንድሞቻቸው እንኳን ብሆኑ በምንም ታአምር ከእነርሱ ጋር ሕብረት ማድረግ የለባቸውም። አንድ ወጣት ከእነዚህ ጋር እስካለ ድረስ በፍጹም ምርጥ ዕቃ መሆን አይችልም። በዚህ ትዝ የሚለን የዝንብና የንብ ታርክ ነው። ምርጥ ዕቃ ለመሆን ውሎ በጣም ወሳኝ ነው። ስለዚህ ውሎ ዘወትር ከንቦች ጋር ይሁን።
4. ከቅዱሳን ወይም ከአማኞች ጋር ሕብረት ማድረግ አለበት።
◈“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22
♦ይህ ነው ከንቦች ጋር መዋል ማለት። ከቅዱሳን ጋር ሕብረት ማድረግ ምርጥ ለመሆን ከምንም በላይ ምርጥ ቦታ ነው።
➥ይህ ሕብረት በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደና መልካም የሆነ የእግዚአብሔር ፍቃድ ያለበት ሕብረት ነው። መዝሙር 133
➥ በዚህ ሕብረት ውስጥ በረከትና ሕይወት አለ።
◈“ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው። በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።" መዝሙር 133፥2-5
♦በዚህ ሕብረት ውስጥ ወጣቶች ማድረግ ያለባቸው ወይም አጥብቆ መያዝና መከታተል ያለባቸው አራት ነገሮች አሉት። እነዚህም ጽድቅ፣ ፍቅር፣ ሰላምና እምነት ናቸው። እነዚህን በንጹሕ ልብ አጥብቆ መከተል አለባቸው።
💠አንድ ወጣት በደንብ ማወቅ ያለበት አንድ ነገር ከላይ ያየናቸው መንገዶች ቀላል አለመሆኑን ነው። መስዕዋትነት ያስከፍላል። በዚህ ጊዜ ልመጣ ካለው ፈተና መካከል አንዱ የሰዎች ንግግር ነው።
💠ትላንት የአንተ ጓደኛ የነበሩ እነዛ ራሳቸውን ማንነታቸውን የረሱ ተራ ዕቃ ለመሆን ለወሰኑ ሞኞች በአንተ ላይ ብዙ ነገርን ልያወሩ ይችላሉ። ለዚህ አንድ ታርክ ልንገራችሁ። ዝሆንና ውሻ
●ምርጥ ዕቃ ምን ይሆናል?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
➀ ለከበረ አገልግሎት ይውላል።
➁ ለተቀደሰ አገልግሎት ይፈልጋል።
➂ ለእግዚአብሔርም ለሰውም ጠቃሚ ይሆናል።
➃ ዘወትር ለመልካም ወይም ለበጎ ሥራ ዝግጁ ይሆናል።

Comments
Post a Comment