Posts

Showing posts from April, 2020

የብርሃንና የጨው ማንነትን መግለጥ

13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። 14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። 15 መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። 16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።   ማቴዎስ 5:13-16 ->ይህ ክፍል የተራራው ስብከት በመባል የሚታወቅና በማቴዎስ ወንገል ውስጥ ከሚገኙት አምስት ታላላቅ ትምርቶች አንዱና የመጀመርያ ነው። ->ኢየሱስ ይህን አገልግሎት ያካሄደው በገሊላ ከተማ ሆነው ነው ->ጌታ ኢየሱስ ይህ ትምህርት ስያስተምር ሁሉት ነገር በምሳሌ አንስቷል። ጨውና ብርሃን። 1. ጨውን ለምድር። 1.1. ምድር ስባል ደግሞ በምድር ላይ ያለው ፍጥረታት ሰውም ጭምር ስትሆን 1.2. በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ነገር ግን በሕይወታቸው ጣዕም ያጡ ሕይወት መራራ የሆነባቸው ናት። 2. ብርሃንን ለዓለም። 2.1. ዓለም ስባል ደግሞ አሁን በእኛ ዘመኔ ያለች በክፋትና በተንኮል የተሞላች ዓለም ስትሆን 2.2. ያልዳኑ ጌታ ኢየሱስን ያልተቀበሉ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች  ወይም አሕዛብ ናት። @=>ጌታ ኢየሱስ ለሎችን ብዙ ዓይነት ምሳሌ መጠቀም እየቻለ ለምንድ ነው ጨውና ብርሃን መጠቀም የፈለገው? @ምክንያቱም  ሰው ያለ ጨውና ያለ ብርሃን መኖር አይችልም። ሰው በሕይወት ለመኖር ከእግ/ር በታች ጨውና ብርሃን ያስፈልጋሉ። ->እንደዚህ ሁሉ እኛም ለዚህች ምድርና ዓለም እናስፈልጋለን ምክንያቱም “የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ...

ዘወትር በሕይወታችን እሳት ይንደድ

Image
#ዘወትር_ከሕይወታችን_እሳት_አይጥፋ ☞እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ የሚቃጠለው የመሥዋዕቱ ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ ባለው እንጨት ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስኪጸባ ድረስ ይሆናል፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፡፡ ካህኑም የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ በሥጋው ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል። ልብሱንም ያወልቃል፥ ሌላም ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ተሸክሞ ከሰፈሩ ንጹሕ ስፍራ ወደ ሆነ ወደ ውጭ ያወጣዋል። እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል። ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም። ዘሌዋውያን 6፡8-13 ✍ከዚህ ክፍል በደንብ ማየት የሚንችለው አንድ ነገር አለ፡፡ በዚህ ቦታ ብቻ ትኩረት ተሰቶ ሦስት ጊዜ ያህል ተደጋግመው ተገልጿል፡፡ ይህም  እግዚአብሔር ለሕዝብ ደጋግመው አፅንኦት ሰቶ የተናገረው ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ጉዳይ ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነደድ አይጥፋ የሚል ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሕዝብ የሚፈልገው ነገር ብኖር አንዱ ከመሠዊያ እሳት እንዳይጠፋ ነው፡፡ ✍ይህን ያህል እግዚአብሔር አፅንኦት ሰተው የተናገረበት ትልቁ ምክንያት ➊ እርሱ ራሱ እሳት ስለሆነ ሕዝቡም ማኝነቱን አውቋት እንድያመልኩት፡፡ “አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።”  ዘዳግም 4፥24 “አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።”  ዕብራውያን 12፥29 ➋ ከእርሱ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለሆነ ...

