ለእኛ የተሰጠንን ሕይወት እንኑር
#ለእኛ_የተሰጠንን_ሕይወት_እንኑር
▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪
⚫ለእኛ ከላይ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የተሰጠ፤ መኖር የሚገባኝ ውብና አስደናቂ ሕይወት አለ። በጣም ብዙዎቻችን አሁን እየኖረን ያለነው የእኛ ሕይወት አይደለም። ብዙዎቻችን ለእኛ ከተሰጠው ሕይወት ውጭ ተራ ሕይወት እየኖረን ነው። ከዚህ የተነሳ የብዙዎቻችን ሕይወት ትርጉም አልባና ጣዕም የሌለው ሆኗል። ይህ ጉዳይ ደግሞ ማንነትን ከመርሳትና የሕይወት ዓላማን ከመሳት ጋር የተያያዘ ነው። ይህ አካሄድ እጅግ በጣም ከአደገኛ የሆነ ሰውን በምድር ላይ ተራና የማይረባ ሰው ከማድረግም አልፎ ከእግዚአብሔር መንግሥትም ጭምር ማስቀረት የሚችል መጥፎ አካሄድ ነው።
⚫ይህን ርዕስ በማስብበት ወቀት የአንድ መዶሻ ታርክ ትዝ አለኝ። መዶሻው በመጀመሪያ የራሱን ሕይወት መኖር ያልቻለ በኃላ ግን የራሱን ማንነት ያገኘና ለእሱ የተሰጠውን ሕይወት መኖር የቻለ መዶሻ ነው። ታርኩን እነሆ፦
◆ሰውየው መዶሻን ከገበያ ገዝተው ካመጣ በኃላ ለጊዜው ሳይጠቀምበት በዕቃ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ያስቀምጠዋል። መዶሻውም የራሱን ሕይወት ሳይኖር በሳጥን ውስጥ ተቀምጦ ይቆያል። በዚህ ጊዜ መዶሻው ምነው ሳጥን ውስጥ ታስሬ ተቀመጥኩ በማለት ማሰብ ይጀመራል። ምክንያቱም እሱ የተፈጠረው በሳጥን ውስጥ ለመቀመጥ አለመሆኑን ስለሚያውቅ። ዕለት በዕለት ያለምንም ሥራ በሳጥን ውስጥ ታሽጎ መቀመጡ ያሳስበዋል። በውስጡ ምንም ያህል የሚያሳስበው ጉዳይ ቢሆንም ለምን ታሸጎ እንደተቀመጠ ምክንያቱን ሊደርስበት አልቻለም። የሆነ አንድ ችግር እንዳለ አውቆታል ነገር ግን ችግሩ ምን እንደሆን ማወቅ አልቻለም።
◆ከዕለታት አንድ ቀን ሰውየው መዶሻው ታሽጎ ከተቀመጠበት ሳጥን ውስጥ በማውጣት ለማገዶ የሚሆን እንጨት መቁረጥ ጀመረ። አሁን ያደረገው ተግባር ምንም እንኳ የእሱ ትክክለኛ ተግባር ባይሆንም ከታሸገበት ሳጥን ወተው ይህን ተግባር በማከናወኑ እጅግ ተደስቷል። ይሁን እንጂ እንደ ጅማሬው ደስታው አልቀጠለም ድጋሚ ከፋው። ምክንያቱም ቅርንጫፎችን መጨፍጨፍና ለማገዶ የሚሆን እንጨት መቁረጥ ተራ ክዋኔ እንጂ ከተፈጠረበት ዓላማና መኖር ከሚገባው ሕይወት ጋር የሚሄድ አይደለም። ስለዚህ አሁን ትክክለኛ ያልሆነ አንድ ችግር እንዳለ ይሰማው ነበር።
◆ይህ ከሆነም በኃላ በሚቀጥለውም ቀን ሰውየው ሌላ ነገር አደረገ። ይኸውም አንድ እግሩ ለተሰበረ ወንበር መቆሚያ ይሆን ዘንድ ድንጋይ ጠርቦ ለወንበሩ እግር ሰራለት። ይህ ተግባር ከቀድሞ የተለየ አድስ ተግባር ብሆንም በዚህም ተግባር ብዙም አልተደሰተም። ማንነቱንና ለእሱ የተሰጠውን ሕይወት በደንብ ስለሚያውቅ ሌላ የተሻለ ስራ ተመኘ። የተመኘውም ሥራ በዙሪያው የሚገኙትን መደብደብ፣ መጨፍጨፍ፥ መፈረካከስና መጠራረብ ፈለገ። ስለዚህ አንድ ነገርን ተረድቷል። እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት ከቶም ቢሆን ርካታን የሚሰጡት እንዳልነበሩ ለመገንዘብ ጊዜ አልፈጀበትም። ይብዛም ይነስ በሥራ ላይ የተሰማራ ቢሆንም በአገልግሎቱ ግን የእርካታ እጦት እያንገላታው ቆየ።
