Posts

Showing posts from September, 2021

እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ

 #ሰዎች በክርስትና ሕይወት እየቀነሱ ወይም ወደኃላ እየተመለሱ ወይም ደግሞ እየወደቁ እንዳሉ የሚያሳዩ አራት ዋና ዋና ምልክቶች፦ ❶ የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ፥ ለማጥናትና ለመጸለይ ያለው ፍላጎት ከቀን ወደቀን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ይመጣል። ❷ ከአማኞች ወይም ከቅዱሳን ጋር መንፈሳዊ ሕብረት የማድረግ፣ አንድ ላይ የመሆን፣ እግዚአብሔርን በጋራ የማምለክ ፍላጎት ከቀን ወደቀን እየወረደ ይመጣል። ❸ በመንፈሳዊ ሕይወት ጠንክሮ ወደፊት የመቀጠል፣ የማድግ ወይም ደግሞ የመጨመር ፍላጎት ቀስ በቀስ እየጠፋ ይመጣል። ❹ ለጥፋቱና ለድክመቱ ዘወትር ምክንያት ይደረድራል ካልሆነ ደግሞ ስለሌሎችን ተጠያቂ ያደርጋል።