ብልቶቻችን ለእግዚአብሔር እናቅርብ

-#ብልቶቻችን_ለእግዚአብሔር_የጽድቅ_የቅድስና ===☞#መሳሪያ_አድረገን_እናቅርብ☜=== ============================ “ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።”  ሮሜ 6፥13 ✍ይህ  ክፍል ምን እንደምናገር አንዳንድ ነገሮችን እንመለከታለን፡፡ እንዚህ የሚናያቸው ነገሮች በዚህ ትምህርት ላይ ጉል ምና ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ እንዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ማየት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ይህ ክፍል የሚከተሉትን ነጥቦችን ይናገራል፡፡ 1) ይህ ክፍል ሁለት ዓይነት ተቀራኒ መንግሥታት እንዳሉ ይናገራል፡፡ 1. እግዚአብሔርና ሰይጣን ወይም 2. ጽድቅና ዓመፃ ወይም ኃጢአት 2) ይህ ክፍል በሁለት ተቀራኒ መንግሥታት መካከል ጦርነት እንዳለ ይናገራል፡፡ በዚህ ክፍል "ጦር" የሚለው ቃል በቀጥታ ጦርነትን ያመላክታል፡፡ እንዚህ ሁለት ተቀራኒ መንግሥታት እስካሉ ድረስ መቼም ጦርነት እንደማይጠፋ በደንብ እንውቃለን፡፡ ጦርነት ደግሞ ያለው ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ሕዝቡና በሰይጣን ድያብሎስ መካከልም ነው፡፡  በዚህች ምድር እስካለን ድረስ ይህ ውጊያ ወይም ጦርነት እንዳለና የሚቀጥል መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል በኤፌሶን 6፥12 ላይ ይናገራል፡፡ "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” ይላል፡፡ 3) ይህ ክፍል ለዚህ ጦርነት የሚቀርብ መሳሪያ እንዳለ ይናገራል፡፡ ጦርነትን መቼም ብሆን በ...

3ቱ የክርስቲያን ልብሶች

Image
3ቱ_የክርስቲያን_ልብሶች |=================| ✍ለማነኛውም ሰው ልብስ መሠረታዊና አስፈላጊ  ነገር መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ለክርስቲያን ደግሞ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን መልበስ ያለበት እንደ ማነኛውም ዓይነት ሰው ልብስ ሳይሆን ልዩ የሆነ የልብስ ዓይነት አለ፡፡ እነዚህ ልብሶዎች ገበያ ላይ የማይገኙ፣ በገንዘብም የማይገዙ ደግሞ በፍፁም የማይሸጡ ፍፁም ድንቅ  ልብስ ናቸው፡፡ ✍በአጠቃላይ የሰው ልጅ ሦስት ዓይነት ልብስ ይለብሳል፡፡ እነዚህም፦ 1.ኢየሱስ ክርስቶስን ወይም ሰይጣን ዲያብሎስን 2. አዲሱን ሰው ወይም አሮጌውን ሰውን 3.የእግዚአብሔር ዕቃ ጦርን ወይም የጠላት ዕቃ ጦርን ➊አንደኛው ልብስ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ✍ማነኛውም ሰው ከምንም በላይ በመጀመሪያ ደረጃ መልበስ ያለበት የልብስ ዓይነት ክርስቶስ እንደሆነ የእግዚአብሔር ቃል በበገላትያ 3፥27 ላይ “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።” እያለ ይናገራል፡፡ በሮሜ 13:14 ላይም “ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።”  እያል በድጋሚ ይናገራል፡፡ ይህን ልብስ ያልለበስ ሰው ሁሉ የለበሰው የሰይጣን፣ የዓለም ወይም የሥጋ ልብስ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው ለብሶ የሚዞረው ሞትና ጥፋት ነው፡፡ ቶሎ ኢየሱስ ክርስቶስን በመልበስ የነፍሱን ዋስትና ማግኘት አለበት፡፡ ኢየሱስ ክርስቶሰን መልበስ ማለት ፦ -------------------------------------------- 1. በብርሃን መኖር፦ የኢሱስ ብርሃን ነው፡፡ ✍ኢየሱስ ክርስቶስን የለበሰ ብርሃንን መልበስ አ...

