ሳንሰራ በአዳም___ሳንሰራ በኢየሱስ



  • ሳንሰራ በአንዱ(በአዳም) ምክንያት ሞትን ፣ ሳንሰራ በአንዱ(በክርስቶስ) ምክንያት ህይወት አገኘን
  • ሳንሰራ በአዳም ተኮነንን ፣ ሳንሰራ በኢየሱስ ፀደቅን
  • ሳንሰራ በአዳም ሙታን ሆንን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ሕያዋን ሆንን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ተኮነንን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ፀደቅን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ተረገምን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ተባረክን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ተቅበዘበዝን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ አረፍን!!
  • ሳንሰራ በአዳም አለመታዘዝ ሀጥያተኞች ሆንን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ መታዘዝ ፃድቃን ሆንን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ወደቅን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ተነሳን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ጠፋን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ተገኘን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ጠወለግን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ለመለምን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ተሸነፍን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ አሸነፍን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ሞት ነገሰብን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ በሕይወት ነገስን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ቆሰልን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ተፈወስን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ባሮች ሆንን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ልጆች ሆንን!!
  • ሳንሰራ በአዳም ጠላቶች ሆንን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ ወዳጆች ሆንን!!
  • ሳንሰራ በአዳም በጨለማ ኖርን ፣ ሳንሰራ በክርስቶስ በብርሃን ኖርን!!

Comments

Popular posts from this blog

መንፈሳዊ አገልግሎት

3ቱ የክርስቲያን ልብሶች

መንፈሳዊ እርጅና