◆እንደገናም ከዕለታት በአንዱ ቀን ሰውየው መጣና ይዞት ሄዶ ምስማር መምታት ጀመረ። ወዲያውኑ ከመዶሻው ሕይወት ውስጥ የእሳት ብልጭታ ተፈጠረ። በዚያን ጊዜ እርሱ ለምን ዓላማ እንደተፈጠረና ለእሱ የተሰጠው ሕይወት ምን እንደሆነ ገባው። ላከ እሱ የተፈጠረውና መኖር የሚገባው ሕይወት ለማገዶ እንጨት መቁረጥ ወይም ድንጋይን መጥረብ ሳይሆን ምስማርን መምታት ነው። በዚህ ጊዜ በእርጋታ ሆኖ ከዚህ በፊት ሲመታቸው የነበሩትን ነገሮች ከአሁኑ ጋር እያነጻጸረ ነገሮችን ማሰላሰል ጀመረ። መዶሻው ሕይወቱን ሙሉ ሲፈልገው የነበረውን የተፈጠረለትን ዓላማና ለእሱ የተሰጠውና መኖር የሚገባውን ሕይወት አገኘ።
⚫ከዚህ የምንማረው አንድ ነገር ለእኛ ከተሰጠው ሕይወት ውጭ በምንኖርበት ጊዜ ሕይወታችን ምን ያህል ትርጉም አልባና አስቀያሚ እንደሚሆን ደግሞ ዓላማ ብሶች እንደሚያደርግ ነው። ስለዚህ ልክ እንደ መዶሻው ዓላማ ያለበት፣ ትርጉም ያለውና አስደሳች ሕይወት ማለትም ለእኛ የተሰጠውን ሕይወት ለመኖር እጅግ በጣም መፈለግ አለብን።
⚫ከዚህ በመቀጠል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የተሰጠውን ውብና አስደናቂውን ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚቻል ሁለት ነጥቦችን እናያለን።
1ኛው. የተሰጠንን ሕይወት ምን እንደሆነ ማወቅ ስሆን
2ኛው. የተሰጠንን ሕይወት ለመኖር መኖር ነው።
1. #ለእኛ_የተሰጠንን_ሕይወት_ማወቅ
▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪▪
⚫ለእኛ በተለይም ለክርስቲያኖች ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የተሰጠ መኖር የሚገባኝ ውብና አስደናቂውን ሕይወት አለ። ይህንን ሕይወት ለመኖር በቅድሚያ ለእኛ የተሰጠ ሕይወት ምን እንደሆነ አስቀድመን ማወቅ አለብን። ይህ ጉዳይ በቀጥታ ከማንነት ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው። ሰው የራሱን ማንነት ካለወቀ ለእርሱ የተሰጠው ሕይወት መኖር አይችልም። የእኛ ማንነት ለዚህ ለተሰጠው ሕይወት እንደሚሆን ተደርጎ በእግዚአብሔር አምላክ የተፈጠረ ማንነት ነው። ይህንን ማንነት ያገኘነው በራሳችን ተግባር ሳይሆን እንዲሁ በልጁ በክርስቶስ የተሰጠ ሕይወት ነው። ይህን እውነት ጠንቅቆ ማወቅ ለእኛ የተሰጠንን ሕይወት ለመኖር የሚያስችል ትልቅ እርምጃ ነው። ይህን እውነት ያወቀ ሰው ከአልችልም ባይነት ወደ እችላለሁ ባይነት፣ ከዶሮነት ወደ ንስርነት ይሸጋገራል። “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊልጵስዩስ 4፥13)። በተቃራኒው ደግሞ ይህንን እውነት የማያውቅ ሰው የንስር ማንነት ይዞ የዶሮ ሕይወት ይኖራል። ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ የተሰጠ ሕይወት ፍጹምና ሙሉ የሆነ ሕይወት ነው። ይሄውም በረከትን ከገዥነት ጋር፣ ገዥነትን ከስልጣን ጋር፣ ከፍታን ከሞገሰ ጋር ነው።