በፈተና የመደሰት ሚስጥር

#በፈተና_የመደሰት_ሚስጥር    ||•×××××××××××××××××ו|| "ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት" ያዕቆብ 1፡2-3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 1ኛ. በዓለም እስካለን መከራ እንዳለ ማወቅ፡፡ ××××××××××××××××××××××××××××××  “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ" ዮሐንስ 16፥33 ❖የሰው ልጅ በምድር የሚኖርበት ዘመን ሁሉ በፈተና የተሞላ ነው፡፡ ማነኛውም ሰው በምድር እስካለ ድረስ በልዩ ልዩ ፈተና ይፈተናል፡፡ ለሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ፈተና አለው፡፡ ፈተናው የሚለየው በመጠኑና በይዘቱ እንጅ ለሁሉም ሰው ፈተና ይኖራል፡፡ ክር በመርፌ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ሁሉ ሰውም በሕይወት ዘመኑ በፈተና ውስጥ ያልፋል፡፡  ከፈተና ነፃ የሆነና ሁለ በደስታ የሚኖር ማንም የለም፡፡ ለእንድ ሰው ሁሉም ነገር ይኖራል ማለት ፈተና የለም ማለት አይደለም፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ለሁሉም አንደ አቅሙ መጠን ፈተና ወይም መከራ አለው፡፡ ኢየሱስ ስለእኔ መከራን ተቀበለ አይደል ታዲያ ለምን የኢየሱስን እየተከተልኩ ፈተና ይበዛል? የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል“ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤” ፊልጵስዩስ 1፥29፡፡ 2ኛ. መከራ በሕይወታችን ስደርስ አለመደነቅ፡፡ ×××××××××××××××××××××××××××××× "ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፡፡" 1ኛ ጴጥሮስ 4፡12 ❖አብዛኛው ጊዜ መከራ በእኛ ሕይወት ላይ ስደርስ እንፈራለን፣ እንደነግጣለን፣  ተስፋ እንቆርጣለን ደግሞ በእግዚ...

#አገልጋዮች_ውጤታማና_ፍሬአማ_አገልግሎት_ለማገልገል_በቅድሚያ_ማወቅ_ያለባቸው_ሦስት_ወሳኝ_ነጥቦች

Image
_____-------ኤፌ 3፡7-9--------_________ ❶ኛ. አገልጋዩ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ማወቅ አለበት።   ============================= ◉አንድ አገልጋይ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ማወቅ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጥ ጉዳዩ ነው። አንድ አገልጋይ ራሱ አገልጋይ መሆኑን ካላወቀ ማገልገል ለብቻው ምንም ትርጉም የለውም። ◉ይህ ጉዳይ አግልግሎትና አገልጋይን ለይቶ ከማወቅ ጋር  የተያያዘ ነው። እጅግ በጣም ብዙ አገልጋዮች በአገልጋይና በአገልግሎት መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነትን ለይቶ እንኳን አያውቁም። በስሜ አገልጋይ ናቸው ነገር ግን አገልጋይ ማለት ምን ማለት ነው? አገልጋይ ማነው? አገልግሎት ምንድነው ተብሎ ብጠየቅ ተገቢውን ምላሽ መመለስ አይችሉም። ⭐በመሠረቱ አገልጋይ ማለት በጌታው ፊት የሚያገለግል ፤ በጌታው ፊት የሚመላለስ፤ በጌታው ፊት  የሚቆም ቅን ሎሌ ፡ አሽከር ፡ ባሪያ ፡ ገረድ ( ኢዮ ፯፡፪ )። ⭐አገልጋይ ማለት የስም ጉዳይ ሳይሆን  የመጠራትና የመለየት ጉዳይ  ነው።  ✅ “ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።”— ሮሜ 1፥1-2 ◉ዛሬ በእኛ ዘመን ከበፊቱ እጅግ በጣም በተሻለ ሁኔታ ብዙ ዓይነት አገልጋዮች አሉት። ይሁን እንጅ ያሉትን አገልጋዮች በሙሉ አገልጋይ ናቸው ብለን ለመናገር አያስደፍርም። ምክንያቱም ለብዙዎች አገልጋይ የሚመስል አገልግሎት አላቸው እንጅ አገልጋይን የሚመስል የአገልጋይ ሕይወት የላቸውም። ◉ይህ እንደዚህ የሆነበት ትልቁ ምክንያት አብዛኞቹ አገልጋዮች አገልግሎታቸውን ከመጀመር በፍት መቅደም የሚገባውን ወሳኝ ነገርን አላስቀደሙም። ከአ...

