መንፈሳዊ እርጅና

#መንፈሳዊ_እርጅና ◆◆◆◆◆◆◆ 📌መንፈሳዊ እርጅና፦በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚከሰት እርጅና ዓይነት ስሆን የክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ሕይወትን በኃይልና ሁኔታ የሚያጠቃ፣ አልፎም መንፈሳዊ ሕይወትን እስከመግደል የሚደርስ አደገኛ ነገር ነው። 📌መንፈሳዊ እርጅና፦የክርስቲያን መንፈሳዊ ሁለንተናን የሚቆጣጠር፣ መንፈሳዊ አቅምን የሚያሳጣ ሰውን ተራ ክርስቲያን የሚያደርግ አደገኛ የሰይጣን #System ነው። #መንፈሳዊ_እርጅናና_ተፈጥሮአዊ_እርጅና ◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆ 📌መንፈሳዊ እርጅናን ከተፈጥሮአዊ እርጅና ጋር የሚያመሳስላቸውም የሚያለያያቸውም ብዙ ነገሮች እሉት። ለምሳሌ 📌ሁለቱም እርጅናዎች ከጤና ችግር ጋር ተያይዞ ይመጣሉ። ♦ለሰው ልጅ ከምንም በላይ ጤንነት እጅግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነገር ነው። ሰው በሕይወት ለመኖር ከየትኛውም ነገር በላይ ጤንነት ያስፈልጋል። ሰው ጤናማ ካልሆነ በሽተኛ ይሆናል። በሽተኛ ከሆነ ደግሞ ጊዜውን ያልጠበቀ እርጅና ይመጣል። ጊዜውን ያልጠበቀ እርጅና ተከትሎ ደግሞ ጊዜውን ያልጠበቀ ሞት ይመጣል። ለሁለቱም እርጅናዎች ላይ ጤንነት ጉልህ ምናን ይጫወታል። ✔#ጤንነት ስባል ከበሽታና ከህመም ስሜት ብቻ ነፃ መሆን አይደለም፡፡ ጤና የተሟላ #አካላዊ፣ #ስሜታዊ፣ #መንፈሳዊ እና #ማኀበራዊ ደህንነት ነው፡፡ መጀመሪያ ይሄ ግንዛቤ ውስጣችን ሊኖር ይገባል፡፡ አንድ ሰው አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጤንነቱ በሙሉ ተሟልቶ ሲገኝ ነው ሙሉ ጤነኛ ነው ልንል የምንችለው፡፡ እነዚህ ሁሉ ባልተሟሉበት ሁኔታ ውስጥ አንድ ሰው ህመም ስለማይሰማው ብቻ ጤነኛ ነው ሊባል ግን አይችልም፡፡ ሙሉ የሆነ የአካል፣ የስነልቦናዊ እንዲሁም የማኀበረሰባዊ ደኀንነት ነው::” ይለዋል፤ ይህም ሲባል የ...