⚫ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ ከተሰጠው ሕይወት አራቱን ቀጥለን እናያለን።
1ኛ. #የበረከት_ሕይወት_ነው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
“እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥” ዘፍጥረት 1፥28
⚫እግዚአብሔር ለእኛ ከምንም በላይ አስቀድሞ የሰጠው ሕይወት የበረከት ሕይወት ነው። እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኃላ በመጀመሪያ ደረጃ ያደረገው ነገር ብኖር ባርኮት ነው። በእግዚአብሔር ተባርከናል። እንደ እኛ በእግዚአብሔር የተባረከ እንድም ፍጡር የለም ደግሞም አይኖርም። እግዚአብሔር ሁላችንም የባረከው በጎዶሎ በረከት ሳይሆን ፍጹምና ሙሉ በሆነ በሁለንተናዊ በረከት ነው። የተባረከነው በስጋዊ በረከት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊም በረከት ጭምር ነው። “በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።”(ኤፌሶን 1፥3)። እኛ ለበረከት እንጂ ለመርገም አልተጠራንም። ስለዚህ ደህነት፣ ጉስቁልና ማጣት ለእኛ የተሰጠ ሕይወት አይደለም።
⚫እነዚህ በረከቶች የተወሰኑት ብቻ ብንመለከት፦
✔በከተማ በገጠር ቡሩክ መሆን። ዘዳግም 28፥3
✔በሆድህ፥ በምድርህምና፥ በከብትህም ፍሬ ቡሩክ መሆን። ዘዳግም 28፥4፤11
✔በእንቅብህና ቡሃቃህ ቡሩክ መሆን። ዘዳግም 28፥5
✔በመግባትና በመውጣትህም ቡሩክ መሆን። ዘዳግም 28፥6
✔በጐተራና በእጅህ ሥራ ሁሉ ብሩክ መሆን። ዘዳግም 28፥8
✔ባለጠጋ መሆን። ዘዳግም 28፥12
✔በመንፈሳዊ ነገር መባረክ ለምሳሌ በሰላም፣ በእረፍት፣ በጤና እና ወዘተ። ኤፌሶን 1፥3
⚫ነገር ግን አሁን እየሆነና እየታየን ያለው ነገር ፍጹምና ከዚህ ተቃራኒ የሆነ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ሕይወት ነው።
2ኛ. #የገዥነት_ሕይወት_ነው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
“እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” ዘፍጥረት 1፥28
⚫እግዚአብሔር ለእኛ ሁሉንም እንዲሁ አሳልፎ ሰጠ። ይህን ሁሉ በረከት መውረሰ እንድንችል ከበረከቱ ጋር የገዥነትን ሕይወት ሰጠ። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከፈጠረ በኃላ ግዙ ብሎ ለመላእክት ሳይሆን ለእኛ ነው የሰጠው። በዚህም በምድር ያለውን ሁሉን የመግዛት፣ የመቆጣጠር፣ የመንከባከብ፣ ለእኛ ጥቅምና ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ የእኛ ኃላፍነት ነው። ይህን ማድረግ የሚችለው በረከት ያለው ሳይሆን የገዥነት ሕይወት ያለው ሰው። ሰው ምንም ያህል ብባረከ ገዥ ካልሆነ ሌላው በእርሱ ላይ ገዥ ይሆናል። ይህ እንዳይሆን እግዚአብሔር ለእኛ ከበረከት ጋር የገዥነት ሕይወት ስቷል። እኛ ለገዥነት እንጂ ለባርነት አልተፈጠረንም። ዛሬ ላይ እየታየና እየሆነ ያለው ነገር ፍፁሙ ተቃራኒ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው። ዛሬ ለብዙ ነገር ባርያዎች ሆነናል።