የዛሬ ዮናስ ማነው?

Image
★የሰው ልጅ ለሚዘራው ለየትኛውም ዓይነት ዘር በስተመጨረሻ የሚታጨድ የራሱ የሆነ ፍሬ እንዳለው ሁሉ ሰው ለሚሠራው ለየትኛውም ዓይነት ሥራም (ክፉ ይሁን ደግ) የሚተርፍ ወይም የሚደርስ የራሱ የሆነ ውጤት ወይም ዋጋ አለው።  ★እዚህ ጋ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ድርጊቱ ወይም ሥራው የአንድ ግለሰብ ብሆንም የሥራው ውጤቱ ወይም ዋጋው የሚተርፈው ግን ለብዙዎች ነው። በአንድ ሰው ሥራ ምክንያት የሚመጣ የትኛውም ዓይነት መልካም ይሁን ክፉ ነገር የሚተርፈው ለአንድ ግለሰብ ወይም ለባለቤቱ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ጭምር ነው። ▦የእግዚአብሔር ቃል በዘጸአት 20፡5-6 ላይ ይህን እውነት ይይናገራል። "በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።" ★በሌላ ቦታ ደግሞ ለኃጢአተኞች የመጣ ቁጣ ለጻድቃንም እንደምተርፍ የእግዚአብሔርም ቃል ይናገራል። አው ለኃጢአተኞች የመጣ ቁጣ ለጻድቃንም ይተርፋል። ይህን ከእግዚአብሔር ቃል ማየት እንችላለን። ለምሳሌ፦ ●አሁን በምድራችን በተከሰተው በከሮና ቫይረስ ምክንያት እስካሁን ብቻ ባለን መረጃ ማለትም እስከ 08/08/12 ድረስ ከ2,088,240 በላይ ሰው በበሽታ ተይዟል። በዚህ በሽታ የሞተው የሰው ብዛት ደግሞ ከ134,720 በላይ ነው። እነዚህ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ናቸው? በፍጹም አይደሉም። ይህ ሌሎች ሰዎች የዘሩት የዘር ውጤት ነው። ●በመሪ በኢያሱ ዘመን በአካን ምክንያት ታላቅ የኢስራኤል ስራዊት በትንሿ በጋይም ሰዎች ተመቱ። ኢያሱ 7፥5 ✅እንደ ሕግ ከሆነ ኃጢአት የሰራው መሞትም ያለበት አካን ነበረ ነገር ግን የተመቱትና የሞቱ...

ውስጡ የጌታ ከሆነ ውጭው የማነው?

♦የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ♦መጽሐፍ ቅዱሳችን በምናይበት ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ብዙ ዓይነት ሐሰት አስተማሪዎች እንደሚነሱ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። ለአብነት ያህል በ2ኛ ጴጥሮስ 2፡1 ላይ "ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ" ይላል። ♦ሐሰት አስተማሪዎች እስካሉ ድረስ ደግሞ ሐሰት አስተምህሮዎች መኖሩ አይቀሬ ነው። መቼስ ሐሰት አስተማሪዎች የሚነሱት እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማስተማር ሳይሆን ውሸተኛውን የአባታቸውን የሰይጣን ትምህርት ለማስተማር ነው። ♦አሁን ጊዜው የዘመን መጨረሻ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ዓይነት ሐሰት አስተምህሮዎች በምድራችን ላይ ተነስቷል። አሁን ላይ ከተነሱት ከሐሰት አስተምህሮዎች አንዱ "አንድ ሰው አንድ ጊዜ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኋላ ኃጢአትን ብሰራ እንኳን በምንም ሁኔታ ደህንነቱን ሊያጣና ሊፈረድበት አይችልም። በገዛ ሥጋው ላይ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋ ጋር ጉዳይ የለውም። ሥጋ በዚህ ምድር የሚቀር አፈር ስለሆነ ሰው በሥጋው ላይ የፈለገውን ቢያደርግም ነገር ግን ነፍሱ ከዳነች ምንም ችግር የለም ምክንያቱም የውስጡ የጌታ ነው ውጪ የአፈር ነው " የሚል ነው። ♦ይህ ትምህርት ዓይነት በተለይም ለወጣቱ ትውልድ እጅግ በጣም የሚመች አስደሳችና ምርጥ ትምህርት ነው። ስጀመር ይህ ሐሰት አስተምህሮ ከመምጣቱም በፍት  በ1ኛ ሳሙኤል 16፥7 ላይ “ሰው ፊትን ያያል፥ እ...

እግዚአብሔር ለምድራችን ዕረፍት ይሰጣል

◉በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረም፥ በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ነበረ። እግዚአብሔር በመከራው ሁሉ ያስጨንቃቸው ነበርና። 2 ዜና 15፡4-5 ◉ይህ ዛሬ የእኛ ዘመን ነው። ከዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ምድራችን🌎🌐 ያሳርፋል። እግዚአብሔር ለምድራችን 🌎🌐 ዕረፍትን ይሰጣል። ይህ ዕረፍት  ስሆን  ለሚወጣው ለሚገባው ሰላም ይሆናል፣ ከሰዎች መሀል ድንጋጤ ይወገዳል። ይህ ብቻ አይደለም፦ዓለማችን ከመከራና ከጭንቀት ታርፋለች። ◉ነገር ግን ይህ ሁሉ ዝንብሎ አይመጣም። ይህን ዕረፍት ወደ ምድራችን ለማምጣት ማድረግ ያለብን ነገሮች አሉ። ➽የእግዚአብሔርን ቃልን ስንመለከት በራሳቸው ዘመን ለራሳቸው ምድር የዕረፍት ምክንያት  የሆኑ ሰዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ፦ ▦➀በኢያሱ መጽሐፍ  በምዕራፍ በ11፤14 ላይ ኢያሱና በካሌብ፦ ➖➤በእነርሱ ዘመን በእነርሱ ምክንያት ምድርቷ ከውጊያ አረፈች።  ▦➁በመሳፍንት መጽሐፍ በምዕራፍ በ3፤5፣8 ላይ ጎቶንያል፣ ድቦራና ጌዴዎን፦ ➖➤በእነርሱ ዘመን በእነርሱ ምክንያት ምድርቷ ለአርባ ዓመት  ዐረፈች። ▦➂በመሳፍንት መጽሐፍ በምዕራፍ በ3 ላይ  ናዖድ፦ ➖➤በእርሱ ዘመን በእርሱ ምክንያት ምድርቷ ሰማንያ ዓመት ዐረፈች። ▦➃በ2 ዜና 14፥1 ደግሞ አብያ፦ ➖➤በእርሱ ዘመን በእርሱ ምክንያት ምድርቷ አሥር ዓመት ያህል ዐረፈች። ◉እኛ ወጣቶች ለዚህች (በመከራ፣ በጭንቀት፣ በጥፋት ላለች) ምድር የዕረፍት ምክንያት መሆን አለብን። ዛሬ ለዚህች ምድር እናስፈልጋታለን። ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን አራት ነጥቦችን ማድረግ አለብን። 🔵1ኛ.ከሕይወታችን ከመካከላችን እግዚአብሔር የማይወደውን አጸያፊ ነገርን እናስወግድ። □ “ከይሁዳና ከቢንያምም አገ...

ማን ነገረህ?