3ኛ. #ስልጣን_ሕይወት_ነው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⚫እግዚአብሔር አምላክ አዋቂ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ በረከትን ከገዥነት ጋር ብቻ ሳይሆን ከስልጣን ጋር የሰጠው ነው። ምክንያቱም ስልጣን የሌለው ገዥነት ምንም ጥቅም የለውም። እርሱ ባለው ነገር ገዥ ብሆንም ሙሉ ስልጣን ለሌላ ሰው ስለሆነ ስልጣኑ በጣም ውስን ነው። ይህ እንዳይሆን እግዚአብሔር የሰጠው ሙሉ ስልጣን ነው። ለእኛ የስልጣን ሕይወት ሰቶናል። ከላይ በኩል ከተዘረዘሩት ከሁለቱም ሕይወት በተለየ መልክ ይህ ሕይወት እጅግ በጣም የሚያስደንቅ ሕይወት ነው። ምናልባት ሰው በብዙ ልባረክ ይችላል፣ ምናልባት ሰው ዓለምን በሙሉ ልገዛ ይችላል፣ እንዲሁም ብዙ ዓይነት ስልጣን ሊኖርም ይችላል። ነገር ግን ለእኛ የተሰጠው ስልጣን እንዲሁ ተራ ስልጣን ሳይሆን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ብቻ የሚሰጥ እጅግ በጣም ልዩና አስደናቂ የሆነ የልጅነት ሰይጣን ነው። ይህንን ስልጣን ያገኘነው ልጁን ጌታ ኢየሱስ በማመን ነው። ይህንን ስልጣን ማግኘት የምንችልበት ዋነኛና ብቸኛ የሆነ መንገድ የእግዚአብሔር ልጅን የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ማመንና ግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ነው። “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤” ዮሐንስ 1፥12
⚫ከዚህ በልጅነት ስልጣን ውስጥ ካሉት ስልጣኖች የተወሰኑት፦
✔በአጋንንት ሁሉ ላይ ያለው ስልጣን፦ ሉቃስ 9፥1
✔እባቡንና ጊንጡ ላይ ያለው ስልጣን፦ ሉቃስ 10፥19
✔በርኩሳን መናፍስት ላይ ያለው ስልጣን፦ማርቆስ 6፥7
✔በደዌና በሕመም ላይ ያለው ስልጣን ፦ማቴዎስ 10፥1
✔በጠቅላላ የመንቀል፣ የማፍረስ፣ የማጥፋት፣ የመገልበጥ፣ የመስራት፣ የመትከል እና ወዘተ ስልጣኖች። ኤርምያስ 1፥10
⚫ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ይህን ስልጣን በአገባቡ እየተጠቀምን አይደለንም።
4ኛ. #የከፍታ_ሕይወት_ነው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⚫እኛ ማለት ምድር ላይ ሆነን በሰማያዊ ሰፍራ ከክርስቶስ ጋር በአብ ቀኝ የተቀመጥን የከፍታ ሕይወት የተሰጠን ድንቅ ፍጡሮች ነን። ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ የተሰጠ ሕይወት የበላይ እንጂ የበታች የመሆን፣ የቀንድ እንጂ ጅራት የመሆን፣ ከፍት እንጂ ከኃላ የመሆን፣ የከፍታ እንጂ ዝቅታ የመሆን ሕይወት አይደለም። ምክንያቱም ለእኛ የተሰጠው የዶሮ ማንነት ሳይሆን የንስር ማንነት ነው።
⚫ ነገር ግን አሁን እየኖረን ያለነው ሕይወት የዚህ ተቃራኒ የሆነ ሕይወት ነው።
“የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል።” ዘዳግም 28፥2 ለምሳሌ፦
2. የተሰጠንን ሕይወት ለመኖር መኖር።