▦የተወደዳችሁ፣ የተመረጣችሁና የተከበራችሁ ውድ ወገኖቼ፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ዛሬም እንደተለመደው አንድ መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤያለሁና እንድታነቡት እጋብዛለሁ። ውድ ወገኖቼ፤ እስከዛሬ በእናንተ ሕይወት ላይ ብዙ ነገር ተወርቶና ተነግሮ ወይም ተብሎ እናንተ ደግሞ ስምታችሁ ይሆናል። ለአብነትም ያህል ፈሪ ነህ፣ ደካማ፣ አትችልም፣ አትጠቅምም፣ አይሆንም፣ አይሳካም፣ አትሄድም፣ አትወጣም፣ አትደርስም፣ አትወርስም፣ እንድህ አትሆንም ወይም ደግሞ እንድህ አይደለህም እና ወዘተ የተባሉ አንጀት ብጥስና ቀስም ስብር የሚያደርጉ መጥፎና አሉታዊ (#Negative) ንግግሮችን ወይም ቃላቶችን በሕይወታችሁ ተነግሮና ተወርቶ እናንተም በበኩላችሁ ሰምታችሁ ይሆናል። ከዚህም የተነሳ ብዙዎቻችሁ ምናልባት አልቅሳችሁ፣ አዝናችሁ ወይም ደግሞ ተስፋም ቆርጣችሁ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነትንም አጥታችሁ፣ የተባለውንና የተነገረውን ንግግሮችንና ቃላቶችን እንዳለ ተቀብላችሁ ዛሬ ላይ በማይሆንና እናንተንም በማይመጥን ቦታ ላይ ትኖሩ ይሆናል። እሽ ይሁን ግድ የለም። ግን ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ። በእናንተ ሕይወት ምን እንደተነገረ ወይም ምን እንደተወራ ወይም ደግሞ ምን እንደተባለ አሁን በደንብ አስቡት። በእናንተ ሕይወት ላይ ምን ያህል መጥፎና አሉታዊ ንግግሮችና ቃላቶች እንደተነገሩ፤ አንደተወሩና እንደተባሉ እናንተ ራሳችሁ በደንብ ታውቁታላችሁ። አሁን ጥያቄ ምን ተነገረ፣ ምን ተባለ ወይም ደግሞ ምን ተወራ የሚለውን አይደለም። አሁን ጥያቄው የሚሆነው ይህን ሁሉ ማን ነገረህ፣ ማን አወራ ወይም ደግሞ ማን አለ የሚለው ነው። ▦ ...

#ለኢየሱስ_ሞት_ተገቢውን_ዋጋ_እንስጥ

Image
❖የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ውድ የጓደኞቼ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። እናንተና እግዚአብሔር በሚተዋወቁበት በየትኛውም ዓይነት ጉዳይ ላይ #ፋስካ_ይሁን እያልኩ አንድ አጭር መልዕክት ላካፍላችሁ። ❖ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ እንስጥ እላለሁ። ይህ በዓል ለእኛ በተለይም ለአማኞች ከበዓል ያለፈ ትልቅ ትርጉም ያለውና ዘወትር መታሰብ ያለበት በዓል ነው። ይህ በዓል ለእኛ ለአማኞች ምን ማለት እንደሆነ መናገር እንኳን አያስፈልግም። የዚህን በዓል ምንነት እኔ መናገር ከሚችለው በላይ በደንብ ታውቁታላችሁ። ❖አሁን ለማንሳት የፈለኩት ዋናው ጉዳይ የዚህን በዓል ምንነት ማወቅ አለማወቅ አይደለም። ዛሬ ሁላችሁንም ለመጠየቅ ያሰብኩት ጥያቄ ለመሆኑ በዓሉን ከማክበርና ከማወቅ ያለፈ ስንቶቻችን ለዚህ በዓል ተገቢውን ዋጋ ሰተን እናውቃለን? ተገቢውን ዋጋ መስጠት ስባል ምን ማለት ነው? ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ ◉በመሰረቱ ለእኛ የተከፈለው ዋጋ በምንም የሚከፈል አይደለም። ምንም እንኳን ለእኛ የተከፈለውን ዋጋ መክፈል ባንችልም ነገር ግን ለተከፈለው ዋጋ ተገቢውን ዋጋ መሰጠት እንችላለን። ኢየሱስ ክርስቶስም ከእኛ የሚፈልገው ይህንን ነው። ይህን በትክክል ማድረግ ከቻለን ዋጋውን እንደ መክፈል ይቆጠራል። ◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መስጠት ስባል በበዓሉ ወቅት በዓሉን ማሰብ፣ በዓሉን ማክበር፣ ምናልባት የሕማማት ሳምንትን በፆምና በፀሎት ማሳለፍ ወይም ደግሞ የተለያዩ በጎ ነገሮችን ማድረግና በበዓሉ መደሰት ማለት አይደለም። ◉ለኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተገቢውን ዋጋ መሰጠት ማለት በ...