⚫ለእኛ በተለይም ለክርስቲያኖች ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የተሰጠ መኖር የሚገባኝ ውብና አስደናቂውን ሕይወት አለ። ይህንን ሕይወት ለመኖር በቅድሚያ ለእኛ የተሰጠ ሕይወት ምን እንደሆነ አስቀድመን ማወቅ እንዳለብን ከላይ በኩል አይተናል። አሁን ደግሞ ለእኛ የተሰጠንን ሕይወት ለመኖር መኖር እንዳለብን ቀጥለን እናያለን።
⚫ለእኛ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን ውብና አስደናቂውን ሕይወት ለመኖር ሁለት ወሳኝ መስፈርቶችን የእግዚአብሔር ቃል በዮሐንስ 15፥7 ላይ ያስቀምጣል። እነዚህ መስፈርቶች፦
1) እኛ በእርሱ (በክርስቶስ) መኖር እና
2) የእርሱ (የክርስቶስ) ቃል በእኛ መኖር ነው።
⚫እነዚህን ሁለት መስፈርቶችን በትክክል ስንፈጽም እርሱ (ክርስቶስ) ራሱ በእኛ ይኖራል። እኛ ደግሞ ለእኛ የተሰጠውን ሕይወት እንኖራለን።
“በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።...በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።” ዮሐንስ 15፥4-7
⚫ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ የተሰጠውን ሕይወት ለመኖር ማለትም፦
1. የበረከት ሕይወት ለመኖር
◆#እንስጥ።
➥“ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።” ሉቃስ 6፥38
✔በመጀመሪያ ሕይወታችንና ማንነታችን እንስጥ። በመቀጠል እውቀታችን፣ ሀብታችንና አቅማችን ወይም ጉልበታችን እንስጥ።
◆#እንታዘዝ_ትዕዛዙን_እንጠብቅ።
➥“እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።” ዘዳግም 28፥1፤ ዘዳግም 15፥4-5፤ ዘሌዋውያን 26፥3
◆#እንስማ።
➥“የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል።” ዘዳግም 28፥2
➥“ቢሰሙ ቢያገለግሉትም፥ ዕድሜአቸውን በልማት፥ ዘመናቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ።” ኢዮብ 36፥11
2. የመግዛት ሕይወት ለመኖር
◆#እንገዛ
➥“እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤” ያዕቆብ 4፥7
➥ለእግዚአብሔርና ለቃሉ ብቻ ሳይሆን ለሰዎችም እንገዛ።
➥ ሁሉንም ለመግዛት እኛ አስቀድመን ለእግዚአብሔር መግዛት አለብን።
➥ ሁሉንም ለመቆጣጠር እኛ አስቀድመን በእግዚአብሔርና በመንፈስ ቁጥጥር ስር መዋል አለብን።
3. የስልጣን ሕይወት ለመኖር
➥የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችን እናረጋግጥ።
➥ የራሳችን ማንነት እንወቅ።
➥ባለስልጣኖች መሆናችንን እናምን።
➥ስልጣን በአግባብ እንጠቀም።
4. የከፍታ ሕይወት ለመኖር
➥ትሁታን እንሆን። ምሳሌ 11፥2
➥ያለልክ ዝቅ ዝቅ እንበል። ፊልጵስዩስ 2፥9
➥በእግዚአብሔር ፍት ራሳችን እናዋርድ። ያዕቆብ 4፥10፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፥6

Comments
Post a Comment